TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
አዲሱ ዓመት 2016 ፦ - ሀዘን ፣ የዜጎችን ሞት ፣ ሰቆቃ ፣ ረሃብ ፣ የእርስ በእርስ መገዳደልና መጠፋፋት የማንሰማበት፤ - ለተበደሉት ፣ ለተገፉት ዜጎች ሁሉ #ፍትሕ የሚገኝበት፤ - ምስኪን እናቶች፣ ህፃናት ፣ አረጋውያን ምንም በማያውቁት ፖለቲካ የማይሰቃዩበት ፤ ወጣቶችም ነፍሳቸውን የማይነጠቁበት፤ - ዘውትር ጭንቀት ለሆነብን የኑሮ ውድነት መፍትሄ የሚያገኝበት፤ - ዜጎች ወጥተው ለመግባት የማይሳቀቁበት፤…
#ኢትዮጵያ2016

ኢትዮጵያ ዛሬ አዲሱን 2016 ዓ/ም አንድ ብላ ጀምራለች።

ዓመቱ የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የአንድነት ፣ የፍትህ ፣ ከችግሮቻችን የምንላቀቅበት እንዲሆን የመላ የኢትዮጵያውያን ምኞት ነው።

አሁንም በኢትዮጵያ የሚወዱትን የተነጠቁ፣ በግፍ ከቄያቸው ተፈናቅለው ሜዳ ላይ ብርድ እና ፀሀይ የሚፈራረቅባቸው ፣ የነበራቸውን ንብረት እና ሃብት በጦርነት እና በግጭት አጥተው የሰው እጅ ጠባቂ የሆኑ ፣ በየወቅቱ በሚፈጠሩ ችግሮች ሰበብ በጅምላ ታስረው የሚገኙ፣ በኑሮ ውድነት ክፉኛ እየተሰቃዩ  ያሉ ወገኖች እጅግ በርካታ ናቸው።

አዲሱ ዓመት ፍትሕ እና ተጠያቂነት የሚሰፍንበት ፤ የተበደለ የሚካስበት ፤ የእርስ በእርስ መግባባት እውን የሚሆንበት ፤ የህዝብ ድምፅ የሚሰማበት ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከበደ ላለው ኑሮ መረጋጋት የሚፈጠርበት እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል።

ይህን አዲስ ዓመት ያለፉ ችግሮቻችን ሁሉ የሚታረሙበት ፣ ለጥፋት የዳረጉን ጥያቄዎች መልስ የሚያገኙበት፣ ለችግሮቻችን ሁሉ ተነጋግረን መፍትሄ የምናበጅበት፣ የተበደሉትን የምናፅናናበት፣ እንደ አንዲት የኢትዮጵያ ልጆች እርስ በእርስ ከጥላቻ ርቀን ለእድገታችን የምንሰራበት እንዲሆን እንደመልካም አጋጣሚ መጠቀም ይገባል።

ሁሌም አዲስ ዓመት በመጣ ቁጥር የሚነገር ምኞት እና የተስፋ ቃላት መሬት ላይ ካልዋለ ትርጉም አልባ ነውና ሁሉም ለሚናገረውና ለሚገባው ቃል መታመንና መፅናት አለበት።

@tikvahethiopia
👍778116🕊56👎31🙏20🥰4😢4😱1