TIKVAH-ETHIOPIA
የዘንድሮው የኣሸንዳ ፣ ማርያ ዓይኒ ዋሪ በዓል እንዴት እየተከበረ ነው ? የኣሸንዳ ፣ ማርያ ዓይኒ ዋሪ በዓል ካለፉት ዓመታት እጅግ በተሻለ ድምቀት በትግራይ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ በዋነኝነት ትግራይ ውስጥ እጅግ በደመቀ ሁኔታ በመከበር ላይ ነው። ከእሁድ ነሃሴ 13/2015 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መከበር የጀመረው በዓሉ ፤ ነሃሴ 13 ና 14 / 2015 ዓ.ም በዓዲግራት…
#ኣሸንዳ
የዘንድሮው የኣሸንዳ በዓል ወደ አለፍነው ጦርነት ያስገቡን ስህተቶች ላለመደግም ቃል የምንገባበት ነው ሲሉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።
" ባለፉት ሁለት ሶስት የጦርነት አመታት በትግራይ ሴቶች የደረሰው ግፍ አሰቃቂ ነው። " ያሉት አቶ ጌታቸው " የትግራይ ሴቶች ሰላምና ስቃይ የትግራይ ህዝብ ሰላምና ስቃይ ነው። " ብለዋል።
" ከሶስት አመታት በፊት የአሸንዳ በዓል ከተጫወቱት ቆነጃጂት በጦርነት ምክንያት አካላቸው የጎደሉ የተሰው አሉ " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ይህንን እንዳይደገም በሚደረገው ትግል የሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ ነው። " ሲሉ አስገንዝበዋል።
ሴቶች ተውበው የአሸንዳ በዓል ሲያከብሩ ኤችአይቪ ኤድስ የመሰሉ ተላላፊ በሽታዎች መዘንጋት እንደሌለባቸው አሳስበዋል።
" በዓሉ ተፋናቃይ ህዝባችን ወደ ቀድመው ቄየው የሚመለስበት ፣ ስቃይ ውስጥ የሚገኘው ህዝባችን ነፃ እንዲሚወጣ ገሃድ የሚሆንበት እንደሚሆን እንተማመናለን " ብለዋል።
@tikvahethiopia

👍730👎310❤66🕊37🥰12😢11👏8😱7🙏3
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሃሳብ ልዩነቱ ወደ ግጭት አያመራም " - አቶ ጌታቸው ረዳ ዓመታዊው የ2016 ዓ/ም የአሸንዳ በዓል ዛሬ ነሃሴ 16/2016 ዓ/ም በመላ ትግራይ መከበር ጀምሯል። በዓሉ እስከ ነሃሴ 24/2016 ዓ.ም አንደሚቀጥል የወጣው መርሃ ግብር ያመለክታል። በሌላ በኩል ፕሬዜዳንት ጌታቸው በ2 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር የተገነባ የ10.2 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ሲመርቁ ፤ የአሸንዳ አደባባይ ግንባታ መሰረተ…
#ኣሸንዳ
ከሰሞኑን በፖለቲካ ትኩሳት ውስጥ የከረመችው ትግራይ በደማቅ ሁኔታ የዘንድሮውን የኣሸንዳ በዓል እያከበረች ነው።
በዓሉን ለማክበር በርካታ እንግዶች ትግራይ ይገኛሉ።
በዓሉ እስከ ነሃሴ 24 ቀን 2016 ዓ/ም በተለያዩ ስነስርዓቶች እየተከበረ ይቀጥላል።
በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የሚከበረው የኣሸንዳ በዓል ፍቅር፣ ይቅር ባይነትና መልካም ተግባቦት በተግባር የሚንጸባረቅበት በዓል ሲሆን በዓሉ በልጃገረዶች ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበረል።
ልጃገረዶች አደባባይ ወጥተው ይህን በዓልን በድምቀት ያከብራሉ።
የበዓሉ ይዘት በዋናነት ህብረተሰቡ ውስጥ ያሉ መልካም ተግባቦቶች፣ ፍቅርንና ይቅር ባይነት ላይ ያነጣጠረ ነው።
የሌሎች ሃሳቦች፣ ጭፈራዎች እና ትእይንቶች እንዲታዩ የሚጋብዝ በዓል ከመሆኑም ባለፈ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት አይንፀባረቅበትም።
ፎቶ፦ ትግራይ ቲቪ (ኖርዘርን ስታር ሆቴል፣ መቐለ ነሐሴ 17)
#Ashenda #Tigray

❤495🕊49😡28🥰23🤔13🙏12😢11😱4😭1