#ናይጄሪያ
ናይጄሪያ ውስጥ አንድ ባለሃብት ገንዘብ ለማደል በጠራበት ዝግጅት ላይ በተፈጠረ ግርግር አንዲት የ8 ዓመት ሕፃንን ጨምሮ 7 ሰዎች ተረጋግጠው እንደ #ሞቱ ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።
ትላንትና እሁድ አልሃጂ ያኩቡ የተባለ ባለሀብት በሰሜን ምሥራቅ የባውቺ ግዛት ነዋሪዎች ወደ ቢሮው ከመጡ ለእያንዳንዳቸው 5 ሺህ ናይራ (የናይጄሪያ ገንዘብ) ለመስጠት ቃል ይገባል።
5 ሺህ ናይራ ወደ ዶላር ሲመነዘር 3 ዶላር ከ70 ሳንቲም ሲሆን፣ ወደ ብር ሲቀየር 210 ነው።
የባለሀብቱን የገንዘብ እደላ ጥሪ ተከተሎ በርካታ ሰዎች ይወጣሉ በዚህ ወቅት በተፈጠረ ግርግር ዕድሜያቸው ከ8 እስከ 55 የሚሆን 7 ሰዎች መሞታቸውን ፖሊስ አረጋግጧል።
ነዋሪዎች ግን የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከተጠቀሰው ይበልጣል ብለዋል።
ብዙ ጊዜ እንዲህ ያለ እደላ/እርዳታ ላይ ወንዶች የእርዳታ ገንዘብ ሲቀበሉ መታየት ስለማይፈልጉ ሴቶችን እንደሚልኩ ተነግሯል።
የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በዕለቱ የተፈጠረውን ነገር ለማጣራት ምርመራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
ቢሮው አካባቢ የጥሬ ገንዘብ ልገሳ ያሰናዳው ባለሀብቱ አልሃጂ ያኩቡ ማይሻኑ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
የናይጄሪያ የምጣኔ ሀብት #መላሸቁን ተከትሎ በርካቶች እርዳታ ጠባቂ ሆነዋል። 5 ሺህ ናይራ አንድን ቤተሰብ ለአንድ ቀን መመገብ ይችላል።
ባለፈው ሳምንት በማዕከላዊ ናይጄሪያ የናሳራዋ ግዛት ዩኒቨርሲቲ ሩዝ ሲታደል ለመቀበል የወጡ የተወሰኑ #ተማሪዎች ተረጋግጠው #ሞተዋል።
ባለፈው ወር የናይጄሪያ ገቢዎች አገልግሎት ሩዝ በቅናሽ ዋጋ ሲሸጥ በተፈጠረ ግርግር የተወሰኑ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው አሳውቆ ነበር።
ናይጄሪያ ውስጥ ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት በርካቶች የሚቀበሉት ደመወዝ ከወር ወር ሊያደርሳቸው እንዳልቻለ ቢቢሲ አስነብቧል።
Via https://tttttt.me/thiqahEth
@tikvahethiopia

😭1.16K❤130😢66😱65😡40🕊32🤔23🙏16👏10🥰8
#ጥንቃቄ🚨
" በተጣሉ ተተኳሾች እና ፈንጂዎች 103 ሰዎች #ሞተዋል ፤ አካላቸው ጎድሏል " - የቆላ ተምቤን ወረዳ
በትግራይ ማእከላይ ዞን የቆላ ተምቤን ወረዳ በጦርነቱ ምክንያት በርካታ ተተካሾች እና ፍንጂዎች ይገኛሉ።
እጅግ አስከፊውና ደም አፋሳሹን ጦርነት ተከትሎ በአከባቢው የተቀበሩትና የተጣሉት ተተካሾችና ፈንጂዎች በበርካታ ሰዎችና እንስሳት ላይ የሞትና የአካል ጉዳት አደጋ በማድረስ ላይ እንደሆኑ ተነግሯል።
በወረዳው በተቀበሩትና በተጣሉት ተተኳሾችና ፈንጂዎች እስካሁን 103 ሰዎች #ሞተዋል ፤ አካላቸው ጎድሏል።
አሁን ላይ አደጋውን ለመቀነስ ነዊና ጉያ በተባሉ የቀበሌ አስተዳደሮች በባለሙያዎች የተደገፈ የማምከን ስራ መጀመሩን የወረዳው አስተዳደር አሳውዋል።
ህዝቡ በአከባቢው ከተለመደው የተለየ ብረት ሲያገኝ ከመንካት እና ከመቀጥቀጥ ተቆጥቦ ለጸጥታ አካላት እንዲያሳውቅ ማሳሰቢያ ተለልፏል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከቆላ ተምቤን ወረዳ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ነው ያገኘው።
#TikvahEthiopiaFamilyMekelle

😭674❤92😢38🕊38🙏32😱17👏13😡13🤔10🥰7