TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ነእፓ

የነእፓ ሊቀመንበር ለጠ/ሚኒስትሩ ደብዳቤ ፃፉ።

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም የአዲሱን ዓመት 2016 ተንተርሶ ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ግልፅ ደብዳቤ ፃፉ።

በዚህ ደብዳቤያቸው እየተጠናቀቀ ባለው 2015 ዓመት እንዲሁም ባለፉት ዓመታት በሀገራችን ስለነበሩ የሰላም እና ጸጥታ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግሮች በወፍ በረር በመዳሰስ ችግሮቹ ወደ አዲሱ አመት እንዳይሸጋገሩ  አሉኝ ያሉትን የመፍትሄ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅፈውላቸዋል።

ከደብዳቤያቸው የወሰድነው ፦

" ለአብዛኛው የሀገራችን ህዝብ ኑሮ እጅግ ከብዷል።

ሰፊው ህዝባችን ጦም እያደረ የፖለቲካ ስልጣን የያዙ እና በነሱ ጉያ ስር የተወሸቁ ጥቂቶች እጅግ የተንደላቀቀ ህይወት የሚኖሩበት አስጊ ሁኔታ ተፈጥሯል።

የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ፓርቲዎ እና መንግስትዎ እናሳካለን ብለው ለህዝብ ከሚነግሩት እውነተኛ የብልጽግና ጉዞ እየተለየ መጥቷል። 

ለም መሬት እና ለሌሎች የሚተርፍ ወንዞች ያላት ሀገራችን ለበርካታ ልጆቿ የቀን ጉርስ ማቅረብ ተስኗታል።

በቅዱሳን መጽሀፍት የሰላም እና የፍትህ ምድር በመባል የምትታወቀው ሀገር ሰላም እና ፍትህ ርቋታል።

ለዓለም ተምሳሌት የሚሆን የአብሮነት እና የመተሳሰብ ባህል የነበራቸው ባለ ብዙ ቀለም ህዝቦች በመካከላቸው መተማመን ቀንሶ እርስ በርስ እየተጠራጠሩ መኖር ጀምረዋል።

በዜጎች ፊት ደስታ እና ተስፋ እየራቀ መጥቷል፣ ስጋት በኢትዮጵያ ሰማይ ነግሷል። ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ልንሸፋፍናቸው ከማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። 

እንደ ሀገር የገጠሙንን ችግሮች በቅንነት፣ ከፖለቲካ ርእዮት እና ወገንተኝነት ወጥተን በሀገር ልጅነት ስሜት ተወያይተን እና ተጋግዘን ለመፍታት ጊዜ እና ታሪክ አንድ ተጨማሪ እድል ሰጥቶናል።

2015 ተገባዶ አዲስ አመት ለመቀበል ቀናት በቀሩበት ወቅት፣ ሁላችንም ያለፉ ስኬቶቻችንን እና ስህተቶቻችንን ቆም ብለን ልናስተውል ይገባል።

2015ን አገባደን አዲስ ዘመን ለመቀበል እየተሰናዳን ባለንበት ወቅት፣ በተለይም ባለፉት አምስት አመታት በሀገራችን የተከሰቱ እጅግ አውዳሚ ጦርነቶች እና ግጭቶች ቆመው ሰላም የሰፈነባት ሀገር ለመፍጠር ሁላችንም ቃል ልንገባ ይገባል። ይህን አለማድረግ ሁላችንንም በታሪክ ተጠያቂ ያደርገናል። 

ሀገራችን ካለችበት ውስብስብ ቀውስ እንድትላቀቅ፣ ህዝባችንም ሰቅፎ ከያዘው ዘርፈ ብዙ ችግር እንዲላቀቅ ማድረግ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ቢሆንም፣ #የመንግስት ድርሻ ከፍተኛ ነው።

በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት ሀገራችን ካለችበት ችግር እንድትላቀቅ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ያለባቸው ሲሆን፣ የመንግስት የአስፈጻሚ አካል መሪ በመሆን የእርስዎ የግል ኃላፊነት እና ተነሳሽነት እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ በታላቅ ትህትና እና ወንድማዊ ስሜት ላስታውሶት እወዳለሁ። "

(ሙሉ የደብዳቤያቸው ቃል ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
👍2.8K221👎112🙏75🕊37😢15😱11🥰8
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነእፓ የነእፓ ሊቀመንበር ለጠ/ሚኒስትሩ ደብዳቤ ፃፉ። የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም የአዲሱን ዓመት 2016 ተንተርሶ ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ግልፅ ደብዳቤ ፃፉ። በዚህ ደብዳቤያቸው እየተጠናቀቀ ባለው 2015 ዓመት እንዲሁም ባለፉት ዓመታት በሀገራችን ስለነበሩ የሰላም እና ጸጥታ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግሮች በወፍ በረር…
#ኢትዮጵያ

መንግሥት ነፍጥ አንግበው ከሚፋለሙ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ተነሳሽነቱን እንዲወስድ እና የሰላም ጥሪ እንዲያደርግ የነእፓ ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም አዲሱን ዓመት 2016 ተንተርሶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፉት ግልፅ ደብዳቤ ጠይቀዋል።

" ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት ነው " ያሉት ዶ/ር አብዱልቃድር " በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈቱ ዘንድ መንግስት በሆደ ሰፊነት ዳግም የሰላም እጁን በመዘርጋት ነፍጥ አንግበው ከሚፋለሙ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ተነሳሽነቱን እንዲወስድ እና የሰላም ጥሪ እንዲያደርግ " ሲሉ ጠይቀዋል።

ሌላው ሊቀመንበሩ ህዝብን እየፈተነ ላለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መንግሥት መፍትሄ እንዲያበጅ ጠየቀዋል።

" የዜጎቻችንን ህይወት እጅግ ከባድ ያደረገው የኑሮ ውድነት ቀንሶ፣ ዜጎች ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው ተሟልተው መኖር ይችሉ ዘንድ፦
- የመንግስት የወጪ ቅደም ተከተል የሀገርን እና የዜጎችን አንገብጋቢ ችግሮች ያማከሉ እንዲሆን፤
- የመንግስት የገንዘብ እና የፊስካል ፖሊሲዎች የዜጎችን የኑሮ ሸክም ለማቅለል በሚያስችል መልኩ እንዲከለሱ " ጥያቄ አቅርበዋል።

በተጨማሪ ሊቀመንበሩ በህግ ቁጥጥር ስር ለሚገኙ ወገኖች " መንግስታዊ ይቅርታ " እንዲደረግ ጠይቀዋል።

" ሀገር የሚቆመው በመተዛዘን፣ በፍቅር እና በይቅርታ ነው። " ያሉት ዶ/ር አብዱልቃድር ፤ " በተለያዩ ምክንያቶች ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ለሚገኙ ወገኖች መንግስታዊ ይቅርታ በማድረግ፣ እጅግ የተካረረው የሀገራችን ፖለቲካ እንዲረግብ፣ ህዝባችንም የእርቅ እና የሰላም አየር እንዲተነፍስ መንግስት የይቅርታ እጁን እንዲዘረጋ " ሲሉ ጠይቀዋል።

እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ሀገር እና ህዝብ የሰጣቸውን ኃላፊነት በመካድ እና ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ፣ በብልሹ አሰራር በዜጎች ላይ የከፋ አስተዳደራዊ በደል በሚፈጽሙ፣ የሀገርን ሀብት እና ንብረት በሚመዘብሩ፣ #የመንግስት_ሹመኞች እና ግበረ አበሮቻቸው ላይ ስር ነቀል እና የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ሀገርን እና ዜጎችን እንዲታደጉ ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
👍2.76K👎334246🕊102🙏57🥰31😱17😢8
#ነእፓ

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ለኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ደብዳቤ ፃፈ።

ፓርቲው በዚህ ደብዳቤው ፤ " የፓርቲ አባል ያልሆኑ የመንግሥት ሰራተኞች በብልፅግና ፓርቲ ስልጠና እንዲሳተፉ የሚደረግበት አሰራር እንዲቆም " ሲል ጠይቋል።

ነእፓ ፤ #የመንግስት እና #የፓርቲ መደበላለቅ በለውጡ ማግስት መጠነኛ መሻሻል አሳይቶ እንደነበር አስታውሷል።

ነገር ግን በተለይ ከ6ኛው ጠቅላላ ምርጫ ማግስት ጀምሮ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቷል ብሏል።

ከቅርብ ወራት ጀምሮ ገዢው ፓርቲ እያካሄደ ባለው የአባላት ስልጠና፣ የፓርቲው አባል ያልሆኑ የፌዴራል እና የክልል የመንግስት ሰራተኞች (Public servants) የገዢውን ፓርቲ ድርጅታዊ ስልጠና እንዲወስዱ እየተደረገ መሆኑ ለዚህ አንድ ማሳያ ነው ሲል አስረድቷል።

ፓርቲው አለኝ ባለው መረጃ የገዢው ፓርቲ አባላት ያልሆኑ የመንግስት ሰራተኞች ስልጠናውን እንዲወስዱ በተለያየ መንገድ ጫና እየተደረገባቸው መሆኑን ገልጿል።

ይባስ ብሎ በየአካባቢው እየተካሄዱ ያሉ ስልጠናዎች ፦
- አበል፣
- ትራንስፖርት፣
- ሆቴል እና ሌሎች የስልጠና ወጪዎች የሚሸፈኑት #በመንግስት_በጀት መሆኑ ችግሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎታል ብሏል።

በመሆኑም የፓርቲ አባል ያልሆኑ የፌዴራል እና የክልል የመንግስት ሰራተኞች የገዢውን ፓርቲ ስልጠና እንዲወስዱ ማድረግ ህገ መንግስቱን እና የኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ስርአት አዋጃ ቁጥር 1162/2011 የሚቃረን በመሆኑ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ድርጊቱ ይቆም ዘንድ የሚጠበቅበትን እንዲያደርግ ፓርቲው ጥሪ አቅርቧል።

በቀጣይ ተመሳሳይ የህግ ጥሰቶች እንዳይፈጠሩ አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወሰድም አሳስቧል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት፤ ገዢው ፓርቲ የስልጠናና ሌሎች ድርጅታዊ እንቅስቃሴውን በመንግስት ሀብት የሚሸፍንበት አሰራር ህግ እና ስርአትን ያልተከተለ ከመሆኑም ባሻገር የፖለቲካ ሜዳውን የሚያዛንፍ በመሆኑ፣ ድርጊቱ ይታረም ዘንድ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።

በተለይም ፦
- የምርጫ ቦርድ፣
- የገንዘብ ሚንስቴር
- የክልል የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ቢሮዎች፣
- በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምከር ቤቶች አዋጁን በማስከበር ገዢው ፓርቲ ድርጅታዊ መዋቅሩን ከመንግስት መዋቅር ለይቶ እንዲሰራ ኋላፈነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርቧል።

(ፓርቲው የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
748🙏136🕊55😡47😭33😱19😢19🥰11