#MekelleUniversity
የመቐለ ዩኒቨርስቲ በ29ኛ ዙር ከ2000 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ። ከተመራቂ ተማሪዎች 40 በመቶ ሴቶች ናቸው።
ዩኒቨርስቲው ከተማሪዎች ምረቃ ጎን ለጎን 29ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉም አክብረዋል።
በምረቓው ስነ-ሰርአት የዩኒቨርስቲው ፕረዚደንት ተወካይ ዶ/ር ዓብደልቃድር ከድር ንግግር አድርገው ነበር።
ባለፉት 3 አመታት በትግራይ በተካሄደው ጦርነት የደረሰው ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት እጅግ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አስታውሰዋል።
ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በተገኘው አንፃራዊ እርጋታ ዪኒቨስቲው ተስተጓጉሎ የነበረውን የመማር ማስተማር ስራ ፈጥኖ መጀመሩን ገልጸዋል።
የ17 ወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው የነገ ተስፋ አንግበው ወደ ስራ በመመለስ ተማሪዎችን ለዛሬ ምረቃ ላበቁ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት ምስጋና አቅርበዋል።
ዩኒቨርስቲው የድህረ ጦርነት እቅድ በማዘጋጀት ፤ ከፌደራልና በአገሪቱ ክልሎች እንዲሁም በውጭ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲ በመነጋገርና በመፃፃፍ ያለፉት 3 የጦርነት አመታት የሚያካክስ ስራ ለመስራት በከፍተኛ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሆነ ገልጸዋል።
ዩቨርሲቲው በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን በመረዳት የፌደራል መንግስት የመደበለት አነስተኛ በጀትና የሰራተኞች ውዙፍ ደመወዝ በአፋጣኝ በመመለስ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ ስራውና ተልእኮው እንዲመለስ እንዲያደርግ አደራ ብለዋል።
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የማህበራዊ ዘርፍ ክላስተር ሰክሬተሰሪያት ሃላፊና የመቐለ የኒቨርስቲ ቦርድ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በበኩላቸው ፤ መቐለ ዩንቨርስቲ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰበትን ጉዳት ተቋቆቁሞና ወደ ስራ ተመልሶ በአጭር ጊዜ ይህን የመሰለ ድንቅ የምረቃ ስነ-ሰርአት ማዘጋጀቱ ነገ ለመድረስ ያቀደውን እንደሚያሳካ እንደ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል።
ይህንን የሆነው ለሰላም በተከፈለው እጅግ ወድ ዋጋ በመሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች ሆኑ ሌላው የማህበረሰብ ክፍል የተጀመረው ሰላም ስር እንዲሰድ በተሰማሩበት ሁሉ ሰላምና ልማት መስበክ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ዩኒቨርስቲው በ29 አመታት ጉዞው የዛሬ ጨምሮ ከ100 ሺህ በላይ ተማሪዎች ማስመረቁ ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያስረዳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
@tikvahethiopia

❤500👏82🕊36🙏23🥰19😢13😡13😱10😭6