TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሸዋሮቢት

በሸዋሮቢት የተጣለው የሰዓት ገደብ ዛሬ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።

ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ በተጣለው ገደብ መሰረት ከምሽቱ 12 ሰዓት አንስቶ ማንኛውም ሰውም ይሁን ተሽከርካሪ ከተማይቱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ ማድረግ አይችልም።

በተጨማሪ ፤ አገልግሎት ሰጪዎች የምሽት መዝናኛ ቤቶችን ጨምሮ ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት አይችሉም።

በሌላ በኩል ፥ ትላንት " ባልታወቁ ገዳዮች " የተገደለቱ የከተማው የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ተፈፅሟል።

ቅብራቸው የተፈፀመው በዛው ሸዋሮቢት በሚገኘው እንሰርቱ የሙስሊም መካነመቃብር ነው።

አቶ አብዱ የሁለት ወንድ እና የአንድ ሴት ልጆች አባት እንደነበሩ ተገልጿል።

ፎቶ ፦ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር

@tikvahethiopia
👍419👎125😢10647😱9🥰5🙏5