TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሐረሪ

" የሽንኩርት ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ወስደናል " - የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ

የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ ፤ " የሽንኩርት ዋጋን ያለቅጥ አንረዋል " ባላቸው የሐረር ከተማ ነጋዴዎች ላይ የእስር ዕርምጃ መውሰዱን አስታውቋል።

በዳቦ ነጋዴዎችም ላይ ተመሳሳይ ዕርምጃ እወስዳለሁ ሲል አስጠንቅቋል።

የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ " የሽንኩርት ዋጋን ያላግባብ ያስወድዳሉ " ያላቸውን 3 ዋና ዋና ነጋዴዎችን ጨምሮ 17 የሽንኩርት አከፋፋዮችን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ ማድረጉን ገልጿል።

በሽንኩርት ነጋዴዎቹ ላይ ዕርምጃ ከመወሰዱ በፊት ቀደም ብሎ የማወያየት ሥራ መከናወኑን አመልክቷል።

የክልሉ ንግድ ልማት ኤጀንሲ ኃላፊ አቶ ሸሪፍ ሙሜ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ፦ " ባቢሌ አካባቢ የተፈጠረውን የአንድ ቀን ግጭትና መንገድ መዘጋት ተጠቅመው በሽንኩርት ላይ የተጋነነ ዋጋ ጨመሩ፡፡

ነጋዴዎቹን ቢሮ ድረስ ጠርተን ከማወያየት ባለፈ ቦታው ድረስ ባለሙያ በመላክ ሁኔታውን ገምግመናል፡፡

በጉዳዩ ላይ በመተማመን ዋጋውን ለማስተካከል ቃል ገብተው ቢሄዱም፣ ዋጋውን ባለማስተካከላቸው ወደ ዕርምጃ ተገብቷል። " ብለዋል።

ዕርምጃ የተወሰደባቸው የሽንኩርት ነጋዴዎቹ በሐረር ከተማ ብቻ ሳይሆን፣ በዙሪያው ባሉ አካባቢዎችም የማከፋፈል ሥራ የሚሠሩ ዋና ዋና ነጋዴዎች መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

ከ110 ብር እስከ 150 ብር አሻቅቦ የነበረው የአንድ ኪሎ የሽንኩርት ዋጋ ከዕርምጃው በኋላ መስተካከሉን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ፤ የሐረሪ ክልል ንግድ ልማት ኤጀንሲ ፤ ዳቦ ቤቶችን እና ነጋዴዎችን በቀጣይ ሳምንት በቢሮው ሰብስቦ እንደሚያነጋገር አሳውቋል።

የዳቦ ግራምና ዋጋ የሚያጭበረብሩ እንዲያስተካክሉ የአንድ ሳምንት ወይም የአሥር ቀን ገደብ ይሰጣል ብሏል።

ማስተካከያ ባላደረጉ ላይ ግን ልክ እንደ ሽንኩርት ነጋዴዎቹ ሁሉ ዕርምጃ ይወሰዳል ሲል ማስጠንቀቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

#ሽንኩርት ፦ የሽንኩርት ዋጋ በመዲናዋ ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች ዋጋው አልቀመስ ካለ ሰንበትበት ብሏል። በርካቶች በዋጋው ንረት ሸምቶ ለመግባት ማቸገራቸውን ይገልጻሉ። እርሶስ በጉዳዩ ላይ ምን ይላሉ ? በዚህ ይነጋገሩ @BirlikEthiopia

@tikvahethiopia
1.69K🙏435😡110😢98🕊63🥰37😱32