#ጋምቤላ
አዲስ አመራር ከመጣ በኃላ በጋምቤላ መሻሻል ታይቷል ?
በጋምቤላ ክልል ካለፈው ነሐሴ 2016 ዓ/ም ወዲህ የአመራር ለውጥ ከተደረገ ወዲህ በክልሉ የነበረው የሠላም ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን አዲሱ አስተዳደር፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንዲሁም ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ባለፈው ዓመት በጋምቤላ ክልል በተለያዩ አካባቢዎችና ጊዜዎች ግጭቶች እየተከሰቱ በሰው ህይዎት ላይ ጉዳት ሲደርስ ቆይቷል።
ከሰብዓዊ ጉዳቱ ባሻገር በክልሉ ነዋሪዎች መካክል የነበሩ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በአንዳንድ ቦታዎች እስከመገደብ ደርሰውም ነበር።
የክልሉ ልማትና ሰላምም በእጅጉ ተጎደቶ ነበር።
በተለይ ቀደም ባሉት ጊዜዎች የአኙዋክ ተውላጆች ወደ ኑዌር ሰፈር አይሄዱም፣ ኑዌሮችም በተመሳሳይ ወደ አኙዋክ ሰፈር ይሻገሩ አልነበረም።
አሁን ላይ ግን ሁኔታዎች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን የጋምቤላ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የጋምቤላ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ጋትሏክ ሮን ምን አሉ ?
- ችግሮችን ለማስተካክልና በክልሉ ሠላም ለማስፈንና ህዝቡን ወደልማት ለማምጣት በክልሉ ከነሐሴ 2016 ዓ/ም መጀመሪያ ሳምንት ላይ የአመራር ለውጥ በመደረጉ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ሠላም ሰፍኗል።
- በክልሉ በነበረው የሠላም እጦት ምክንያት የጋምቤላ ከተማ የአኙዋክና የኑዌር በሚል ተከፍሎ አኙዋኮች ወደ ኑዌር ሰፈር፣ ኑዌሮችም ወደ አኙዋክ መንደር ለመሻገር ችግሮች ነበሩ። አሁን ያ ሁሉ ቀርቶ አዲሱ አመራር ወደ ሥራ ከገባና ህዝባዊ ውይይቶች ከተደረጉ በኋላ ሁሉም በሠላም በሁሉም ሥፍራ ይንቀሳቀሳል።
🔵 ማሉት ዴቪድ የተባሉ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ የምክትል ርዕሰ መስተዳድሩን ሀሳብ ይጋሩታል፣ አሁን አንዱ ወደ ሌላው ያለስጋት እንደሚንቀሳቀስ ነው ያረጋገጡት። ከተማውም ሠላም እንደሆን አመልክተዋል።
- አዳዲስ ሹመቶችና ምደባዎች ተሰጥተዋል። ይህም የትምህርት ዝግጅትንና የሥራ ልምድን መሠረት ያደረገ ነው።
- ለውጥ ያመጣሉ ተብሎ የታመነባቸው ቀደም ሲል ስልጣን ላይ የነበሩና ህዝባዊ አመለካከት ያላቸው በርከት ያሉ አመራሮችም በአዲሱ ሹመትና ምደባ እንደገና ተካተዋል።
- " ሠላም ወርዶ ህዝቡ በልማት መካስ አለበት " በሚል እሳቤ እውቀት፣ ልምድና የተሻል አመለካክትና እይታ ያላችው ሠዎች ወደ አመራሩ ተካተዋል።
- በኮታ መታሰር ቀርቷል። ቀደም ሲል በነበረው አሰራር ወንጀል ያልሰሩ ሰዎች በኮታ ጭምር ይታሰሩ ነበር። አሁን ግን በወንጀል የተጠረጠሩትን ብቻ ተጠያቂ የሚያደርግ አሰራር ተዘርግቷል።
- በፊት አንድ ኑዌር ቢያጠፋና ቢታሰር ሌላ አኙዋክ አብሮ እንዲታሰር ይደረግ ነበር፣ ሌላ አኙዋክ አጥፍቶ ቢታሰር የኑዌር ተወላጅ ተደርቦ እንዲታሰር ይደረግ ነበር ፤ አሁን ግን ጠፋተኛው ከየትኛውም ወገን ይሁን ጠፋተኛ ከሆን ተጠርጣሪው ብቻ ተለይቶ ተጠያቂ ይሆናል። የኮታ እስር ቀርቷል።
" ከአዲሱ አመራር ጋር ለመስራት ዝግጁ ነኝ " - ጋብዴን
የጋምቤላ ብሔራዊ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ጋብዴን) ሊቀመንበር አቶ ኡባንግ ኡሞድ ቀደም ሲል የነበረው አመራር ህዝቡን መምራት እንዳልቻለና ለውጥ እንዲመጣ ሲታግሉ እንደንበር ገልጠዋል።
ችግሩ የአመራሩ ሆኖ ሳለ ህዝቡን በከፍተኛ የሠላም እጦት ውስጥ ከትቶት ነበር ነው ያሉት።
በክልሉ የነበረውን ችግር እስከ የተፎካካሪ ፓርቲ የጋራ ምክር ቤት በማድረስ የነበረው የሠላም እጦት እንዲታወቅ መደረጉንና ለውጥ እንዲደረግ በግልም በጋራም ትግል ሲደረግ እንደነበር አስረድተዋል።
አዲሶቹ አመራሮች በሕዝቡ ተቀባይነት ማግኘታቸውንና ፓርቲያቸውም በአዲሱ አመራር ደስተኛ መሆኑን አቶ ኡባንግ ተናግረዋል።
ከአዲሱ አመራር ጋርም በጋራ ለመስራት ዝግጁ እንደሆኑም ነው የገለጡት።
የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ነሐሴ 9/2016 ዓ ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡመድን የመጀመሪያዋ የክልል ሴት ርዕሰ መስተዳድር፣ ዶ/ር ጋትሏክ ሮንን ደግሞ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መሾሙ ይታወሳል።
ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።
@tikvahethiopia

❤353🕊55👏29🙏23😡12😱10🤔7😭7😢5🥰4
#ጋምቤላ
“ በተለይ በዚህ ወርና እስከ ሚያዚያ መጨረሻ የሙርሌ ታጣቂዎች የሚፈታተኑንበት ወቅት ነው። ምልክቶችን እያየን ነው ፤ እየመጡ ነው ” - ጋምቤላ ክልል
ከደቡብ ሱዳን በሚያዋስኑ ወረዳዎች ዘልቀው የሚገቡ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች የሚፈጸመው ጥቃት አለመቆሙን፣ ወቅቱ ታጣቂዎቹ ለጥቃት ሚበረታቱበት መሆኑን የጋምቤላ ክልል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።
ታጣቂዎቹ ድንበር ጥሰው በመግባት ህፃናትና ከብቶችን ዘርፈው እንደሚወስዱ በተደጋጋሚ የሚነገር ሲሆን፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያ፣ አሁንስ ጥቃቱ ቆመ ? እንደቀጠለ ነው? ሲል ጋምቤላ ክልልን ምላሽ ጠይቋል።
የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኦጁሉ ጊሎ በሰጡን ምላሽ፣ “ ሰውም ስለተደራጀ ትንሽ የቀነሰበት ሁኔታ አለ። ግን ታጣቂዎቹ አልፎ፣ አልፎ ደግሞ ይመጣሉ ” ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
“ በተለይ በዚህ ወርና እስከ ሚያዚያ መጨረሻ ድረስ ታጣቂዎቹ የሚፈታተኑንበት ወቅት ነው። ኩሬዎች ስለሚደርቁ ለእነርሱ መምጣት አመቺ ይሆናል። አሁን ትንሽ፣ ትንሽ ምልክቶችን እያየን ነው። እየመጡ ነው ” ብለዋል።
ከወር በፊት በአኮቦ ወንዝ አዋሳኝ ወረዳዎች በሙርሌ ታጣቂዎች ሊወሰዱ ከነበሩ 4 ልጆች ውስጥ ሚሊሻዎች ከታጣቂዎቹ ጋር ተታኩሰው 3 ህፃናት ሲመለሱ፣ የአንዱ ህይወት በተኩሱ ወቅት እንዳለፈ አስታውሰዋል።
ጋምቤላን ከደቡብ ሱዳን በሚያዋስኑ አራት ወረዳዎች በኩል እንደሚመጡ ጠቅሰው፣ “ ይህን ሁሉ በጸጥታ አካል እንዲጠበቅ ማድረግ ትንሽ ይከብዳል ” ሲሉ ተናግረዋል።
“ ክብደቱ ታጣቂዎቹ በቡድን ሳይሆን ተበታትነው 7፣ 10 እየሆኑ ነው የሚመጡት ” ያሉት አቶ ኦጁሉ፣ የአካባቢውን ማህበረሰብ በማደራጀትና በማስታጠቅ ራሱን እንዲጠብቅ ማድረግ አንዱ እየተወሰደ ያለ እርምጃ መሆኑን አስረድተዋል።
“ በተለይ ታጣቂዎቹ የሚገቡባቸው በሮች ላይ የሁላችንም የጋራ ጥረት ያስፈልጋል። ይሄን ሁሉን ድንበር በሰራዊት ለማስጠቅ በጣም ሰፊ ቦርደር ነው” ብለው፣ የሁለቱ ሀገራት መንግስታት እየተወያዩ እንደሆነ ገልጸዋል።
የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች መጀመሪያ ዓላማቸው ከብት መውሰድ እንደነበር፣ በኋላ ህፃናትንም አፍነው መውሰድ እንደጀመሩ፣ ህፃናቱንም ለባርነት እንደሚሸጧቸው ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መገለጹ ይታወሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA

😭571❤125😡76🙏54🕊41😢24💔19😱18🥰16👏9
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጋምቤላ
“ አውቶብሱ እየተጓዘ የሙርሌ ታጣቂዎች ከመንገድ አድፍጠው ተኩስ ከፍተውበት አራት ወንዶች፣ ሁለት ሴቶች መኪናው ውስጥ እንዳሉ ተገድለዋል ” - ክልሉ
ከዲማ ወደ ጋምቤላ ከተማ ከ30 በላይ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ አውቶብስ የሙርሌ ታጣቂዎች በከፈቱበት ተኩስ ንጹሐን መገደላቸውን የጋምቤላ ክልል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።
የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ኦጁሉ ጊሎ በሰጡን ቃል፣ የመርሌ ጎሳ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ 6 ተሳፋሪዎች መገደላቸውን ገልጸዋል።
ጥቃቱ የተፈጸመው እሁድ ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ/ም እንደሆነ፣ አውቶብሱ እየተጓዘ የሙርሌ ታጣቂዎች መንገድ ላይ ደፈጣ ይዘው ተኩስ እንደከፈቱበት፣ የጸጥታ አካላት አሁንም ክትትል እያደረጉ እንደሆነ አስረድተዋል።
“ አራት ወንዶች፣ ሁለት ሴቶች ከመኪናው እንዳሉ ተገድለዋል ” ሲሉ ገልጸዋል።
ከሟቾች ባሻገር በጥቃቱ የቆሰሉ እንዳሉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የጠየቃቸው ሲሆን፣ እስካሁን የደረሳቸው መረጃ የሟቾቹ እንደሆነ ተናግረዋል።
በአጋጣሚ በአውቶብሱ ተሳፍሮ የነበረ አንድ የክልሉ ቀበሌ ሚሊሻ በአንድ የሙርሌ ታጣቂ ላይ የአጸፋ እርምጃ ወስዶበት ታጣቂው እንደተገደለ የሚመለከት መረጃም እንደደረሳቸው አስረድተዋል።
“ ታጣቂዎቹ ከብት መዝረፍ፣ ህፃናት መውሰድ የለመደባቸው ትሬንድ ነው። እሁድ ባሱ የተመታበት ቦታ ብዙ ጊዜ የወረዳው ከፍተኛ አካላት ትኩረት የሚያደርበት ነው። ግን የትላንቱ ክስተት በአጋጣሚ ከባድ ነበር ” ብለዋል።
ከዚህ ቀደም በሙርሌ ታጣቂዎች ተገደለ የሚባለው አንድ፣ ሁለት ሰዎችን እንደነበር ያስታወሱት አቶ ኦጁሉ፣ “ የትላንቱ ጥቃት ትንሽ የሚያሳዝን ነው። ሆኖም ግን እዛ አካባቢ የጸጥታ አካላት አሁንም ቁጥጥር በአግባቡ ይሰራሉ ” ነው ያሉት።
ክልሉ ከወር በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል፣ “ በተለይ እስከ ሚያዚያ መጨረሻ ድረስ ታጣቂዎቹ የሚፈታተኑንበት ወቅት ነው። ኩሬዎች ስለሚደርቁ ለእነርሱ መምጣት አመቺ ይሆናል። አሁን ትንሽ፣ ትንሽ ምልክቶችን እያየን ነው። እየመጡ ነው ” ብሎ ነበር።
“ በተለይ ታጣቂዎቹ የሚገቡባቸው በሮች ላይ የሁላችንም የጋራ ጥረት ያስፈልጋል። ይሄን ሁሉን ድንበር በሰራዊት ለማስጠቅ በጣም አስቸጋሪ ነው ሰፊ ቦርደር ነው ” ሲል አስገንዝቦም ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ

😭885❤205😡91🤔53💔43🕊34😢32👏27🙏23🥰22😱14
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጋምቤላ
" አራት ሴቶች በደቡብ ሱዳን ታጣቂዎች ታፍነዉ ተወስደዋል " - የጋምቤላ ክልል ፖሊስ
➡️ " በአንድ ዓመት ብቻ 16 ሕፃናት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በታጣቂ ቡድኑ ተወስደዋል ! "
የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኦጉላ ኡጁሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት በትናትናው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት አከባቢ በአኝዋክ ብሔረሰብ ዞን በጎጊ ወረዳ ተዶ በሚጠራዉ አከባቢ የሙርሌ ታጣቂዎች አራት ሴቶችን አፍነዉ መዉሰዳቸዉን ተናግረዋል።
" ሙርሌ" የተሰኘዉ የደቡብ ሱዳን ታጣቂ ቡድኑ ከ14 እስከ 27 ዓመት ዕድሜ ክልል ዉስጥ ያሉ አራት ሴቶችን ወደ ፒኝውዶ ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ተኩስ በመክፈት አፍኖ እንደወሰዳቸዉ የገለፁት ኮሚሽነሩ አስቀድሞ በአከባቢዉ የነበሩ የጎግ ወረዳ ፖሊስ አባላትና ሚሊሻዎችን በኋላም የፌዴራል ፖሊስ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የፀጥታ መዋቅር የጋራ ግብረ ሃይል ታፍነዉ የተወሰዱትን ለማስመለስ ቡድኑን እየተከታተሉ መሆናቸዉንም አስታዉቀዋል።
በደቡብ ሱዳን የሚንቀሳቀሰው የሙርሌ ታጣቂ ቡድን ከጋምቤላ ክልል የተለያዩ አከባቢዎች በተደጋጋሚ ሰዎችን እያፈነ እንደሚወስድ የተናገሩት ኮሚሽነር ኦጉሉ በፀጥታ ሃይሎች ኦፕሬሽን ከተመለሱት በስተቀር አብዛኞቹን እንደሚገድልና ሱዳን ወስዶ ለጉልበት ስራ እንደሚሸጣቸዉም መረጃዎች እንደሚደርሷቸዉ ገልፀዋል።
ኮሚሽነሩ አክለዉም በ2017 ዓ/ም ብቻ 16 ሕፃናት እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ከብቶች በነዚህ የታጠቁ ቡድኖች ተዘርፈዋል ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahEthiopiaFamilyHW

❤678😢338😭115😡97💔44🕊30🙏20🤔19😱18🥰7👏1