TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሱዳን #ኢትዮጵያ

የሱዳን ጋዜጦች የኢትዮጵያን ጦር የተመለከተ ሀሰተኛ ዜናዎች ሲያሳራጩ ነበር።

የተሰራጨው ዜና ምን ነበር ?

ከትላንት ምሽት ጀምሮ የሱዳን ሚዲያዎች በተለይም በ " አልሱዳኒ ጋዜጣ " የኢትዮጵያ ጦር በሱዳን ላይ ጥቃት ከፍተ የሚሉ ሀሰተኛ መረጃዎች ሲያሰራጩ ነበር።

አል ሱዳኒ ፤ በትናንትናው እለት የኢትዮጵያ ጦር በታንክ፣ በታጠቁ ተሽከርካሪዎች እና በብዙ እግረኛ ወታደሮች በመታገዝ በ " አልፋሽቃ አል-ሱግራ " ላይ ወረራ እና ጥቃት ፈጽሟል ፤ የሱዳን ጦርም ጥቃቱን በመመከተ ከፍተኛ ኪሳራ አድርሷል ሲል ነው ሀሰተኛ መረጃ ያሰራጨው።

ይህንን ዜናም በርካቶች ወዲያውኑ ሲቀባበሉት እና ለብዙሃኑ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚ ሲያዳርሱ ነበር።

ይህ መሰል ዜና እንዲሰራጭ ያደረገው የ " አልሱዳኒ " ጋዜጠኛ በትክክለኛ የፌስቡክ ገፁ የተሰራጨው ዜና ትክክል እንዳልሆነ በመግለፅ አንባቢውን ይቅርታ ጠይቋል።

" ዜናው እውነት አይደለም " ያለው ይኸው ጋዜጠኛ " ወረራም አልነበረም ፣ በሱዳንና በኢትዮጵያ ጦር መካከልም ግጭት አልነበረም " ብሏል።

የሰራው ሀሰተኛ ዜና በተፈጠረው ግራ መጋባትና መደናገር እንዳዘነ ይኸው ጋዜጠኛ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ፅፏል።

ሱዳን እጅግ በጣም ሰፊ የኢትዮጵያ መሬትን በኃይል ተቆጣጥራው እንደምትገኝ ይታወቃል። ይህን ያደረገችውም በትግራይ ክልል ጦርነት መነሳቱን እንደ አጋጣሚ በመጠቀም ነበር።

ከዚህ በኃላም ኢትዮጵያ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የድንበር ውዝግብ በጠረጴዛ ዙሪያ በሰላም እና በንግግር መፈታት እንዳለበት በተደጋጋሚ አቋሟን ስትገልፅ ቆይታለች።

ከሰሞኑን በሱዳን የውስጥ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ጦርነት ሳቢያ ሱዳን ከገባችበት ከፍተኛ ትርምስ እንድትወጣ ለማድረግ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደምታደርግ አሳውቃለች።

ግጭት ውስጥ ያሉት የሱዳን ኃይሎችም ግጭት እንዲያረግቡ የሰላም ጥሪ ያቀረበችው ኢትዮጵያ ላለው ችግር አፍሪካዊ መፍትሄ ለመስጠት አዲስ አበባ በሯ ሁሌም ክፍት መሆኑን አቋሟን ገልጻለች።

@tikvahethiopia
👍977👎18489🕊38😱28🙏18🥰13😢13
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update RSF የግብፅ ወታደሮችን ለቀይ መስቀል አስረከበ። የሱዳን ጦርነት በጀመረበት ወቅት በጄነራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ የሚመራው የሱዳን ፋጥኖ ደራሽ (RSF) ኃይል እንደማረካቸው የገለፃቸውን የግብፅ ወታደሮችን ዛሬ ጥዋት ለዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ማስረከቡን አሳውቋል። RSF ለቀይ መስቀል ያስረከባቸው የግብፅ ወታደሮች በማራዊ ጦር ሰፈር የነበሩና ላለፉት 5 ቀናት ይዞ ያቆያቸው ናቸው…
#ሱዳን

የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል / RSF የ72 ሰዓታት ተኩስ አቁም ማድረጉን አውጇል።

ይህን ያደረገው የዒድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ እና ዜጎች ከግጭት ቀጠና እንዲወጡ የሰብዓዊ ኮሪደር ለማመቻቸት በተጨማሪም ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ ለማድረግ መሆኑን ገልጿል።

ምንም እንኳን RSF ይህን ቢልም በሱዳን በተለይም በካርቱም በዛሬው የዒድ አልፈጥር በዓል ዕለት ግጭት መቀጠሉ ፣ ከተማዋ በከባባድ መሳሪያዎች ድምፅ እየተናወጠች ስለመሆኑ ለማወቅ ተችሏል።

RSF የሱዳንን ጦር በአስከፊ ጥቃቶችን እየፈፀመ ነው በሚል ከሷል።

ከሱዳን ጦር በኩል በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተኩስ አቁም ለማድረግ ሃሳብ ይኖር እንደሆነ የታወቀ ነገር እንደሌለ አልጀዚራ ዘግቧል።

ባለፉት ቀናት ለሁለት ጊዜ ተኩስ አቁም ለማድረግ ተሞክሮ ምንም አልተሳካም።

በሱዳን እየተካሄደ ያለው ጦርነት በከተሞች ውስጥ እየተደረገ በመሆኑ በርካቶች ከቤታቸው ለመንቀሳቀስ ተቸግረዋል።

@tikvahethiopia
👍522😢10265🕊56👎17🥰6🙏6
TIKVAH-ETHIOPIA
#IOM እንደ ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት መረጀ በመቶዎች የሚቆጠሩ የቱርክ ዜጎችን ጨምሮ ከ3,500 በላይ ሰዎች በሱዳን ያለውን ከባድ ጦርነት ሸሽተው በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል። ከሚያዚያ 21 እስከ 25 ባለው ጊዜ ውስጥ ከ3500 በላይ የሆኑ የ35 ሀገራት ዜጋ  ስደተኞች ተመዝግበዋል። ከተመዘገቡት አጠቃላይ ስደተኞች መካከል ከ40 በመቶ በላይ የቱርክ ዜጎች ሲሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን 14…
#ኢትዮጵያ #ሱዳን #መተማ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ፤ በሱዳን እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በመሸሽ በየቀኑ ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ የተለያዩ ሀገራት ዜጎች ድንበር አቋርጠው ወደ #ኢትዮጵያ እየገቡ እንደሆነ አሳውቋል።

ይህ ቁጥር አሁንም እየጨመረ ነው ብሏል።

እስካሁን በሱዳን ጦርነት ምክንያት #በመተማ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ዜጎች ቁጥርም በአጠቃላይ ከ12 ሺ በላይ መድረሱ ተመላክቷል።

ሱዳን እና ኢትዮጵያ በሚዋሰኑበት ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ በኩል ሕይወታቸውን ለማትረፍ ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ካሉት መካከል አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ የሌሎች አገራት ዜጎች እንደሚገኙበት የመንግሥታቱ ድርጅት መሥሪያ ቤት መረጃን ዋቢ በማድረግ ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
👍728😢12290🕊38😱22👎14🙏11🥰6
#ሱዳን

የሱዳን ተፋላሚ ኃይሎች ባለፈው ሳምንት በአሜሪካ እና ሱዑዲ አረቢያ አደራዳሪነት የተኩስ ማቆ ስምምነት ላይ ማድረሳቸው ቢነገርም እንደ ከዚህ በፊቶቹ ስምምነቶች ሁሉ ተጥሶ ካርቱም ትላትናም በፍንዳታ ስትናጥ መዋሏን ቪኦኤ ዘግቧል።

የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት ከሰኞ ምሽት ለአራት ሩብ ጉዳይ ይጀምራል የተባለና ለሰባት ቀናት የሚቆይ ነበር።

ተኩስ ኡቅም ላይ ተደረሰ በተባለ በደቂቃዎች ውስጥ የአየር ድብደባ እና የተኩስ ልውውጥ እንደነበር የዓይን እማኞች ተናግረዋል። በሰሜን ካርቱም ውጊያ ሲካሄድ፣ ከካርቱም በሥተ ምስራቅ ደግሞ የአየር ድብደባ እንደነበር ዘገባው ጠቁሟል።

በአንዳንድ የካርቱም ክፍሎች ደግሞ፣ የሚያስጨንቅ ጸጥታ ሰፍኖ እንደነበር እና ነዋሪዎቹም የሰላም ስምምነቱ ውጊያውን ያስቆማል በሚል ተስፋ አድርገው እንደነበር ተነግሯል።

ነዋሪዎች ሕይወት አድን ርዳታ እንዲደርስ እና ወደ ጦር አውድማነት ከተቀየረችው ካርቱም በሕይወት ለመውጣት እንደሚሹም ታውቋል ሲል ቪኦኤ በዘገባው ገልጿል።

እስካሁን ድረስ ከ1,000 በላይ ሰዎች የሞሩ ሲሆን ከሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። 250 ሺሕ የሚሆኑትን ደግሞ #ኢትዮጵያን ጨምሮ የተሻለ ሰላም እናገኛለን ወዳሉባቸው ጎረቤት አገራት ሸሽተዋል።

@tikvahethiopia
👍327😢7646🕊21🙏6👎5🥰4😱3
TIKVAH-ETHIOPIA
የግብፁ መሪ ምን አሉ ? የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር የሁለቶሽ ምክክር ካደረጉ በኃላ በጋራ ሆነው መግለጫ ሰጥተው ነበር። በዚህም ወቅት የግብፁ መሪ ፤ " የአረብ ሊግ ቻርተር በሉዓላዊነታቸው እና በግዛታቸው ላይ ጥቃት የሚደርስባቸውን የአረብ ሀገራት እንድንከላከል ያስገድደናል " ሲሉ ተደምጠዋል። " ግብፅ በሶማሊያ ደህንነት ላይ ምንም አይነት ስጋት እንዲፈጠር…
ራስ ገዟ ሶማሌላንድ ስለ ግብፅ ምን አለች ?

" በስምምነቱ ዙሪያ የሚነሱ ማንኛውንም የውጭ #ጣልቃገብነቶችን እንቃወማለን " - ሶማሌላንድ

ዛሬ የራስ ገዟ ሶማሌላንድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል መግለጫ አውጣለች። በዚህ መግለጫም ስለ ለሰሞነኛው የግብፅ ሁኔታ ምላሽ ሰጥታለች።

ምን አለች ?

ሶማሌላንድ ፤ ከግብፅ ጋር ያላትን ታሪካዊ ግንኙነት ከፍ አድርጋ እንደምትመለከት ገልጻ በአፍሪካ ቀንድ መረጋጋት ላይ ያላትን ስጋትም እውቅና እንደምትሰጥ ገልጻለች።

" ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከተከሰቱ ክስተቶች አንፃር ቀጠናዊ ጉዳዮችን በውይይት እና በትብብር ለመፍታት ያለኝን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጣለሁ " ብላለች።

ይሁን እንጂ በሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እና በ #ኢትዮጵያ 🇪🇹 መካከል ከተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት (MoU) በኋላ የሚነሱ ማንኛውንም አይነት የውጭ #ጣልቃገብነቶችን እንድምትቃወም በድጋሚ አረጋግጣለች።

በመግለጫዋ ፤ " የሶማሌላንድ ሪፐብሊክ እንደ አንድ ሉዓላዊ ሀገር በተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ማዕቀፍ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቶች አከብራለሁ " ስትል ገልጻለች።

" ሁሉም ፍላጎት ያላቸው አካላት ቀጠናዊ መረጋጋትን እና ገንቢ አጋርነትን በማስፈን ላይ እንዲያተኩሩ አበረታታለሁ " ያለችው ሶማሌለንድ ፤ " በዚህ መንፈስም #ግብፅ በቅርብ ጎረቤቶቿ እንደ ፦
* #ሱዳን
* #ሊቢያ
* #ጋዛ ያሉ ግጭቶችን ለመፍታት ዲፕሎማሲያዊ አቅጣጫዋን እንድትቀይር እናበረታታታለን " ብላለች።

" እነዚህ አካባቢዎች (ሱዳን፣ ሊቢያ፣ ጋዛ) በአሁኑ ጊዜ ጉልህ ከሆኑ ተግዳሮቶች ጋር #እየታገሉ ነው ፤ እናም የግብፅ ገንቢ ተሳትፎ ለዘላቂ ሰላም እና ደህንነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለን እናምናለን " ስትል ገልጻለች።

የሶማሌለንድ መንግሥት በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማትን ለማስፈን ከሁሉም ሀገራት ጋር ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን እና ትብብርን ያደርጋል ስትል አሳውቃለች።

" የጋራ ጂኦፖለቲካዊ አካባቢያችንን ሁኔታ ለማሻሻል ከግብፅ እና ከሌሎች ተባባሪዎች ጋር #በመከባበር እና #በጋራ_ጥቅም ላይ የተመሰረተ ገንቢ ግንኙነትን ለመፍጠር እንሰራለን " ስትል ገልጻለች።

@tikvahethiopia
936🙏95😡52🕊50😢19🥰12😭12😱7