TIKVAH-ETHIOPIA
#IGAD ዛሬ በኡጋንዳ፣ ኢንቴቤ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግስታት (ኢጋድ) መሪዎች ስብሰባ ይደረጋል። ስብሰባው ትኩረት ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች አንዱ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ነው። ሌላው የሱዳን ጦርነት ነው። ለኢጋድ የመሪዎች ስብሰባ እስካሁን ድረስ በታወቀው ፦ ➡ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር የጅቡቲው ፕሬዜደንት ኢሳሜል ኦማር ጌሌህ ➡ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት…
#IGAD
" ... ማንኛውም #ስምምነት ወይም #ዝግጅት በሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት #ፈቃድ መሆን አለበት " - ኢጋድ
የምሥራቅ አፍሪካ ልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ዛሬ ኡጋንዳ ኢንቴቤ ውስጥ አስቸኳይ የመሪዎች ስብሰባውን አድርጎ ነበር።
ይህ አስቸኳይ ስብሰባ የኢጋድ መስራቿ ኢትዮጵያን ጨምሮ የኤርትራ እና የሱዳን መንግሥት ተወካዮች / መሪዎች ባልተገኙበት የተካሄደ ነው።
ስብሰባው ትኩረት ያደረገው ስለ ወቅታዊው የኢትዮጵያ እና ሱማሊያ ግንኙነት ጉዳይ እንዲሁም ስለ ሱዳን ጦርነት ነው።
ከኢጋድ አባል ሀገራት የትኞቹ መሪዎች ተገኙ ?
🇩🇯 የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢማኤል ኦማር ጌሌህ (ስብሰባውን የመሩት እሳቸው ናቸው/ የወቅቱ የኢጋድ ሊቀመንበር ናቸው)
🇰🇪 የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊልያም ሩቶ
🇸🇴 የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ
🇸🇸 የደቡብ ሱዳን ፕሬዜዳንት ሳልቫኪየር ማያርዲት
🇺🇬 የኡጋንዳ ፕሬዜዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ተገኝተው ነበር።
ሌሎችስ እነማን ተገኙ ?
- የኢጋድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ፤
- የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ የሱዳን የግል መልዕክተኛ ራምታኔ ላምራ፣
- የሳውዲ አረቢያ መንግሥት ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋሌድ አልኩራጂ
- የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች / #UAE የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ካሊፋ ሻሂን አል ማራርት
- የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አኔታ ዌበር፤
- #የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክ ሐመር፤
- የአረብ ሀገራት ሊግ ረዳት ዋና ፀሀፊ ሆሳም ዛኪ
- የኢጋድ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ መሐመድ አብዲ ዋሬ
- የደቡብ ሱዳን የኢጋድ ልዩ መልዕክተኛ እና የሱዳን የሰላም ሂደት የኢጋድ ተወካይ አምባሳደር እስማኤል ዋይስ
- የኢጋድ የቀይ ባህር፣ የኤደን ባህረ ሰላጤ እና የሶማሊያ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር መሀመድ አሊ ጉዮ
- #በቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የምስራቅ አፍሪካ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ቱትኩ ኢናም
- የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ቺክ ኮንዴ ተገኝተው ነበር።
ኢጋድ ከስብሰባው በኃላ ባወጣው መግለጫ ምን አለ ?
➡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ግኙነት መካከል የተፈጠረው ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጿል።
➡ በዋነኛ መርህነት የሶማሊያ ሉዓላዊነት ፣ አድነት እና የግዛት አንድነት ሊከበር ይገባል ሲል አረጋግጧል። ማንኛውም ተሳትፎ ይህንን መርህ ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል ብሏል። ማንኛውም #ስምምነት ወይም #ዝግጅት በሶማሊያ ፌዴራላዊ መንግስት #ፈቃድ መሆን አለበት ብሏል።
➡ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው ያለውን ውጥረት በማርገብ በምትኩ ገንቢ የሆነ ውይይት እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
ኢትዮጵያ ስብሰባው ላይ ለምን አልተገኘችም ?
ኢትዮጵያ ከዛሬው የአስቸኳይ ስብሰባ ቀደም ብላ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል " በተደራራቢ መርሃ ግብር " ምክንያት በዚህ ስብሰባ ላይ መገኘት እንዳማትችል ለጂቡቲ የውጭ ጉዳይና አለም አቀፍ ትብብር እና ኢጋድ በድብዳቤ አሳውቃለች።
ኢጋድ ከጠራው ጉባኤ ቀደም በሎ ከተያዘ መርሃ ግብር ጋር የሚጋጭ በመሆኑ እና የተቀመጠውም ጊዜ አጭር በመሆኑ በስብሰባው ላይ መገኘት እንደሚያስቸግራት በዚሁ ደብዳቤ አሳውቃ ነበር።
ነገር ግን " ኢጋድ በሚመራበት ደንብ መሰረት " በተለዋጭ ቀን ለመወያየት ዝግጁ መሆኗን አሳውቃቸዋለች።
(ሙሉ የኢጋድ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)
@tikvahethiopia

❤835😡295🕊90🙏86😭71😢37🥰25😱19
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የአማራ ክልል ይፋዊ ምላሽ ሰጠ። * " የዛቻና የጠብ አጫሪነት የሆነውን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መግለጫ ተመልክተነዋል " - የአማራ ክልል የአማራ ክልል መንግሥት ዛሬ ሀሙስ ባወጣው ይፋዊ መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ መጋቢት 16 ቀን 2016 ዓ/ም የአማራ ክልል ተማሪዎች መማሪያ መጻህፍትን እንደሰበብ ተመርኩዞ ያወጣውን የዛቻ እና የጠብ አጫሪነት…
" ... ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣ እንመክራለን " - የአማራ ክልላዊ መንግሥት
የአማራ ክልል መንግሥት ባወጣው መግለጫ ፤ " የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ለሀገሪቱ ቋሚ ቀውስ ምንጭ ከሚያደርጉት ተግባራት እንዲታቀብ " ሲል #አስጠነቀቀ።
የክልሉ መንግሥት ፥ በአሁን ሰዓት የወልቃይት ጠገዴ ፣ ጠለምት እንዲሁም የወፍላ ወረዳዎች እና የራያ የማንነት ጥያቄ ያለባቸው ወረዳዎች ህዝብ ለረጅም ዓመታት በ " ህወሓት " በኃይል ተገፍፎባቸው የነበረው የማንነትና ጥያቄና ራስን በራስ የማስተዳደር ነጻነት የተመለሰበት እንደሆነ ጠቁሟል።
ህዝቡም እንደማንኛውም የሀገሪቱ ሕዝብ ሁሉ የልማቱ ተሳታፊና ተጠቃሚነት መብቱ ሊቀለበስ የማይችል ነው ብሏል።
" የፕሪቶሪያው የሠላም #ስምምነት ከመፈረሙ በፊት ጀምሮ የአማራ ክልል እንደሌሎቹ ዞኖችና የልማት ትሩፋቶች ሁሉ የአካባቢው ሕዝብም #በትምህርቱም_መስክ ተጠቃሚ እንዲሆን አድርጓል " ሲል ገልጿል።
ክልሉ ፤ እንደሌሎቹ አካባቢዎች የነዚህ አካባቢ ህፃናትም የመማር መብታቸው እንዲከበር ግዴታውን መወጣቱን ገልጿል።
የትምህርት ስርዓቱን ሰበብ በማድረግ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአማራ ክልል ላይ ጥቃት ከመፈጸም የማይመለስ መሆኑን የሚገልጽ የጠብ አጫሪ መግለጫ እንዳወጣ ጠቁሟል።
ይህም " ካለፉት ድርብርብ ውድቀቶች ትምህርት አለመውሰድን ከማሳየት የዘለለ ፋይዳ አይኖረውም " ሲል ተችቷል።
የአማራ ክልል መንግሥት ፥ " ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሀገራችንን እና ሁለቱን ክልሎች ወደ #ቀውስ ከሚያስገቡ ተግባራት በመቆጠብ ከለመደው አጓጉል የካርታ ፖለቲካ ጨዋታ እንዲወጣና የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረጉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩር እንዲሁም አንድ ሀገር ለመገንባት ለሚፈለገው ዘላቂ ሠላምና ለሕዝቦች አንድነት መጽናት በሚበጅ ሐሳብና ተግባር ላይ እንዲያተኩር እንመክራለን " ብሏል።
ሙሉ መግለጫ ፦ https://tttttt.me/tikvahethiopia/86444

👏1.12K😡347🕊203❤104🤔31🙏27😭22🥰19😢17😱16