TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የመምህራንድምጽ

° " ግንባታው እንዲቆም ተደርጎብናል " - መምህራን

° " ጉዳዩን የጸረሙስና አካላት ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል፤ ምርመራ ተጀምሯል " - የሀዋሳ ፖሊስ

ከሰሞኑን " በማህበር ተደራጅተን የምንገነባውን የመኖሪያ ቤት ግንባታ በማስቆም እንዲገነባልን ውል የገባውን ተቋራጭ አሰሩብን " ያሉ የሀዋሳ ከተማ መምህራን ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

መምህራኑ " አመራሩ ሊደግፈን ሲገባ እየገፋን ነው " ብለዋል።

" በሀገሪቱ ጠ/ ሚኒስትር ሳይቀር ለመምህራን ድጋፍ ተደርጎ የቤት ባለቤት የምንሆንበት መንገድ ይመቻች በተባለበት በዚህ ወቅት መምህራን የሚገነቡትን ቤት አስቁሞ ተቋራጭን ማሰር መንግስትና መምህራንን ለማጋጨት የታሰበ ሴራ እንጅ ሌላ ምንም አይደለም " ብለዋል።

" ድርጊቱ አሳፋሪ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

መምህራኑ፤ ከሳምንት በፊት አመራሩ በመምጣት " በርቱ " እንዳላቸውና ከፌደራል ሳይቀር እንግዳ ጋብዞ ፣ እገዛ ልናደርግ ዝግጁ ነን " እንዳላቸው ተናግረዋል።

በድንገት ግን ተገልብጦ ስራው ህጋዊ አይደለም ማለቱን ጠቁመዋል።

" ችግሮች ቢኖሩ እንኳን በውይይት ማስተካከል ይቻላል " የሚሉት መምህራኑ ለ9 አመታት የቆመ ቤት ድንገት መሰራት ሲጀምር ለማስቆም መሯሯጥ ከጀርባው ሌላ ዓላማ ያነገበ እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልጸዋል።

መምህራኑ ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚያሰሩትን የህንጻ ዲዛይን ከG+3 ወደ G+4 መቀየራቸውን የከተማው ማዘጋጃ ቤት የማህበራት ማደራጃ እና የከንቲባ ጽህፈት ቤት የሚያውቀው እንደሆነ ጠቁመዋል።

ይህ ሆኖ እያለ ግንባታው #እንዲቆም መታዘዙን ገልጸው ፤ " ወቅቱ መምህራን የሚደገፉበት እንጅ ጥሪታቸውን ያፈሰሱበትን የሚቀሙበት አይደለምና እንቅፋት የሆኑብን አካላት ሊተዉን ይገባል " ብለዋል።

" በህግ አምላክ እጃችሁን ከድሀው መምህራን ላይ አንሱልን ፤ ይህ ባይሆን ግን አደባባይ በመውጣት ጩኸታችንን ለማሰማት ዝግጁ ነን " ሲሉም ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የከተማው አስተዳደር ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በአጠቃላይ ለስድስት የመምህራን መ/ቤቶች ህብረት ስራ ማህበራት የጻፈውን ደብዳቤ ደርሶት ተመልክቷል።

በዚህም ደብዳቤው ፦

- የነበረው ዲዛይን ከG+3 ወደ G+4 ማስተካከያ እንዲደረግ ተጠይቆ የG+4 ዲዛይን መሰጠቱ ፤

- ነገር ግን ይህ ዲዛይን የመምህራን መ/ቤቶች ማህበራት ከተደራጁበት አላማ አንጻር ተጻራሪ ዓላማ እንዳለው ስለተደረሰበት የG+4 ዲዛይን መሰረዙን ሌላ ደብዳቤ እስኪላክላቸው ድረስ ቀድሞ በነበረውም G+3 ዲዛይን ግንባታ ማካሄድ እንደማይችሉ ያዛል።

የመምህራኑን ጥያቄ ይዘን ጥያቄ ያቀረብንለት የከተማው ፖሊስ ጉዳዩን የጸረሙስና አካላት ወደ ፍርድ ቤት ወስደዉ ምርመራ እንደጀመሩበት በመግለጽ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🤔9771😡27😢10😱9🕊8👏7🙏4🥰3😭3