TIKVAH-ETHIOPIA
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት . . . ዛሬ ማክሰኞ የኢትዮጵያ ፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት በ "ኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት" ላይ ሊደረጉ የሚገቡ ናቸው ያላቸው ማሻሻያዎች ላይ ያደረገውን ጥናት ይፋ አድርጓል። ጥናቱ ምን ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ? ጥናቱ ሁሉም የሕገ-መንግሥቱ አንቀፆች ላይ ሳይሆን ብሔር ነክ በሆኑ ድንጋጌዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። አሁን ያለው ሕገ-መንግሥት ላለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት…
ስለ ሕገ መንግሥት ማሻሻል . . .
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲቲዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ምን አሉ ?
" ሕገ መንግሥቱ #ከተረቀቀበት ጊዜ አንስቶ ክርክር እየተነሳ ይገኛል።
በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ለሚፈጠሩ ችግሮች፣ መፈናቀሎች እና ብሔር ተኮር ግጭቶች ሕገ መንግሥቱ መሰረታዊ ድጋፍ ይሰጣል የሚሉ ሃሳቦች ይደመጣሉ፡፡
በሌላ በኩል የማንነት መሰረት ነው የሚሉም አሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ጥናት መሥራት አስፈልጓል።
ሕገ መንግሥቱ የሊህቃኑ ብቻ ሳይኾን የሕዝብም በመኾኑ ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ መጓዝ ይገባል። "
የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ስዩም መስፍን ምን አሉ ?
" ሁሉም የሕገ መንግሥት ድንጋጌዎች በተለያየ መንገድ የሚሻሻሉበት ሁኔታ አለ።
በመደበኛም ይሁን በኢመደበኛ መንገድ ሕገ መንግሥቱ ይሻሻላል።
391 አንቀጽን የያዘው የሕንድ ሕገ መንግሥት 105 ጊዜ ተሻሽሏል። በመሆኑም ሕገ መንግሥቱ ሙሉ ሊሆን አይችልም።
ምንም እንኳን ሕገመንግሥቱ አልተሻሻለም ይባል እንጂ የተለያዩ አንቀጾቹ በአዋጅ እና በትርጉም እንዲሁም በሌላ መንገድ ተሻሽለዋል።
የፌዴሬሽን ምክርቤት ለእነዚህ ሕገ መንግሥት ማሻሻያዎች ዕውቅና ያልነፈገ በመሆኑ እንዲሻሻል እንደፈቀደ ይቆጠራል።
ለምሳሌ ፤ የፌዴራሉ አባል ክልሎችን የሚደነግገው አንቀጽ 47 ተሻሽሏል። በተመሳሳይ የፌዴራል እና የክልል የጋራ ገቢዎች የሚወስነው አንቀጽ 58 እንዲሁም መሬት ማሥተዳደርን በተመለከተ የሚደነግገው አንቀጽ 89 እና ሌሎች አንቀጾች ተሻሽለዋል
ሕገ መንግሥትን በተመለከተ በሀገር ደረጃ 3 ምልከታዎች አሉ።
አንደኛው ሕገ መንግሥቱ ረብ የለውም የሚል ሲኾን ሁለተኛው ደግሞ በፍፁም መነካት የለበትም የሚል ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚል ይገኝበታል።
ጠቃሚው ሀሳብ ሁሉንም ባካተተ መልኩ ይሻሻል የሚለው ነው።
ሕገ መንግሥቱን ማሻሻል እጅግ አስፈላጊ ነው። ሕገ መንግሥቱ የማይሻሻል ከሆነ ጥያቄ የሚያነሱ አካላት ሕገ መንግሥቱን ሙሉ በሙሉ በኃይል የመቀየር እንቅስቃሴ እና ፍላጎት ሊያሳዩ ይችላሉ።
በሀገሪቱ ያሉ የግጭት እና የአለመግባባት ጉዳዮችን በቀላሉ ለመፍታትም እንዲያስችል ሁሉንም ያማከለ ሀሳብ ይዞ ቢሻሻል መልካም ነው። "
#አሚኮ
@tikvahethiopia

👍1.35K👎219❤135🙏32🕊24😢17🥰14😱8
#አብና🕯
" የ4ሰዎች አስክሬን ተገኝቷል ፤ የ6 ሰዎች አስከሬን ሊገኝ አልቻለም ! "
በአማራ ክልል፣ ሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ 10 ሰዎች ሞተዋል።
የጠለምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋየ ወርቅነህ ምን አሉ ?
" የ4 ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል ፤ የቀሪ 6 ሰዎች አስከሬን ሊገኝ አልቻለም።
በጉዳቱ በ8 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል። በደጃች ሜዳ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው።
በመሬት መንሸራተት አደጋው ከ35 በላይ የቤት እንሰሳት ሞተዋል። ከ30 ሄክታር በላይ በሰብል የተሸፈነ መሬት ጉዳት ደርሷል።
በደረሰው አደጋ 480 አባውራዎች እና 2 ሺህ 400 የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል። በቀበሌው ማዕከል ወደሚገኙ ማኅበራዊ ተቋማት በጊዜያዊ እንዲጠለሉ ተደርጓል።
በቀጣይም የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊከሰትባቸው ይችላሉ በተባሉ የኖላ፣ ላጌ፣ ውፋ፣ ኩዳድ እና ጅብ ዋሻ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው። " #አሚኮ

😭2K❤160😢84🕊67🙏46😱42😡25🥰24👏22🤔14