TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ቻይና

ኢትዮጵያ ለአንድ ቻይና ፖሊሲ አሁንም አቋሟ ያልተቀየረና የፀና መሆኑን አሳውቃለች።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤ ኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ ላይ ያላት አቋም ዛሬም የጸና ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ የአንዲት ቻይና ፖሊሲን ለረጅም ዓመታት ስታራምድ መቆየቷን አስታውሰው ይህ አቋሟ በዘመናት መካከል መንግስታት አፅንተው የያዙት መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ ላይ ያላት አቋም ዛሬም የጸና መሆኑን አረጋግጠዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከሰሞኑን ራሷን ከቻይና ነጥላ እንደ ነፃ ሀገር በምትቆጥረው ታይዋን ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ተደርጎ ነበር።

በዚህ ምርጫ ቻይና አትወዳቸውም የሚባሉት፣ አስቸጋሪና አደገኛ ሰው ብላቸው የምትጠራቸው በሙያቸው ሐኪም የሆኑት ዊሊያም ላይ ማሸነፋቸው ተዘግቧል።

ዶክተሩ " ለቻይና አንንበረከክም !! " በሚል አቋማቸው ነው የሚታወቁት።

ቻይና ከምርጫው በፊት አምርራ ለምትጠላው ለገዢው ዲሞክራቲክ ፕሮግረሲቭ ፓርቲ (ዲፒፒ) ህዝቡ ድምጽ እንዳይሰጡ አሳስባ የነበረ ቢሆንም የዚሁ ፓርቲ አባል የሆኑት የሕክምና ዶክተሩ ዊሊያም ላይ ቺንግ አሸንፈዋል።

ሰውየው በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት " ታይዋን ነጻ አገር መሆኗን ማወጅ አያስፈልጋትም፣ ምክንያቱም ታይዋን ሉአላዊና ነጻ አገር ስለሆነች " ብለዋል።

ይህንን ምርጫ ተከትሎ ሀገራት አቋማቸውን እና አስተያየታቸውን ሲሰጡ ነበር።

አሜሪካ በምርጫው ላሸነፉት ፕሬዜዳንት በይፋ የ" እንኳን ደስ አልዎት " መልዕክት አስተላልፋ ፤ ከታይዋን እና ከገዢው ፓርቲ ጋር ያላትን ግንኙነት እንደምታጠናክር አሳውቃለች።

ከምርጫው በኃላ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ፤ " እኛ ነፃነትን አንደግፍም ... " የሚል አስተያየት ሰጥተው ነበር።

አሜሪካ ከታይዋን ጋር ይፋዊ ያልሆኑ ግንኙነቶች ያሏት ሲሆን ታዋይም የአሜሪካ ድጋፍ እንዳላት በተለያየ ጊዜ ተናግራለች ፤ የአሁኑን ምርጫም ተከትሎ የቀድሞ ብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ስቴፋን ሃድሌይ ጭምር ያሉበት ይፋዊ ያልሆነ ልዑክ ወደ ታይዋን ልካ ከአሁኑ ተመራጭ ፕሬዜዳንት እና ከቀድሞ ጋር ውይይት አድርጋለች።

ከአሜሪካ በተጨማሪ፣ ዩናይትድ ኪንግደም፣ የአውሮፓ ህብረት፣ እንዲሁም ካናዳ ፣ ጃፓን ለገዢው ፓርቲ ደስታ መልዕክት አስተለልፈዋል።

በሌላ በኩል፤ ሩስያ ምርጫውን ተከትሎ ታይዋን የቻይና አንድ አካል መሆኗን ገልጻለች። ኢራን ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ቬትናም ፣ታጃኪስታን " የአንድ ቻይና " ፖሊሲን እንደምትደግፍ አረጋግጣለች።

ከአፍሪካ ደግሞ የኢትዮጵያ ጎረቤት ሶማሊያ ለአንድ ቻይና ፖሊሲ ድጋፍ በማሳየት ፤ ታይዋን የቻይና ግዛት ናት ስትል መግለጫ አውጥታለች። ከቀናት በፊት ቻይና " ሶማሌላንድ የሶማሊያ ግዛት ናት " ማለቷ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ስለምርጫው ምንም ባትልም አሁንም " የአንድ ቻይና " ፖሊሲዋ እንዳልተቀየረ አሳውቃለች።

ቻይና ታይዋንን " የራሷ ግዛት አድርጋ ነው የምታስባት፤ #ወደ_እናት_ሀገሯ መመለስ አለባትም ብላ ታምናለች ለዚህም ታይዋንን የሚደግፉ ሁሉ በሀገር አንድነት ላይ አደጋ ያመጡ አድርጋ ነው የምትወስዳቸው።

@tikvahethiopia
701😡228🕊88🙏70😭43🥰26😱21😢21