TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AdigratUniversity

በጦርነት ምክንያት የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ስራ ዳግም ለማስቀጠል ሲደራ የነበረው ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለሁሉም መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አደረገ።

ዩኒቨርሲቲው መደበኛ ተማሪዎቹን በሙሉ (የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን ጨምሮ) ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 01/2015 ዓ.ም እንደሚቀበል አሳውቋል።

በመሆኑም መደበኛ ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት በዋናው ግቢ በመገኘት እንዲመዘገሹ ተብሏል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦

- የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተማሪ መታወቂያ ካርድ
- ብርድ ልብስ፣ አንሶላና ትራስ ጨርቅ
- ጉርድ ፎቶግራፍ (4)

የመደበኛ መርሃ ግብር ላልሆኑ ተማሪዎች በቅርቡ ጥሪ እንደሚደረግ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

(የዩኒቨርሲቲው ጥሪ ደብዳቤ ከላይ ተያይዟል።)

@tikvahuniversity
👍40751👎47👏21🙏4🥰1