" መንግሥት የሰውን ሞት ትኩረት እየሰጠው አይደለም " ሲል እናት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ለሰጠው ቃል ወቅሷል።
ድርጊቱን ማስቆም እንዳለበትም አጥብቆ ጠይቋል።
እናት ፓርቲ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በነበረው ቆይታ ምን አለ ?
Q. ፓርቲው አሁናዊ የኢትዮጵያ የጸጥታ እና ደህንነት ሁኔታ እንዴት ይገመግመዋል ? በምን ደረጃ ላይ ይገኛል ?
እናት ፓርቲ ፦
" አገራዊ ሁነቱ የውድቀት አፋፍ ላይ ነው ያለው። ኢትዮጵያ ከእግዚአብሔር ጥበቃ በታች የመጨረሻ የሚባለውን ሰቆቃ እያየች ነው።
ሰው በሰላም ወጥቶ የማይገባባት፣ የሰው ሞት የእንስሳትን ሞት ያህል የማያስጨንቅበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።
በሌላ ጎን ሞቱ አለ፤ በሌላ መንገድ ደግሞ ሞቱን የሚንቅ አለ። ‘ይሄ በለውጥ ሂደት ውስጥ የሚያጋጥም ነውና እኔ ትክክለኛ ስራዬን እየሰራሁ ነው ፤ ከእኔ ስንፍናና ጉብዝና የሚገናኝ አይደለም ' ብሎ የሚያምን፣ ለሕዝብ ሞት እውቅና የማይሰጥ ስርዓት ነው ያለው። "
Q. መፍትሄው ምንድን ነው ?
እናት ፓርቲ ፦
" የአማራ ሕዝብ የህልውና አደጋ፣ ከፍተኛ መከፋት ውስጥ ወድቋል። እናም መንግሥት እሰጥ አገባውን አቁሞ ወደ ድርድር መምጣት አለበት።
ድርድሩ ደግሞ ቄስ፣ ሼይኽ በመላክ አይሆንም። ምክንያቱም ይሄ ስርዓት እንዲህ አይነት እሴቶችን የሚያከብር ይመስላል እንጂ አይቀበልም።
የሚቀበለው ባለዶላር ፤ ባለዩሮዎችን ነው። ስለዚህ እነሱ በተገኙበት ለ “ ሸኔ ” እንደተደረገው ቁጭ ብሎ መነጋገሩ የተሻለ ነው። "
Q. “ መርጦ አልቃሽ ናችሁ ” የሚል አስተያዬት ለፓርቲያችሁ ይሰጣል ፤ ለዚህ ምላሻችሁ ምንድን ነው ?
" በኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ ትግራይ፣ በተለይ አማራ፣ በሃይማኖት ደግሞ ኦርቶዶክስ በፍጹም ታርጌት ተደርጎ ይገደላል። ይሄ ማለት ኦሮሞ ውስጥ ያለው ኦሮሞ አይገደልም ማለት አይደለም።
በእስልምናውም በክርትናውም ነባር በሆኑት ተደጋጋሚ ግድያ ይደረጋል። በዛ ምክንያት ሞቅ ብሎ ተሰምቶ ሊሆን ይችላል።
ሞቅ ብሎ የተሰማው ግን በተግባር የተደረገ ነው። አልተደረገም ብሎ የሞገተን አካል የለም፤ ሊኖርም አይችልም፤ እውነት ነውና። "
Q. እንደ ፓርቲ ደረሰብን የምትሉት ጫና ምንድን ነው ?
እናት ፓርቲ ፦
" በአመራሮች ላይ እስራት እየተፈጸመ ነው። ለአብነትም የወልዲያና አካባቢው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ደርበው ከዋሽ አርባ በእስር እየማቀቀ ይገኛል።
ምርጫ ቦርድ የተሻለ ነበር በዘመነ ብርቱካን፤ አሁን ‘ለምን’ ብሎ የሚጠይቅ የለም። ስብሰባ መሰብሰብ፣ በአካል ማግኘት አይቻልም።
ፓለቲካ ላይ መስራትን በእሳት እንደ መጫወት ነው ያደረገው ስርዓቱ። "
Q. በቀጣይ ይደረጋል ተብሎ ለሚጠበቀው ሀገራዊ ምርጫ ምን አይነት ዝግጅት እያደረጋችሁ ነው ? ለህዝብ አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ እየተዘጋጃችሁ ነው ?
እናት ፓርቲ ፦
" ዝግጅት እያደረግን ነው። እውነትም ምርጫ አለ ወይ ? የሚለው ጥያቄ በሁላችንም አዕምሮ የሚመላለስ ቢሆንም እያደር የምንገልጻቸው ጉዳዮች ይኖራሉ። በምርጫ ተሳትፈን ማሸነፍ ነው በቸኛው አማራጫችን። "
በተለይም ፦
- ስለሀገራዊ ጸጥታ እና ደህንነት ጉዳይ ያላቸውን ግምገማ
- ስለዜጎች የሰብዓዊ መብት ፣
- ስለብልሹ አሰራር
- ስለኑሮ ሁኔታ
- ስለቀጣዩ ምርጫ አማራጭ ሆኖ ለመቅረብ ስላላቸው ዝግጅት በዋነኝነት ያነሳል።
#TikvahEthiopiaFamilyAA
@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
❤542😡79🙏46👏32😭22🤔8🕊8🥰7😢7😱6