TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba

የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አመራሮች በአዲስ አበባ የፀጥታ ሁኔታ ላይ ውይይት ማካሄዳቸው ተሰምቷል።

ውይይት ሲካሄድ የነበረው በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ሲሆን ሰዓታትን የወሰደ ሰፊ ውይይት መካሄዱ ተጠቁሟል።

ከፍተኛ አመራሮቹ ከውይይቱ በኃላ ባወጡት መግለጫ ሰሞኑን በአዲስ አበባ በተካሄደ የተቀናጀ ኦፕሬሽን ፦
- በእገታ ወንጀል፣
- በሕገ-ወጥ የጦር መሣሪያ፣
- በተደራጀ ከባድ የዝርፊያ ወንጀል
- ሞተር ሳይክል፣ ባጃጅ፣ የሜትር ታክሲዎችን ተጠቅመው #የሰው_ግድያ፣ የሞባይል ንጥቂያ እና ሌሎች ወንጀሎችን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ፦
- በርካታ የሺሻ ማስጨሻ፣
- #የጭፈራ_ቤቶች እንዲሁም ሕገ-ወጥ የንግድ ሱቆች ላይ እርምጃ ተወስዶ እንዲዘጉ መደረጉን አስረድተዋል።

የፌዴራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ የስፖርት ውርርድ ቤቶችን " የቁማር ቤቶች (betting) " ሲሉ የጠሯቸው ሲሆን በእነዚህም ላይ እርምጃ ተወስዶ እንዲዘጉ መደረጉን ገልጸዋል።

እነዚህ ወንጀሎች ለኅብረተሰቡ የፀጥታ ሥጋት በማይሆኑበት ደረጃ ላይ ለማድረስ ተከታታይ ኦፕሬሽን እንደሚቀጥል አሳውቀዋል።

በየጊዜው ውጤቱ እየተገመገመ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግም ገልጸዋል።

* የሜትር ታክሲ፣
* የሞተር ሳይክል
* የባጃጅ አጠቃቀም ሥርዓት እንዲይዝ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ይሰራልም ያሉ ሲሆን በወንጀል ተሳትፈው ከተገኙ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወሰድ አስጠንቅቀዋል።

በቀጣይ ለሚካሄድ ኦፕሬሽን የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ለፖሊስ መረጃ በመስጠት ድጋፍ እንዲያደርጉ ባወጡት መግለጫ ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
👏1.21K😡274198🙏86🕊41😢25😭16🥰15😱15
#ኩሽ #ሴራሊዮን

የሴራሊዮን መንግሥት በአገሪቷ በተንሰራፋው ‘ #ኩሽ / Kush ’ እየተባለ በሚጠራው የአደንዛዥ እፅ ምክንያት ብሔራዊ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አወጀ።

' ኩሽ ' የተለያዩ ሱስ የሚያስይዙ ግብዓቶችን በመደባለቅ የሚሰራ አደገኛ እፅ ሲሆን ለዓመታት በአገሪቷ ተንሰራፍቶ ይገኛል።

በአደንዛዥ እጹ ውስጥ ከሚጨመሩ ግብዓቶች መካከል አንዱ የተፈጨ #የሰው_አጥንት ነው።

በዚህም ምክንያት #ከመቃብር ውስጥ አፅም ለማውጣት የሚቆፍሩ #ሱሰኞችን ለማስቆም የጸጥታ አካላት በመካነ መቃብር ሥፍራዎች የሚያደርጉትን ጥበቃዎች አጠክረው ቆይተዋል።

የሴራሊዮን ፕሬዚደንት የሆኑት ጁሊየን ማዳ ባዮ አስተዳደራቸው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲያውጅ ያስገደደውን ይህንን እፅ / ኩሽ “ የሞት ወጥመድ ” ሲሉ የገለጹት ሲሆን በአገሪቷ ላይም የህልውና ቀውስና ስጋት ፈጥሯል ብለዋል።

ፕሬዚደንት ባዮ ፤ በእፁ ምክንያት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥርም እንዳሻቀበ ተናግረዋል።

በመሆኑም በ ' ኩሽ ' እፅ ምክንያት የሚደርሰውን ቀውስ ለመከላከል በሀገሪቱ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል ፤ ብሔራዊ ግብረ ኃይል እንዲቋቋምም መደረጉን ቢቢሲ አስነብቧል።

ፎቶ/ቪድዮ ፦ ቻናል 4 እና አፍሪካ ኒውስ (ፋይል)

@tikvahethiopia
😭1.38K😱431188🤔131😢55🙏53👏47😡36🥰34🕊28