TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ #ባንኮች

የአገሪቱ ባንኮች ከአሠራር ጋር በተያያዙ ክፍተቶች በተለያዩ ሥልቶች ለሚፈጸሙ የማጭበርበር ድርጊቶች በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸውን ፣ ይህ ሁኔታም በቀጣይ የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ ውስጥ የበለጠ እንደሚጨምር የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ጤናማነትን በመገምገም አንድ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ሪፖርቱ ምን ይላል ?

➡️ የአገሪቱ ባንኮች በበይነ መረብ ማጭበርበርያ ሥልቶች፣ ከባንኮች የውስጥ ሠራተኞችና ከሦስተኛ ወገን በሚደርሱባቸው የምዝበራ ድርጊቶች በከፍተኛ ደረጃ እየተጋለጡ ናቸው።

➡️ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ ማለትም እስከ ሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በሐሰተኛ ሰነዶችና በሌሎች የማጭበርበር ድርጊቶች ባንኮች 1 ቢሊዮን ብር አጥተዋል። የተመዘበሩት የገንዘብ መጠንም ከቀዳሚው ዓመት በእጥፍ ጨምሯል።

➡️ የባንክ ማጭበርበሮች በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ወደ 1 ቢሊዮን ብር ሲደርሱ፣ ከአምናው በእጥፍ አድጓል። እነዚህ ጉዳዮች የተከሰቱት በዋናነት ፦
° ሐሰተኛ የገንዘብ ኖቶችንና ቼኮችን በመጠቀም ገንዘብ በማጭበርበር፣
° ያልተፈቀደ የባንክ ዋስትና በማቅረብ፣
° የተሰረቁ የኤቲኤም ካርዶችን በመጠቀም ገንዘብ በማውጣት ድርጊት
° በሐሰተኛ የስልክ ጥሪዎችና አጭር የጽሑፍ መልዕክቶችን በመጠቀም ነው። በተጠቀሱት የማጭበርበሪያ ሥልቶችም 20 ባንኮች ጉዳት ደርሶባቸዋል። በሰኔ ወር 2015 መጨረሻ ላይ 3 ባንኮች 200 ሚሊዮን ብር ተዘርፈዋል።

➡️ ባንኮች አዳዲስ ምርቶችንና አገልግሎቶችን ሲተዋወቁ በአሠራር ክፍተቶች ሳቢያ በከፍተኛ ደረጃ ለአደጋ እየተጋለጡ ናቸው።

➡️ ባንኮች ከአሠራር ጋር የተያያዙ አደጋዎችን ለመከላከልና የመጭበርበር ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ፣ ውጤታማ የቁጥጥር ሥልቶችንና አሠራርችን በመተግበር ላይ ሊያተኩሩ ይገባል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የ #ሪፖርተርጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
😭12685👏42😱25🤔19😢10🕊7🥰6😡3🙏1