TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.61K videos
217 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ግዕዝ

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በግዕዝ ጥናት መስክ በዶክትሬት ዲግሪ ፕሮግራም ሰልጣኞችን መቀበል ሊጀምር ነው።

ዩኒቨርሲቲው ሰልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን ስርዓተ ትምህርት እንዳዘጋጀ አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት በማድረግና ስርዓተ ትምህርት በመቅረፅ ዝግጅት ሲያደረግ መቆየቱን፥ ትምህርቱን ለመጀመር በተዘጋጀ የምክክር አውደ ጥናት ላይ ተገልጿል።

የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት በሰርተፊኬት እና በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ከሚሰጡ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል፦
- ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ይጠቀሳሉ።

Via
@tikvahuniversity
163.03K👏588🙏200😡133🥰51🤔37🕊36💔32😭18😱11😢8