TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#JawarMohammed

" አልፀፀትም " / " HIN GAABBU "

በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የገዘፈ ስም ካላቸው ፖለቲከኞች አንዱ የሆኑት የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ መፅሀፍ ይዘው እየመጡ እንደሆነ ገለጹ።

የኢህአዴግን ስርዓት በሰላማዊ መንገድ በመታገል ስርዓቱ ሳይወድ በግዱ እንዲቀየር በማድረጉ ረገድ ግንባር ቀደሙን ድርሻ እንደሚይዙ የሚነገርላቸው አቶ ጃዋር መሀመድ ከዚህ ቀደም ሰፋ ያለ መፅሀፍ እየጻፉ እንደነበር መግለፃቸው ይታወሳል።

በመጨረሻም መፅሀፋቸው መጠናቀቁን እና ለአንባቢያ ሊደርስ መሆኑን አሳውቀዋል።

በቀጣይ ሳምንት ኬንያ፣ ናይሮቢ ውስጥ በሚዘጋጅ ዝግጅት መፅሀፉ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።

" አልፀፀትም " / " HIN GAABBU " በሚል ርዕስ የተዘጋጀው መፅሀፋቸው በርካታ እና ከዚህ ቀደም ይፋ ያላደረጓቸው ጉዳዮች የተዳሰሰበት እንደሆነ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመረዳት ችሏል።

አቶ ጃዋር መሀመድ ፦
° በኢትዮጵያ ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል የገዘፈ ስም ያላቸው ፤
° አሜሪካ ሆነው የኢህአዴግን ስርዓት በሰላማዊ ትግል በመጣሉ በኩል ቁልፍ ሚና የነበራቸው ፤
° ' ለውጥ መጣ ' ተብሎ ወደ ሀገር ከገቡ በኃላ የሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ከቀብር ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ሁኔታ ታስረው ለበርካታ ወራት በእስር ቆየተው መፈታታቸው ይታወሳል።

ፖለቲከኛው ከእስር ቤት ቆይታ በኃላ ቀድሞ የሚታወቁባቸውን ኃይለኛ ንግግሮችን እና ፅሁፎችን በመተው ዝምታን መርጠው ብዙ ጊዜያቸውን በመፅሀፍ ዝግጅት ላይ እንዲሁም በሀገሪቱ ያሉ ግጭቶች እንዲቆሙ የድርሻቸውን የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይነገራል።

ከእስር በኃላ ኢትዮጵያ እንዲሁም ኬንያ ናይሮቢ እየተመላለሱ የሚኖሩ ሲሆን አብዛኛውን ጊዜያቸውን ግን ናይሮቢ ናቸው።

በኬንያ ፣ ናይሮቢ ገቢ የሚያገኙባቸውን ስራዎች ከመስራት ባለፈ እንደ ኢትዮጵያ ብዙ ሰዎች ሊያገኟቸው / ሊጠይቋቸው ስለማይመጡ በጥሞና ለማሰብ፣ ለማንበብ እና መፅሀፋቸውን ለማዘጋጀት ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው ለመረዳት ተችሏል።

" አልፀፀትም / HIN GAABBU " የተሰኘው መፅሀፋቸው ቀጣይ ሳምንት ሀሙስ ናይሮቢ ውስጥ ላውንች ይደረጋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
61.44K😡400👏148🤔50🕊50🙏38😭37🥰30😱12😢5
TIKVAH-ETHIOPIA
#JawarMohammed " አልፀፀትም " / " HIN GAABBU " በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የገዘፈ ስም ካላቸው ፖለቲከኞች አንዱ የሆኑት የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ መፅሀፍ ይዘው እየመጡ እንደሆነ ገለጹ። የኢህአዴግን ስርዓት በሰላማዊ መንገድ በመታገል ስርዓቱ ሳይወድ በግዱ እንዲቀየር በማድረጉ ረገድ ግንባር ቀደሙን ድርሻ እንደሚይዙ የሚነገርላቸው አቶ ጃዋር መሀመድ ከዚህ ቀደም…
#JawarMohammed

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አመራሩ አቶ ጃዋር መሐመድ ' አልጸጸትም / HIN GAABBU ' መጽሐፍ ዛሬ ሳይመረቅ ቀረ።

መጽሐፉ ዛሬ በኬንያ፣ ናይሮቢ ሊመረቅ ቀጠሮ ተይዞለት ነበር።

አቶ ጃዋር መሐመድ ናይሮቢ ሊካሄድ የነበረው የመፅሐፍ ምርቃት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን አረጋግጠዋል።

ጃዋር " በተሳታፊዎች ብዛት እና በደህንነት ስጋት ምክንያት የምረቃ አዳራሹ አስተዳደር ላልተወሰነ ጊዜ ማስተላለፉን " ገልጸዋል።

" በቅርብ ቀን ተቀያሪ ቦታ እናሳውቃለን " ብለዋል።

ቢቢሲ አማርኛው አገልግሎት ደግሞ ምንጮቼ  እንደገለጹልኝ የመጽሐፍ ምርቃቱ ሳይካሄድ የቀረው ከተለያዩ አካላት ማስፈራሪያዎች እና ዛቻዎች በመድረሳቸው ነው ብሏል።

መጽሐፉ የሚመረቅበት ናይሮቢ የሚገኘው የኬንያታ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል መሆኑ ከታወቀ በኋላ የተለያዩ ማስፈራሪያዎች ደርሰዋል ተብሏል።

ዛቻው እና ማስፈራሪያው የጸጥታ ስጋት እንዳለ በመጥቀስ ማዕከሉን ለሚያስተዳደሩት አካላት በመድረሱ ምርቃቱ መሰረዙን እኚሁ ምንጮች ገልጸዋል።

እኚህ አካላት እነማን እንደሆኑ ግን ዘገባው በግልጽ አላሰፈረም።

በቅርቡ አቶ ጃዋር መሐመድ ከቢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ መጽሃፋቸውን በኢትዮጵያ ለማስመረቅ እንደሚፈልጉ ነገር ግን "... በአገሪቱ መጽሐፍ ማስመረቅ ይቅርና ለመተንፈስ ከባድ ነው " የሚል ነገር ተናግረዋል።

" ኢትዮጵያ ለማስመረቅ ፍላጎት ነበረኝ " ያሉ ሲሆን " ሆኖም ግን ገዢዎቹ ደስተኛ አልነበሩም። አሁን አገራችን ካለችበት ሁኔታ አንጻር ለመጽሐፍ ብዬ አምቧጓሮ ውስጥ ለመግባት አልፈለግኩም " በማለት በጎረቤት አገር መዲና መጽሐፉን ለማስመረቅ የወሰኑበትን ምክንያት አስረድተዋል።

አቶ ጃዋር መሐመድ የፖለቲካ ጉዞ እና የሕይወት ታሪካቸውን በሚመለከት ' አልጸጸትም / HIN GAABBU ' በሚል ርዕስ በአፋን ኦሮሞ እና በአማርኛ መጽሐፍ ጽፈው አሳትመዋል።

@tikvahethiopia
785😡158🕊61🤔57🙏56😭25👏24😱22🥰15😢6