TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የጤናባለሙያዎችድምጽ

" አስተዳደራዊ በደል በድሬዳዋ ጤና ቢሮ ተፈፅሞብኛል " - የሳቢያን ሆስፒታል ሀኪም ዶክተር ሀብታሙ አለሙ

➡️ " በሆስፒታሉ ከተቀጠረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የቀረበበት የዲስፕሊን ጉድለት
የለም " - የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ

በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሳቢያን ሆስፒታል የጠቅላላ ህክምና ሃኪም የሆኑት ዶክተር ሀብታሙ አለሙ በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ባለሙያዎች ያቀረቡትን ቅሬታ በመደገፋቸው በቢሮው አስተዳደራዊ በደል ተፈፅሞብኛል በማለት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተመለከተውና ለባለሞያው የተጻፈው ደብዳቤ " ለስራ በተመደበበት ክፍል የሙያ ስነምግባርን በተፃረረ መልኩ በእናቶች እና በህፃናት ክፍል ወላድ እናቶችን በተደጋጋሚ ማመናጨቅ፣ መሳደብ እና ያለአግባብ ማመላለስ እና ማስጠንቀቂያ ቢሰጥም ባለመታረሙ ወደ ገኦዳ ጉዱንፈታ ጤና ጣቢያ አዘዋውረናል " የሚል ነው።

የጤና ባለሙያው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ?

" በሀገር አቀፍ ደረጃ የህክምና ባለሙያዎች የደመወዝ ጭማሪ ይደረግልን ተብሎ ቅሬታ ሲያቀርቡ ለምን ሃሳቡን ደገፍክ ብለው የድሬዳዋ ከተማ ጤና ቢሮ ሃላፊ እና ምክትል ደውለው ለምን ይሄን አደረክ አሉኝ፣ እኔም ጥያቄው እንደሀገር ነው የቀረበው፣ እንደ ድሬዳዋ አይደለም፣ ይሄ ደግሞ የመብት ጥያቄ ነው ብየ መለስኩኝ ።

የሃላፋዎች ምላሽም በድሬዳዋ ከተማ አንደዚህ መንቀሳቀስ አትችሉም፣ የከተማችንን ስም ያቆሽሽብናል፣ ስለዚህ የህክምና ባለሙያው ዝም ነው ማለት ያለበት አሉኝ።

በነጋታው ከሰዓት የዝውውር ደብዳቤ እና የዲስፕሊን ጉድለት አለብህ ብለው ከሃላፊዎች ሲሰጠኝ የጤና ቢሮ ሃላፊዋን ዶክተር ፅጌሬዳን ለማናገር ቢሮ ስሄድ ባለማግኜቴ ስልክ በመደወል ሳናግሯቸው ቅድሚያ ስሜን አጥፍተሀል እና ፌስቡክ ላይ ይቅርታ ብለህ ፃፍ ከዚያ ውጭ አላናግርህም አሉኝ " ሲሉ አስረድተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ላይ ስማቸው የተጠቀሰው የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጽጌረዳ ክፍሌ እንዲሁም ምክትል ኃላፊ አቶ ዩሱፍ ሰይድ ለማነጋገር በተደጋጋሚ ስልካቸው ላይ ቢደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልም።

በጉዳዩ ላይ የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ ምን አለ ?

ዶ/ር ሀብታሙ " እንደ ሆስፒታል በዲስፕሊን ተፅፎብኝ የሚያውቅ ደብዳቤ የለም " ማለታቸውን ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሳቢያን ሆስፒታል የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑትን ዶክተር አባይነህን ጠይቋል።

በምላሻቸውም " በሆስፒታሉ ከተቀጠረ ጀምሮ እስካሁን ድረስ የቀረበበት የዲስፕሊን ጉድለት ክስ #የለም " ሲሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህንን መረጃ እያዘጋጀ በነበረበት ወቅት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ሲስተር መስከረም አሰፋ በኃላፊነት ቦታቸው ላይ እንደሌሉ ሰምቷል።

ሲስተር መስከረም ይኽ መረጃ እስከተዘጋጀበት ጊዜ ከሥራ እረፍት እንዲያደርጉ እንጂ ዝውውርም ሆነ እድገት እንዳልተሰጣቸው ለማረጋገጥ ችለናል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከደመወዝ ጥያቄው ጋር በተገናኘ እንዲሁም በዚህ መረጃ ላይ ለቀረቡት ቅሬታዎች የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊዎችን ለማናገር ያደረግው ጥረት ባለመሳካቱ ምላሻቸውን ማካተት ሳይቻል ቀርቷል።

በጉዳዩ ላይ ቢሮውም ሆነ ማንኛውም አካል ምላሽ እና ማብራሪያ ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ ለማስተናገድ ዝግጁ መሆኑን ይገልጻል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
አዲስ አበባ
#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
😭911😡166128💔33🤔23😢20🥰10🕊10👏8🙏8😱5