TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አማራ #ዋግኽምራ " ዞኑ ከነበሩት 33 አምቡላንሶች አሁን ላይ 9 አምቡላንሶች ብቻ ነው ያሉት። … የህፃናትና የእናቶች የህክምና አገልግሎት አደጋ ውስጥ ነው " - የዋግኽምራ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ ፦ * የመድኃኒት፣ * የትራንስፖርት፣ * የሕክምና መሣሪያዎች እጥረት በማጋጠሙ በዞኑ የሚገኙ የሕክምና ተቋማት አገልግሎት ለመስጠት ፈተና እንደሆነባቸው በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሄረሰብ…
#ዋግኽምራ

" ድርቁ በጣም እየባሰ ነው። መታከም ያለባቸው ህፃናት ለተከታታይ 2 ወራት ምንም አልተደረገላቸውም" - ዋግኽምራ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ

በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ በዞኑ ስላሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

- ድርቁ በጣም #እየባሰ ነው። ባለፈው ጥናት ካጠናን በኋላ ሊደረግ የሚገባው ግን ያልተደረገ በጣም በስፋት ነው ያለው።

- የምግብ እጥረት እንዳለባቸው በተረጋገጠው መሠረት #ህፃናት #ነፍሰጡር#አጥቢ እናቶች ወደ ተለያዩ ፕሮግራሞች ገብተው ሊደገፉ ነበር። እስቲል ማሟያ ምግብ በምንለው እጥረት እስካሁን ምንም  አልተደረገላቸውም። እኛ #እየጮህን ነው። እስካሁን የመጣ፣ የተደረገ ድጋፍም የለም።

- በሌላ በኩል ድርቅ በተከሰተባችው አካባቢዎች አጠቃላይ የጤና መድህን የምንለው ፕሮግራም የአመት ክፍያው የሚያልቀው አሁን ነው። አልፎ ለማስከፈልም አልቻልንም። በጠቅላላ የጤና አገልግሎታቸው በጣም #የሚያሳዝን ሁኔታ እየገባንበት ያለንበት ሁኔታ ነው ያለው።

ምን ያህል ህፃናትና እናቶች ናቸው አሁን አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው? 

* በድርቅ የተጎዱት ወደ 33,000 የሚሆኑ ሰዎች ናቸው ከአንድ ወረዳ ብቻ። በአጠቃላይ እንደ ዞን በዚህ ድርቅ ተጎድተዋል ብለን የምናስባቸው ከ180,000 በላይ ህዝቦች ናቸው። 

* ከእዚህ ውስጥ የሚበዙት ነፍሰጡርና አጥቢ እናቶች ናቸው። ወደ 7,000 ይደርሳሉ #ነፍሰጡርና አጥቢዎች ብቻ። ከአምስት ዓመት በታች #ህፃናት ኦልሞስት ወደ #18,000 አካባቢ ይደርሳሉ። እነዚህ ሁሉ አስቸኳይ ምግብ የሚፈልጉ ናቸው።

አቶ አሰፋ ታጣቂዎችን በተመለከተ ምን አሉ ?

° ታጣቂዎች የመጀመሪያ ታርጌታቸው ጤና ተቋማትን መዝርፍ ነው። እኛ አገልግሎት ላለማቋረጥ እየታገልን ነው እንጂ እስካሁን 3 የሚደርሱ ጤና ጣቢያዎች፣ ወደ 12 የሚደርሱ ጤና ኬላዎች አሁንም በየቀኑ በታጣቂ ኃይሎች ይዘረፋሉ።

° መጀመሪያ በስፋት #ፕላምፕሌት አልሚ ምግቦችን ሲወስዱ ነበር። እነርሱ ምግቦች ለሕፃናትና ለእናቶች ካልደረሱ ወደዛ መውሰድ አስፈላጊ አይደለም ብለን  ስናስቆማቸው ጤና ኤክስቴሽኖችን እናንተ ናችሁ የደበቃችሁት አምጡ አስልኩ አይነት ነገር ማስፈራሪያ፣ ዛቻ፣ ድብደባዎች እያደረሱ ነው።

° ጋዝጊቭላና ድሀና ወረዳዎች አዚላ የሚባል ክላስተር አለ፣ በዚያ ስር ያሉ ጤና ኬላዎች፣ በጋዝጊብላ ወረዳ ደግሞ አዱፍቃ፣ አርካ ጤና ጣቢያዎች ስር ባሉ ጤና ኬላዎች ላይ ነው እንግልት እየተደረገ ያለው።

° የጤና አገልግሎቱ እየተቆራረጠ ነው። በቋሚነት እየተሰጠ አይደለም። ከአንድ እስከ ሶስት ቀናት በተከታታይ ይሰጣል። ከሆነ ጊዜ በኋላ ይመጡና እደገና ያቋርጡታል። ኮሚዩኒቲ ሰርቪስ የምንለው በጤና ኬላ ደረጃ የሚሰጠው ኦልሞስት እየቆመ ነው። 

ለመፍትሄው ከማን ምን ይጠበቃል?

☑️ የአጋር ድርጅት ድጋፍ የተቀዛቀዘ ነው። ድጋፍ ማድረግ ቢችሉ የሰዎችን ሕይወት ይታደጋሉ። ከጸጥታው  ጋር ተያይዞ ሊሆን ይችላል ኤኒይወይስ ስለ ረሀብ ደግሞም ስለ ህፃናት፣ ነፍሰጡር አጥቢ እናቶች ረሃብ ነው እያወራን ያለነው። 

☑️ አይደለም እንደዚህ ድርቅ ተከስቶ አፍጦ መጥቶ ኖርማል በመደበኛ ሁኔታ እንኳ እንደዚህ ለይተናቸው የምግብ እጥረት እንዳለባቸው ሲታወቅ ወዲያውኑ ወደ ፕሮግራም ገብተው መታከም ያለባቸው ህፃናት ለተከታታይ 2 ወራት ምንም አልተደረገላቸውም።

ዘገባውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia
😭52475😢46😡26🕊24🙏6👏5🥰3
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዋግኽምራ " ድርቁ በጣም እየባሰ ነው። መታከም ያለባቸው ህፃናት ለተከታታይ 2 ወራት ምንም አልተደረገላቸውም" - ዋግኽምራ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ በዞኑ ስላሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ? - ድርቁ በጣም #እየባሰ ነው። ባለፈው ጥናት ካጠናን በኋላ ሊደረግ የሚገባው ግን ያልተደረገ በጣም በስፋት…
#አማራ #ዋግኽምራ

በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰሃላ ሰየምትን ጨምሮ ድርቅ በተከሰተባቸው ሌሎችም ወረዳዎች ላይ እንስሳት በመኖ እጥረት #እየሞቱ ፣ አካባቢያቸውን ለቀው #እየተፈናቀሉ መሆኑን አስተዳደሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

የአስተዳደሩ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፣ ከ10,000 በላይ የተለያዬ እንስሳት በውሃና በመኖ እጥረት ሞተዋል።

በአበርገሌ፣ በሮቢና፣ በበለቃ በላይኛው ተከዜ ተፋሰስ በተለይ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ነጻ ያልወጡ፣ መንግሥት የማይቆጣጠራቸው ቀበሌዎች ላይ ሰፋ ያለ ችግር እንዳለ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ በድርቁ ቀጥተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉ እንስሳትን በሚመለከት ኃላፊው ፤ በሦስቱም ወረዳዎች ፦
* ሰሃላ ሰየምት፣
* ዝቋላ፣
* አበርገሌ በጣም የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብለው የለተለዩ ወደ 791,000 አካባቢ እንደሆኑ አስረድተዋል።

ከ791,000ዎቹ ውስጥ በተለይ ሰሃላ ሰየምት ወረዳ ላይ ያሉት ክርቲካሊ የዕለትም አቅርቦት ስላጡ 171,000 ወደ ደሃና ወረዳ ተፈናቅለው እንዲሄዱና ተጠግተው ለጊዜው እንዲቆዩ መደረጉን ተናግረዋል።

" ይህን ይህል ተፈናቅሎ ከሄደ ቀሪው 620,000 ደግሞ ከዚያው #እየተላወሰ ነው ያለው " ሲሉ አክለዋል።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-24

@tikvahethiopia
😭451😢4437🕊12😱7🥰6🙏5😡4