TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ProsperityParty #TPLF

ህወሓት እና ብልፅግና የጀመሩት ፓለቲካዊ  ውይይት ቀጥለውበታል።

ፓርቲዎቹ ዛሬ ግንቦት 7/2016 ዓ.ም በመቐለ ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ ውይይት አካሂደዋል።

ህወሓት ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ብልፅግና እና ህወሓት መሰረታዊ የአላማና የአይዲዮሎጂ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች ናቸው " ያለ ሲሆን " ልዩነት እንዳለ ሆኖ ሊወያዩባቸው የሚገባ በርከታ የጋራ አጀንዳዎች አሉዋቸው " ብሏል።

ብልጽግና ፓርቲ በበኩሉ ፤ " ቀደም ሲል የተደረሰውን የፓርቲ ለፓርቲ የግንኙነት መርሆዎች በማስታወስና የተጀመሩትን ዋና ዋና አጀንዳዎች የመለየት ሂደት በማጠናቀቅ በአጀንዳዎቹ ቅደም ተከተል ላይ መክረናል " ሲል ገልጿል።

" ከዘላቂ ሰላም ማረጋገጥ ጋር ተያይዞ በዝርዝር ውይይት በማድረግ ለዘላቂ ሰላም መረጋገጥ በጋራ በቁርጠኝነት ለመስራት ተስማምተናል " ሲል አሳውቋል።

ከዚህ ባለፈ ፦

- " በቅርቡ በራያ የተፈጠረውን የግጭት ክስተት በተመለከተ በዝርዝር ውይይት ተደርጎ ክስተቱ መፈጠር ያልነበረበትና ከተጀመረው ዘላቂ ሰላም የማረጋገጥ ሂደት ጋር የሚቃረን እንደሆነ መግባባት ላይ ተደርሷል " ብሏል።

- ማንኛውንም ጉዳይ በሰላማዊ መንገድና በውይይት እየፈቱ ለመሄድ በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል።

- የኮሚኒኬሽን ስራዎች የሰላም ሂደቱን የሚደግፉና ግጭት ቀስቃሽ ከሆኑ ንግግሮችና ይዘቶች የተቆጠቡ እንዲሆኑ መግባባት ላይ ተደርሷል ብሏል።

- ማናቸውንም ግጭት የሚፈጥሩ አዝማሚያዎችን በጋራ ለመከላከል እና ከተፈጠሩም በፍጥነት ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት ለመስራት ስምምነት ላይ መደረሱን አመልክቷል።

- የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ወደ መሬት ለማውረድ እየተሰሩ ላሉ ስራዎች ስኬት ምቹ ፖለቲካዊ ሁኔታ ለመፍጠር ሁለቱም ፓርቲዎች ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

#ProsperityParty #TPLF

@tikvahethiopia
🕊428😡19197🙏31👏29😭25🤔20🥰17😱9😢8