TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#MekelleUniversity

" ዛሬ ሰላም ስለሆነ ወደምትወዱት ዩኒቨርሲቲያችሁ ተመልሳችኃል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ግዙፍ ዩኒቨርሲቲዎች አንዱ የሆነው መቐለ ዩኒቨርሲቲ ትላንት ለተማሪዎቹ ይፋዊ የአቀባበል መርሀ ግብር አካሂዷል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ከትምህርታቸው ርቀው የቆዩ ተማሪዎች፣ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እና የትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች፣ የተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

በዕለቱ ንግግር ያደረጉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኣል ክፍሌ ፤ በርካታ ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው መምህራን በሌለ ግብዓት እና መሰረተ ልማት ዝግጅት አድረግው ተማሪዎችን በመቀበላቸው አድንቀዋል።

" ከትምህርት የተለያችሁበት ወቅት ፈታኝ እንደነበር እናውቃለን " ያሉት ዶ/ር ሳሙኤል " ዛሬ ሰላም ስለሆነ ወደምትወዱት ዩኒቨርሲቲያችሁ ተመልሳችኃል " ብለዋል።

" ወደፊት መልሰን ሰላምን እንዳናጣ እናተ አለኝታ እንድትሆኑን እንፈልጋለን፣ ሀገራችን በሰላም እንድትቆይ ልማቷም እንዲሰፋ ፤ ከድህነት እንድትወጣ ፤ ችግርም ካለ ቁጭ ብሎ የሚነጋገር ትውልድ ከእናተ ጀምረን ማግኘት እንሻለን " ሲሉ ገልጸዋል።

" የሰላም መታጣት ባዶ የሆኑ ቄዬዎችን ሰፈሮችን ፤ የፈረሱ መሰረተ ልማቶችን እንጂ የተሻለ ሀገር አስረክቦ አያውቅም " ያሉት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታው " ወደፊት በሚኖራችሁ የህይወት ምዕራፍ የኢትዮጵያ ኩሩ ልጆች ሆናችሁ ኢትዮጵያን ስታገለግሉ ለንግግር እና ሀሳብ ቦታ እንድትሰጡ ፣ ምትማሩት ትምህርት እንዲቀይራችሁ ፣ ሃሳብን ንግግርን እንድታስቀድሙ፣ ከጦርነት ሰላምን እንድታስቀድሙ አደራ እላለሁ " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የመቐለ ከተማ ከንቲባ አማካሪ አቶ ነጋሽ ኣርዓያ ትምህርት ሚኒስቴር የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቀዋል።

" እዚህ ያሉት ተማሪዎች የተወሰኑ ተማሪዎች ናቸው ፣ የራያ ተማሪዎች አልመጡም፣ የወልቃይት ተማሪዎች ተከዜን ተሻግረው እዚህ መድረስ አልቻሉም ፤ የኢሮብ፣ ባድመ ተማሪዎች ታግተዋል፤ በጣም የተወሰኑ ተማሪዎችን ይዘን ነው እየቀጠልን ያለነው " ብለዋል።

" የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ባልሆነበት ጊዜ ትምህርት መቀጠል አስፈላጊ ቢሆንም ከፊል ነው ፤ ስለዚህ የትምህርት ሚኒስቴር ኃላፊዎች ባላቸው ኃላፊነት የፕሪቶሪያው ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበርና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ አደራ እላለሁ " ሲሉ ተናግረዋል።

ጦርነት #ክፉኛ_ያወደማትን ትግራይን መልሶ በመገንባት ሂደት የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ተማሪዎች ድርሻ ትልቅ ነው ተብሏል።

@tikvahethiopia
👍1.38K👎334174🕊51🙏26😢19👏14🥰7😱5😭1
#MekelleUniversity

የመቐለ ዩኒቨርስቲ በ29ኛ ዙር ከ2000 በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ። ከተመራቂ ተማሪዎች 40 በመቶ ሴቶች ናቸው።

ዩኒቨርስቲው ከተማሪዎች ምረቃ ጎን ለጎን 29ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉም አክብረዋል። 

በምረቓው ስነ-ሰርአት የዩኒቨርስቲው ፕረዚደንት ተወካይ ዶ/ር ዓብደልቃድር ከድር  ንግግር አድርገው ነበር።

ባለፉት 3 አመታት በትግራይ በተካሄደው ጦርነት የደረሰው ሰብአዊና ቁሳዊ ውድመት እጅግ እጅግ ከፍተኛ መሆኑን አስታውሰዋል።

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ በተገኘው አንፃራዊ እርጋታ ዪኒቨስቲው ተስተጓጉሎ የነበረውን የመማር ማስተማር ስራ ፈጥኖ መጀመሩን ገልጸዋል።

የ17 ወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው የነገ ተስፋ አንግበው ወደ ስራ በመመለስ ተማሪዎችን ለዛሬ ምረቃ ላበቁ የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት ምስጋና አቅርበዋል።

ዩኒቨርስቲው የድህረ ጦርነት እቅድ በማዘጋጀት ፤ ከፌደራልና በአገሪቱ ክልሎች እንዲሁም በውጭ ከሚገኙ ዩኒቨርስቲ በመነጋገርና በመፃፃፍ ያለፉት 3 የጦርነት አመታት የሚያካክስ ስራ ለመስራት በከፍተኛ እንቅስቃሴ ውስጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

ዩቨርሲቲው በጦርነቱ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰበት መሆኑን በመረዳት የፌደራል መንግስት የመደበለት አነስተኛ በጀትና የሰራተኞች ውዙፍ ደመወዝ በአፋጣኝ በመመለስ ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ ስራውና ተልእኮው እንዲመለስ እንዲያደርግ አደራ ብለዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር  የማህበራዊ ዘርፍ  ክላስተር ሰክሬተሰሪያት ሃላፊና የመቐለ የኒቨርስቲ ቦርድ አባል ፕሮፌሰር ክንደያ ገ/ህይወት በበኩላቸው ፤ መቐለ ዩንቨርስቲ በጦርነቱ ምክንያት የደረሰበትን ጉዳት ተቋቆቁሞና ወደ ስራ ተመልሶ በአጭር ጊዜ ይህን የመሰለ ድንቅ የምረቃ ስነ-ሰርአት ማዘጋጀቱ ነገ ለመድረስ ያቀደውን እንደሚያሳካ እንደ ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል ብለዋል።

ይህንን የሆነው ለሰላም በተከፈለው እጅግ ወድ ዋጋ በመሆኑ ተመራቂ ተማሪዎች ሆኑ ሌላው የማህበረሰብ ክፍል የተጀመረው ሰላም ስር እንዲሰድ በተሰማሩበት ሁሉ ሰላምና ልማት መስበክ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ዩኒቨርስቲው በ29 አመታት ጉዞው የዛሬ ጨምሮ ከ100 ሺህ በላይ ተማሪዎች ማስመረቁ ከተቋሙ የተገኘ መረጃ ያስረዳል ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።                              
 
@tikvahethiopia
500👏82🕊36🙏23🥰19😢13😡13😱10😭6