" . . . ግድያው መከላከያን በካደ አንድ ግለሰብ የተፈጸመ እንጂ በሠራዊቱ ደረጃ የተፈጸመ አይደለም " - የሶማሌ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን
ከትላንት በስቲያ በሶማሌ ክልል፣ ቀብሪደኀር ከተማ አንድ የመከላከያ ሠራዊትን ከድቶ ከካምፕ ያመለጠ ነው የተባለ አባል ድንገት ተኩስ በመክፈት አራት ሰዎችን ገድሎ ሶስት ሰዎችን ማቁሰሉ ተሰምቷል።
የክልሉ ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ለቪኦኤ ሬድዮ በሠጠው ቃል ፤ ድርጊቱን የፈጸመው ወታደር ከካምፕ #አምልጦ የጠፋና ለሦስት ቀናት ክትትል ሲደረግበት የቆየ እንደሆነ ገልጾ አስቀድሞ ተኩሶ የመታውም ተከታትለው የደረሱበትን የቀብሪ ደኀር ነዋሪ እና የከተማዋን አመራር አባል ነው ሲል ገልጿል።
ግድያውን የፈጸመው ወታደር ተጨማሪ ጉዳት ከማድረሱ በፊት በመከላከያ ሠራዊት አባላት ርምጃ እንደተወሰደበት ተገልጿል።
የሶማሌ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ግድያውን የፈጸመው ወታደር ከ3 ቀናት በፊት ከመከላከያ ካምፕ ያመለጠና ክትትል እየተደረገበት የነበረ የመከላከያ ሠራዊት አባል መሆኑን ገልጾ " ግድያው መከላከያን በካደ አንድ ግለሰብ የተፈጸመ እንጂ በሠራዊቱ ደረጃ የተፈጸመ አይደለም " ብሏል።
በሌላ በኩል የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) ባወጣው መግለጫ ፤ ከቀብሪድሃር ከተገደሉት አራት ሰዎች ሶስቱ ፓርቲው አባላት እንደነበሩ አንዱ ሰው ደግሞ የብልፅግና ፓርቲ አመራር እንደነበር ገልጿል።
የፌዴራል እና የክልሉ መንግሥት እንዲሁም የጦር ሰራዊቱ ድርጊቱን በፍጥነት አጣርተው እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቋል።
ባለፉት ስድስት ወራት በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅት አካባቢውን ለቆ የነበረው መከላከያ ሠራዊት ወደ ሶማሌ ክልል ከተመለሰ በኋላ ይህን መሰል ጥቃት በልዩ ልዩ ከተሞች እየተሰማ ነው ሲል ኦብነግ በመግለጫው አመልክቷል።
ኦብነግ፤ የሠራዊቱ ካምፖች ከከተሞች እንዲርቁና የመከላከያ አባላት ትጥቅ ይዘው ወደ ከተማ ከመግባት እንዲከለከሉ ጠይቋል።
የሶማሌ ክልል ሕዝብ በዘመነ " ኢሕአዴግ " በርካታ ጅምላ ጭፍጨፋዎች እንደተፈጸሙበት ያስታወሰው ኦብነግ ዛሬም የመከላከያ ሠራዊቱን እንደ ጠላቱ እንዲያይ ከሚያደርጉ አካሔዶች መቆጠብ ተገቢ ነው ሲል አስጠንቋል።
ተመሳሳይ ጥቃቶች ዳግም እንዳይፈጸሙ ርምጃዎች መወሰድ አለባቸውም ብሏል።
ትላንት የመከላከያ ሠራዊት አመራሮችና የሶማሌ ክልል አመራሮች የቀብሪደኀር ከተማ ነዋሪዎችን ሰብስበው ስለ ጉዳዩ እንዳወያዩዋቸው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታውቀዋል።
መረጃው የቪኦኤ ሬድዮ አማርኛ አገልግሎት ነው።
ፎቶ፦ ኦብነግ
@tikvahethiopia

👍623👎121❤82🕊24😢23🙏8😭1