#Dollar
💵 " ዶላርን በሌላ የመገበያያ ገንዘብ መተካት አይታሰብም፤ ይህን ባደረጉ አካላት ላይ 100% ታሪፍ እጥላለሁ '' - ትራምፕ
➡️ "አሜሪካ ሌሎች ሀገራት ዶላርን ብቻ እንዲጠቀሙ ለማስገደድ መሞከሯ ያለፈበት እሳቤ ነው '' - ሩሲያ
የአሜሪካው ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የBRICS+ አባል ሀገራት የአሜሪካን ዶላር ትተዉ በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ ለአሜሪካ ገበያ በሚያቀርቡት ሸቀጦቻቸዉ ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ እንደሚያደርጉ ዛቱ።
ትራምፕ ባሰራጩት ማስጠንቀቂያ የBRICS+ አባል ሐገራት ከዶላር ለማፈንገጥ ማሰባቸዉ " ማብቃት አለበት " ብለዋል።
" ዶላርን በሌላ የመገበያያ ገንዘብ መተካት አይታሰብም " ሲሉ ገልጻዋል።
የBRICS+ አባል መንግሥታትን ለአሜሪካ " የጠላትነት አዝማሚያ " የሚታይባቸዉ በማለት ወርፈዋል።
ትራም እነዚህ ሀገራት " ግዙፍ " ያሉትን የአሜሪካን ዶላር ለመተካት አዲስ ገንዘብ ካሳተሙ ወይም በሌላ ገንዘብ ለመጠቀም ከወሰኑ ከአሜሪካ ገበያ መሰናበት አለባቸዉ ብለዋል።
ትራምፕ እንደሚሉት የBRICS+ ሀገራት አዲስ ዶላር ትተው በሌላ ገንዘብ ለመገበያየት ከወሰኑ አስተዳደራቸው ወደ አሜሪካ በሚገቡ የየሀገራቱ ሸቀጦች ላይ የ100% የቀረጥ ጭማሪ ያደርጋል።
ሩሲያ ለዚሁ የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ዛቻ ምላሽ ሰጥታለች።
" አሜሪካ ሌሎች ሀገራት ዶላርን ብቻ እንዲጠቀሙ ለማስገደድ መሞከሯ ያለፈበት እሳቤ ነው " ብላለች።
የBRICS+ ቡድን ባሁኑ ወቅት #ኢትዮጵያን ጨምሮ 10 አባል መንግስታትን ያስተናብራል።
በኢንዲስትሪ የበለፀጉትን 6 ምዕራባዉያን ሀገራትና ጃፓንን የሚያስተናብረዉ ቡድን 7 የሚያደርሰዉን ተፅዕኖ ለመቋቋም ያለመ ነዉ።
ሩሲያና ቻይናን የመሳሰሉ የBRICS ጠንካራ አባላትና መሥራቾች የአሜሪካ ዶላር በዓለም ገበያ ላይ የሚያደርሰዉን ጫና አጥብቀዉ ይተቻሉ።
ማሕበራቸዉ አማራጭ መገበያያ እንደሚያስፈልገዉም ያሳስባሉ።
የአሜሪካዉ ፕሬዝደንት ግን ዶላርን መተካት " አስደናቂ " ከሚሉት ከአሜሪካ ምጣኔ ሐብት መሰናበት ነዉ።
መረጃው የዶቼቨለና ቴሌግራፍ ነው።
@tikvahethiopia

❤776😡381👏113🤔86😭74🕊39🙏35🥰33😱29😢14
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#SidamaBuna
ወላይታ ዲቻን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ያሸነፈው ሲዳማ ቡና በሚቀጥለው አመት #ኢትዮጵያን🇪🇹 በመወከል በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድር ይሳተፋል።
@tikvahethiopia
ወላይታ ዲቻን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ያሸነፈው ሲዳማ ቡና በሚቀጥለው አመት #ኢትዮጵያን
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1.25K😡160💔53👏52🙏50🕊41😭22🤔20🥰18😱7😢4
#Medrek
አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ የመድረክ ሊቀመንበር ሆኑ።
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሆነዋል።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) " ታሪካዊ " ሲል የጠራውን ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ አዲስ አመራር መምረጡን ይፋ አደረገ።
" በሀገሪቱ ብቸኛው ቀዳሚ የብሔር ብሔረሰቦች የፖለቲካ ጥምረት " እንደሆነ የገለጸው መድረክ 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ የውስጥ መነቃቃቱን የሚያበስር ወሳኝ እርምጃ እንደወሰደ ገልጿል።
በግንባሩ ጽ/ቤት የተካሄደው ጉባዔ፣ አዲስ አመራር በመምረጥና እውነተኛ ዴሞክራሲያዊትና ሰላማዊ #ኢትዮጵያን🇪🇹 ለመገንባት የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ በማስቀመጥ መጠናቀቁን አሳውቋል።
አዲስ የተመረጠው አመራር፣ ወጣት አመራሮችን ከተመክሮና ልምድ ካካበቱ አንጋፋ ፖለቲከኞች ጋር በስትራቴጂካዊ ቅንጅት ያካተተ እንደሆነና ይህም መድረክ የኢትዮጵያን ውስብስብ ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች በብቃት እንዲወጣ እንደሚያስችለው አመልክቷል።
አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆነው እነማን ተመረጡ ?
1. አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ ፦ የመድረክ ሊቀመንበር
2. አቶ ሱልጣን ቃሲም፦ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. ወ/ሮ መርየም ሓሰን ፦ ምክትል ሊቀመንበርና የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ
4. አቶ ሙላቱ ገመቹ፦ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ
5. ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ፦ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ
6. አቶ ለገሰ ለንቃሞ፦ የመድረክ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
7. አቶ ደስታ ዲንቃ፦ የመድረክ ምክትል ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል።
መድረክ ፦
- ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉዓላዊነት (ዓረና)፣
- የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣
- የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) እና የዓፋር ህዝብ ፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲን በአባልነት አቅፏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የደረሰው ከመድረክ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።
(NB. ከላይ የተያያዘው የመድረክ መግለጫ ነው)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
ፎቶ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ የመድረክ ሊቀመንበር ሆኑ።
ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሆነዋል።
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) " ታሪካዊ " ሲል የጠራውን ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዶ አዲስ አመራር መምረጡን ይፋ አደረገ።
" በሀገሪቱ ብቸኛው ቀዳሚ የብሔር ብሔረሰቦች የፖለቲካ ጥምረት " እንደሆነ የገለጸው መድረክ 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን በተሳካ ሁኔታ በማካሄድ የውስጥ መነቃቃቱን የሚያበስር ወሳኝ እርምጃ እንደወሰደ ገልጿል።
በግንባሩ ጽ/ቤት የተካሄደው ጉባዔ፣ አዲስ አመራር በመምረጥና እውነተኛ ዴሞክራሲያዊትና ሰላማዊ #ኢትዮጵያን
አዲስ የተመረጠው አመራር፣ ወጣት አመራሮችን ከተመክሮና ልምድ ካካበቱ አንጋፋ ፖለቲከኞች ጋር በስትራቴጂካዊ ቅንጅት ያካተተ እንደሆነና ይህም መድረክ የኢትዮጵያን ውስብስብ ፖለቲካዊ ተግዳሮቶች በብቃት እንዲወጣ እንደሚያስችለው አመልክቷል።
አዲሱ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሆነው እነማን ተመረጡ ?
1. አቶ ዓምዶም ገብረስላሴ ፦ የመድረክ ሊቀመንበር
2. አቶ ሱልጣን ቃሲም፦ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
3. ወ/ሮ መርየም ሓሰን ፦ ምክትል ሊቀመንበርና የፋይናንስ ጉዳይ ኃላፊ
4. አቶ ሙላቱ ገመቹ፦ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበርና የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ
5. ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ፦ ምክትል ሊቀመንበርና የውጭ ጉዳይ ኃላፊ
6. አቶ ለገሰ ለንቃሞ፦ የመድረክ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ
7. አቶ ደስታ ዲንቃ፦ የመድረክ ምክትል ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ተመርጠዋል።
መድረክ ፦
- ዓረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉዓላዊነት (ዓረና)፣
- የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ)፣
- የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) እና የዓፋር ህዝብ ፍትህና ዲሞክራሲ ፓርቲን በአባልነት አቅፏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃው የደረሰው ከመድረክ ህዝብ ግንኙነት ክፍል ነው።
(NB. ከላይ የተያያዘው የመድረክ መግለጫ ነው)
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopiaFamilyAA
ፎቶ፦ ፋይል
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤1.32K🤔129👏76😡58🙏36😭35🕊25😱14😢14🥰5
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ውሳኔ " ተገቢና ህግን ያልተከተለ ውሳኔ " ሲል ተቃወመ። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፈዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ዋንጫ ከሲዳማ ቡና ተነጥቆ ለወላይታ ዲቻ እንዲመለስ ሲል ውሳኔ አሳልፏል። ይህ ተከትሎ የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ቦርድ ውሳኔውን " ተገቢነት የለሌው ውሳኔ ነው። ውሳኔው እጅግ አሳዝኖናል…
" ተክሰናል ፤ ሕዝቡ በልዩ ልዩ መንገዶች ደስታዉን እየገለፀ ነዉ " - የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ
ዛሬ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ያስተላለፈዉን ዉሳኔ ተከትሎ የሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ " የኢትዮጵያ ዋንጫን " ለወላይታ ዲቻ ይመልሳል ወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ቡድንም በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ #ኢትዮጵያን የሚወክል ይሆናል።
ይህን የፌደሬሽኑን ዉሳኔ ተከትሎ የወላይታ ዲቻ ደጋፊዎች በአደባባይ ደስታቸዉን የገለፁ ሲሆን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጥላላ ከበደን ጨምሮ የክልሉና የወላይታ ዞን አመራሮች " የእንኳን ደስ ያላችሁ " መልዕክት አስተላልፈዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ያነጋገርናቸው የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ክለብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሰፋ ሆሲሶ " ዉሳኔዉ በእግር ኳሱ ዘርፍ ተስፋ ሰጪና ለወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ትልቅ ደስታን የፈጠረ ተገቢ ዉሳኔ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
" ተክሰናል " ያሉት ስራ አስኪያጁ " የዉሳኔዉን አፈጻጸም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በሚያስቀሚጠዉ ዕቅድ መሰረት ተፈፃሚ እናደርጋለን " ብለዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
ሀዋሳ
#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

❤1.53K😱173😡143🤔78👏56😭39🕊33🙏28🥰27💔11😢5