TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#RUSSIA ሩስያ ባለፈው ሳምንት ማንኛውም የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት እንቀስቃሴን #ሕገወጥ በማለት ፈርጃለች። የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ዓለም አቀፍ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነት የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዷል። ይህ እገዳ ይፋ ከተደረገ በኃላ ባለፈው አርብ ምሽት የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦ ° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)…
#ሩስያ

ከዚህ ቀደም ማንኛውም አይነት #የግብረሰዶም እንቀስቃሴን #ሕገወጥ እና #ጽንፈኛ በማለት ፈርጃ የነበረችው ሩስያ አሁን ደግሞ የግብረሰዶም እንቅስቃሴን #የአክራሪነት እና #የሽብር ድርጊት ዝርዝር ውስጥ አካታዋለች።

በዚህም ማንኛውም ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም እንቅስቃሴ በሩስያ በአሸባሪነት እና በአክራሪነት ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።

ውሳኔው የተደረሰው የሩስያ የፍትህ ሚኒስቴር የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ የግብረሰዶም ተከራካሪዎች #አክራሪ እና #አሸባሪ ተብለው እንዲጠሩ በህዳር ወር ላይ የሩሲያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከወሰነ በኋላ ነው።

በቅርቡ የሩስያ ፍርድ ቤት በ " አክራሪ ድርጅት " ውስጥ ሚና አላቸው በሚል በመወንጀል ሁለት የመጠጥ ቤት / ባር ሰራተኞችን በእስር ቤት እንዲቆዩ እና እዛው እስር ቤት ሆነው ፍርዳቸውን እንዲከታተሉ ወሷል።

የሩሲያ ጠቅላይ ፍ/ቤት ከዚህ በፊት ዓለም አቀፍ የግብረሰዶም የአደባባይ እንቅስቃሴን " #ጽንፈኛ " በማለት ማንኛውንም እንቅስቃሴዎችን አግዶ ነበር።

በወቅቱም የሩስያ ፀጥታ ኃይሎች በሞስኮ ከተማ በሚገኙ ፦
° የተመሳሳይ ጾታ የምሽት ክበቦች (ክለቦች)
° የተመሳሳይ ፆታ ፓርቲዎችን ያዘጋጃሉ በተባሉ ባሮች
° የወንዶች ሳውና ቤቶች ላይ ዘመቻ አካሂደው ተጠርጣሪዎችን አስረው እንደነበር ይታወሳል።

በሩሲያ የተመሳሳይ ጾታ ጥምረት እውቅና #የለውም

በሩሲያ #ትዳር ማለት የወንድ እና የሴት ጥምረት ማለት ስለመሆኑ ትርጉም ለመስጠት የአገሪቱ ሕገ መንግሥት ከ3 ዓመታት በፊት ተቀይሮ ነበር።

@tikvahethmagazine @tikvahethiopia
👏12.5K1.67K🙏403🥰202🕊106😡55😱32🤔18😭18😢12
" ባለቤቴንና አምስት ልጆቼን ነው ያጣሁት " - ተጎጂ አባት

➡️ " ጥቃቱን ያደረሱት ጽንፈኛ የሚባሉ በዚሁ በወሰን አከባቢ ሸምቀው ያሉ ታጣቂዎች ናቸው ! " - የአካባቢው ነዋሪ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳ ቆንዳላ ቀበሌ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት ቢያንስ 14 ሰዎች ተገደሉ።

ጥቃቱ ከትናንት በስቲያ ሃሙስ ሃምሌ 03 ቀን 2017 ዓ.ም. ምሽት ነው የተፈጸመው።

የታጠቁ አካላት በመደዳው አንድ መንደር ላይ አነጣጥረው የዘፈቀደ ጥቃት ማድረሳቸው ነው የተገለጸው፡፡

ብርሃኑ ሸምሰዲን የተባሉ ተጎጂ በጥቃቱ ሙሉ የቤተሰቦቻቸውን አባል አጥተዋል፡፡

ባለቤታቸውን እና አምስት ልጆቻቸውን ድንገት ከቤት በወጡበት አጋጣሚ አልቀው ማግኘታቸውን ተናግረዋል። አደጋው ዱብ እዳ እንደሆነባቸው በደከመና በሚቆራረጥ ድምፅ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ተናግረዋል።

" ምሽት አንድ ሰዓት ተኩል አከባቢ ነው ስድስት የቤተሰቤ አባላት በሙሉ የጨረሱብኝ፡፡ የሁለት ዓመት ጨቅላ ህጻንና ባለቤቴን ጨምሮ ሶስት ወንድ ልጆቼን እና ሁለት ሴት ልጆቼ አልቀውብኛል " ብለዋል።

" የአምስት ዓመት፣ የ11 እና 12 ዓመት እንዲሁም የ14 ዓመት እድሜ ልጆች ናቸው ያለቁብኝ፡፡ ገዳዮች ከኔ የተለየ ቂም የላቸውም፤
#ጽንፈኛ የሚባሉ በአከባቢያችን የደቡብ ክልል አዋሳኝ አከባቢ ሸምቀው ያሉ መሆናቸው ብቻ ነው የተነገረን " ሲሉ አክለዋል።

" በመንደራችን በመደደው በተወሰደብን ድንገተኛው ጥቃት እንደ እኔ ሙሉ ቤተሰቦቻቸው አልቆባቸው ባይጎዱም እንደ እኔ ሁሉ ዉዶቻቸውን ያጡ አራት ቤቶች ግድም ጎረቤቶቼም አሉ " ብለዋል።

ጥቃቱ ድንገተኛና ምንም በማያውቁ ንጹሃን ላይ ያነጣጠረ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ይህ ሁሉ አደጋ በመላው ቤተሰቦቻቸው ላይ የደረሰው እሳቸው ድንገት ለጉዳይ ወደ ጎረቤት ብቅ ባሉበት ሰዓት መሆኑን ገልጸዋል።

" ጥቃቱ የተፈጸመው ሁሉም በማታው ቤቱ ቁጭ ባለበት ሰዓት ነው፡፡ አንዳንዶቹ እራት እየበሉ ሌሎችም ቴሌቪዢን እየተመለከቱ ባሉበት ነው ድንገት ገብተውባቸው የጥይት እሩምታ በማዝነብ ህጻናት እና ሴት ሳይሉ ያገኙትን ሁሉ የገደሉዋቸው " ብለዋል።

" የተኩሱን ድምጽ ሰምቼ ከነበርኩበት ጎረቤት ቤት ልወጣ ስል በግድ አስቀመጡኝ፡፡ በኋላ ሮጬ ቤቴ ስደርስ ግን አንድም የተረፈልኝ የለም፤ ስድስት የቤተሰቤ አባላት በሙሉ አልቀው ጠበቁኝ " ሲሉ ሀዘናቸው መሪር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመበት ቦታ የምዕራብ ሸዋ ዞን ኖኖ ወረዳን ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ጋር በምታዋስን ቆንዳላ ቀበሌ ዳርጌ ከተማ ነው ያሉት የአይን እማኝየአከባቢው ነዋሪ፤ በተለይ ይህ ጥቃት የተፈጸመው በከተማዋ ዳር ላይ በሚገኙ መንደሮች ነው ብለዋል፡፡

ለደህንነታቸው ስባል ስማቸውን ሳይገልጹ አስተያየታቸውን ብቻ ያጋሩን እኚህ አስተያየት ሰጪ፤ " በሰዓቱ ሁላችንም በዚያችው ከተማ ውስጥ ነበርን፡፡ ጥቃቱ በደረሰበት በዚያ አከባቢ የከባባድ መሳሪያዎች ድምጽ ጨምር ስንሰማ ስለነበር ተኩሱ ሲቆም 2፡30  አከባቢ ወደ ቦታው ስናመራ ብዙ አስከሬን አገኘን " ብለዋል።

" የተጎዱትን ወደ ሆስፒታል ብንወስዳቸውም ሆስፒታልም ደርሰው ያለፉብን አሉ፡፡ አሁን ባጠቃላይ 14 ሰዎች ስሞቱ ሶስት ሰዎች በከባድ ሁኔታ ሆስፒታል እየታከሙ ይገኛሉ " ሲሉ ገልጸዋል።

" ሰላማዊ ሰዎች ላይ ነው በር እየከፈቱ እየገቡ የአንድ ዓመት ህጻን ጨምሮ አዛውንትና ሴት ሳይሉ ያገኙት ሁሉ ላይ ጥይት አርከፍክፈው የወጡት " ብለዋል፡፡
 
በወቅቱ የከተማዋን ጸጥታ የሚያስጠብቁ የፀጥታ አካላት በቦታው እንደሌሉ የገለጹት አስተያየት ሰጪው ነዋሪ ጥቃቱን ያደረሱ ታጣቂዎች ወደ 40 የሚጠጉ ናቸውም ብለዋል፡፡

" የፀጥታ መዋቅር በሰዓቱ ወደ ሌላ ስፍራ ተንቀሳቅሶ ነበር ነው የሚባለው፡፡ ይህን ክፍተት በመጠቀም ይመስላል ታጣቂዎቹ ዘልቀው ገብተው እንዲህ ያለ ዘግናኝ ጥቃት ያደረሱት፡፡ ጥቃቱን ያደረሱት
ጽንፈኛ የሚባሉ በዚሁ በወሰን አከባቢ ሸምቀው ያሉ ሲሆን ከተማ ውስጥ ገብተው ጥቃቱን ያደረሱም በቁጥር ከ35 እስከ 40 እንደሚሆኑ ከጥቃቱ የተረፉ ነግረውናል፡፡ መሰል ድርጊቶች በዚህ ቀበሌና አከባቢው ተደጋግሞ የተፈጸመ ሲሆን አሁንም ልቆም አልቻለም " ሲሉ የችግሩን አሳሳቢነት ገልጸዋል፡፡

አከባቢው አሁን ተረጋግቶ እንደሆነ የተጠየቁት አስተያየት ሰጪው ነዋሪ፤ " ለአሁኑማ ምን መረጋጋት አለ፤ ሰው የሞተበትን ቀብሮ ሀዘን ተቀምጠዋል፡፡ የህግ አካላትም መጥተው ' ድርጊቱን የፈጸመውን አካል እያደንን ነው ' ብለዋል " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል።

መረጃው የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
😭973677😡79💔46🕊22😢11🙏11🤔7👏6🥰3😱2