TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ICS

የሕዝብ ተ/ም/ቤት የሕግ እና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን የ9 ወር አፈጻጸም ትላንት ገምግሟል።

ኮሚቴው ከዚህ ግምገማ በፊት ማለትም ሚያዚያ 3/2016 ላይ #ድንገተኛ ምልከታ አድርጎ ነበር።

ቋሚ ኮሚቴው ምን አለ ?

- ምንም እንኳ የተጀመሩ ሥራዎች ጥሩና ተስፋ ሰጪ ቢሆኑም በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን እና የተገልጋይን ቅሬታ መፍታት አልተቻለም።

- ተገልጋዮች አገልግሎት ለማግኘት ብለው በሚደርስባቸው እንግልትና ስቃይ ምክንያት በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ በድንገተኛ ምልከታ መመልከት ተችሏል።

- በዋና መ/ ቤቱ ተገልጋይ በተቋሙ ሠራተኞች ፦
➡️ #መሰደብ
➡️ #መመናጨቅ
➡️ #መገፍተር_ጭምር የሚደርስበት በመሆኑ ተገልጋይ በሥነ ምግባር መስተናገድ አለበት።

- በአዲስ አበባ " ካሳንቺስ አካባቢ " የሚገኘዉ የውጪ ዜጎች አገልግሎት ተቋም የሚሰጠው አገልግሎት ኢትዮጵያን የማይመጥን፣ ምቹ ያልሆነ እና የንጽህና ጉድለት ያለው ነው። ይህ መታረም አለበት።

- ዋናው መስሪያ ቤት ለአገልግሎት ምቹ ያልሆነ፣ ሕንፃው የቆየ እና አስፈላጊዉን የማሻሻያ ጥገና ያላገኘ ነው። ሕንፃው ከተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ባህሪ ጋር የማይጣጣም ስሪት ያለው ነው።

- በዋና መስሪያ ቤት ያለው መጨናነቅ እንዲቀንስ በአዲስ አበባ ከተማ ከአምስት ያላነሱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች እንዲከፈቱ የመፍትሔ ሃሳብ ቢሰጥም አልተፈጸመም። በተለይ በአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የማስፋፋት ሥራዎች መሠራት አለበት።

- የደላላ ሰንሰለት በመለየት ማቋረጥ ያስፈልጋል።

- አሁንም ከደላሎች ጋር የሚመሳጠሩ የተቋሙ #ሠራተኞች በመኖራቸው ትኩረት ሰጥቶ መሥራት አለበት።

- የሠራተኛ ባጅ አለመኖሩም ሊታሰብበት ይገባል።

በምክር ቤቱ የተገኙት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት ለተነሱት ጉዳዮች ምላሽ ሰጥተዋል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/EPA-04-27-2 #EPA

@tikvahethiopia
😭242👏10196😡42🙏13🕊10🥰5😢5😱3
#Passport

የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ተገልጿል።

የኢሚግሬሽን ዜግነትና አገልግሎት የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ገልጿል።

ፖስፖርት ለማደስ 5 ዓመት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ከአንድ ወር በኃላ ወደ ሥራ በሚገባው አሰራር መሰረት ግን ከ25 ዓመት በላይ ለሆናቸው ዜጎች በየ10 ዓመቱ እንደሚታደስ አገልግሎቱ ገልጿል።

#ICS #AHADU

@tikvahethiopia
👏3.76K348🙏185😡90😭53🕊44🤔37🥰29😢28😱17
" ነበሩ ፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜው እስኪያበቃ ጥቅም ላይ መዋሉን ይቀጥላል " -   የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

በኢትዮጵያ የተመረተ አዲስ ፓስፖርት ዛሬ ይፋ ሆኗል።

ፓስፖርቱ የግለሰቡን ባዮግራፊክ መረጃ ብቻ ሳይሆን የጣት ዐሻራ የያዘ የኤሌክትሮኒክስ ቺፕስ አለው ተብሏል።

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚመረተው ይህ ፓስፖርት፤ የቪዛ ገጾቹ የኢትዮጵያን መልክ የያዙ መሆናቸው ተጠቅሷል።

ይህም ከዚህ ቀደም በውጭ ሀገር አምራች ድርጅት እጅ የነበረውን ዲዛይን ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግሥት እንዲሸፈን አድርጓል ተብሏል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በአዲስ የዘርጋው የኢ-ፓስፖርት ሲስተም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስና በጃፓኑ ቶፓን ሴኩሪቲ ኢትዮጵያ አ.ማ. አማካይነት የተሰራ ነው።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ፤ ነበሩ ፓስፖርት የአገልግሎት ጊዜው እስኪያበቃ ጥቅም ላይ መዋሉን የሚቀጥል ሲሆን የዕድሳት ጊዜው ሲደርስ በኢ-ፓስፖርት ይተካል ተብሏል።

አገልግሎት መ/ቤቱ ፤ " 14 አዳዲስ ቅርንጫፎችን በመክፈትም አገልግሎቱን ለመስጠት ዝግጅት ተጠናቋል " ያለ ሲሆን " ከአንድ ነጥብ 5 ሚልየን በላይ ኢ-ፓስፖርት ታትሞ ተዘጋጅቷል " ሲል ገልጿል።

አዲሱ የኢ-ፓስፖርት በነበረው ዋጋ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እንደሚሆን የተነገረ ሲሆን  ደንበኞች ባሉበት ፓስፖርታቸውን በፍጥነት ማግኘት እንዲችሉ ያደርጋል ተብሏል።

"  አዲሱን ኢ-ፓስፖርት በሁለት ወር ከ10 ቀን ማግኘት ይቻላል " ሲል አገልግሎቱ አሳውቋል።

የፓስፖርቱ አገልግሎት ጊዜ 10 ዓመት ሲሆን የዜጎችን ጊዜ፣ ገንዘብ እና ጉልበት ይቆጥባል ተብሏል።

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰላማዊ ዳዊት ፥ " አዲሱ ኢ-ፓስፖርት እስከአሁን ኢትዮጵያ ካላት ፓስፖርት በአይነቱና በደረጃው እጅግ ከፍ ባለ ጥረት የተዘጋጀ የጉዞ ሰነድ ነው " ብለዋል።


#EPA #ICS

@tikvahethiopia
👏1.6K263😡255🙏71😭67🤔47🕊39😱29🥰28😢13
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Passport

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ለአዲስ አበባ አስቸኳይ ፓስፖርት አመልካቾች ባሰራጨው መልዕክት የአስቸኳይ ፖስፖርት ኦንላይን ሲስተም የተወሰነ ማሻሻያ ተደርጎበት ስራ መጀመሩን ገልጿል።

ከግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ሁሉም አመልካች በኦንላይን በማመልከት በቀጠሮ ቀኑ ብቻ ወደ ተቋሙ መሄድ መስተናገድ እንደሚችል አሳውቋል።

በኦን ላይን መሙላት ያልቻሉ አስቸኳይ ጉዳይ ያላቸው አመልካቾች በአካል መጥተው መስተናገድ እንደሚችሉ ገልጿል።

በተጨማሪ አገልግሎቱ ፥ " ከግንቦት 6/ 2017 ዓ/ም ጀምሮ መደበኛ የፓስፖርት አገልግሎት ከጠዋቱ 12:00 - 8:00 ሰአት ድረስ የአስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎት ደግሞ ከ9:00 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4:00 ሰአት በሁለት ፈረቃ እንሰጣለን በቀጠሮ ቀናችሁ በፕሮግራሙ መሰረት ወደተቋማችን በመምጣት ተስተናገዱ " ብሏል።

" ከቀጠሮ ቀን ውጭ በተቋሙ አካባቢ መቆምም ሆነ አላስፈላጊ እንቅስቃሴ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ ነው " ሲልም አሳስቧል።

#ICS

@tikvahethiopia
👏367100😡61🙏31😢21🕊13😭12🤔10🥰2😱2