TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Amhara #Oromia

ከ5 ዓመታት በላይ በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች በሚስተዋለው የጸጥታ ችግር ሳቢያ ወደ አማራ ክልል በመሸሽ ተጠልለው የሚገኙና ገና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ተፈናቃዮችን ኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ቄየዎቻቸው የመመለስ ሥራ ለመስራት ሰሞኑን ባህር ዳር ከተማ ላይ ተደረገ በተባለ የጋራ ውይይት ስምምነት ላይ መደረሱን የሁለቱም ክልሎች የኮሚዩኒኬሽን ቢሮዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ሀይሉ አዱኛ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ "የታሰበው በጸጥታ ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ከክልላችን ተፈናቅለው አማራ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን መልሦ የማቋቋም ሥራ ነው" ብለዋል።

አክለውም፣ "በጸጥታ ምክንያት ከኦሮሚያ ወደ አማራ ክልል የተፈናቀሉ ሰዎችን ለመመለስ አብይ ኮሚቴው በሚቀጥለው ሳምንት ተገናኝቶ መሪ ዕቅዱን ያወጣል" ሲሉ አስረድተዋል።

የአማራ ክልል የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድወሰን አሰፋ በበኩላቸው፣ "ሁለታችን ተቀናጅተን ለመስራት የሚቀጥለው ሰኞ ቀጠሮ ይዘናል። በዛ መሰረት ታይም ቴብሉን እናስቀምጣለን  መቼ ይመለሱ? መቼ ወደዛ እናጓጉዝ? የሚለው በቅዳችን ነው የሚመለሰው" ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ለአብነትም በሰሜን ሸዋ ዞን #ደራ_ወረዳ ከአሥር በላይ ቀበሌዎች፣ በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ታጣቂ ቡድኑ በንጹሐን ላይ ግድያ እየፈጸመ መሆኑን ነዋሪዎች እንደገለጹ፣ ይህ በእንዲህ እንያለ ተፈናቃዮች ቢመለሱ ለደኅንነታቸው ምን ዋስትና ይኖራቸዋል ? የሚል ጥያቄ ቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርቧል።

አቶ ወንድወሰን ለዚሁ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ፣ " የጸጥታ ችግር እያለ እኛም እዲመለሱ አናደርግም። በኦሮሚያ ክልል በኩልም የጸጥታ ችግሩ አስተማማኝ ደረጃ ሳይዘልቅ ተመላሾቹ ለዳግም ችግር የሚጋለጡበትን  መገድ ሁለታችንም አንሰራም" ብለዋል።

አክለውም፣ " ሰሜን ሸዋ አካባቢ ያለው የጸጥታ ችግር ወጣ ገባ የሚል ነው እናተም እደምታውቁት አማራ ክልልም የጸጥታ ችግር አለ። ይህን በዘላቂ መፍትሔ ይሰጠዋል ብለን ነው የምናስበው፣። ሆሮ ጉድሩ ያለውም ቢሆን አሸባሪው ሸኔ  ወጣ ገባ እያለ ችግር ሊፈጥር ይችላል " ብለው፣ በቅድሚያ የጸጥታውን ችግር የምረጋግጥ ሥር እንደሚከናወን አስረድተዋል።

አቶ ሀይሉ አዱኛ በበኩላቸው፣ " የጸጥታው ችግር በተረጋገጠባቸው አካባቢዎች የማስፈሩም መልሶ የማቋቋሙም ሥራ ይሰራል። የጸጥታ ችግር ያልተረጋገጠበት አካባቢዎች ደግሞ እያረጋገጥን ነው መልሰን የምናቋቁመው፣ ዛሬ መልሰን ችግር እንዳይፈጠር ጥንቃቄ በተሞላበት አኳኋን ነው የሚሰራው " ሲሉ ተናግረዋል።

የሁለቱም ክልል ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ባለስልጣናት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት፣ ተፈናቃዮችን ወደነበሩበት ኦሮሚያ ክልል ከመመለስ በፊት ይህን ሥራ ለማስኬድ የተዋቀረው አብይ ኮሚቴ መረጃዎችን ያጠራል።

ያንብቡ - https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-10-27

@tikvahethiopia
😡408138😢35🕊31👏17🙏9😱7🥰6😭2