TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.8K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#UpdateAU #ETHIOPIA የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት ፤ የትግራይ ክልል መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሄደው የሰላም ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኝነቱን መግለፁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል። ይህን የገለፁት የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከፌዴራል መንግስት…
#USA #ETHIOPIA

" አሜሪካ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ትቆማለች ፤ የአፍሪካ ህብረትን (AU) ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን ትደግፋለች " - አንቶኒ ብሊንከን

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሀገራቸው አሜሪካ #ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንደምትቆም እና በአፍሪካ ህብረት እየተመራ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት #እንደምትደግፍ ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት ለሊት ባወጡት መግለጫ ነው።

ብሊንከን ፤ የአፍሪካ ህብረት እየተካሄደ ላለው ግጭት ሰላማዊ መፍትሄ ለማበጀት የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት (TPLF) በተቻለ ፍጥነት ወደ ውይይት እንዲመጡ ለማድረግ እየሰራ ላለው ስራ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ለሰላም ሲባል ከህወሓት ጋር " በየትኛውም ስፍራ፣ በማንኛውም ጊዜ "  ለመነጋገር ዝግጁ መሆኑን እንደገለፀ ያስታወሱት ብሊንከን ለዚህ የመንግስት ዝግጁነት የሚሰጥ ምላሽን እናበረታታለን ብለዋል። ህወሓት (TPLF) ግጭት ለማቆም እና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ያወጣውን መግለጫ እናበረታታለን ሲሉም አክለዋል።

ዓለም አቀፍ አጋሮች የሰላም ሂደቱን ለማገዝ ዝግጁ ናቸውም ብለዋል።

ኤርትራ እና ሌሎችም ግጭቱን ማቀጣጠል ማቆም አለባቸውም ሲሉ ገልፀዋል።

አሜሪካ የኢትዮጵያን #አንድነት#ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት እንደምትደግፍ የገለፁት አንቶኒ ብሊንከን አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ወደ #ጠንካራ_አጋርነት መመለስ ትፈልጋለች ሲሉ ገልፀዋል።

" የአዲስ ዓመት መንፈስን ታሳቢ በማድረግ የአገሪቱ መሪዎች አገሪቱ መከራዋ ወደሚያበቃበት እና ዘላቂ ሰላም ሊያስገኝ ወደሚያስችል መንገድ እንደሚሯት ጥሪ እናቀርባለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
👎1.42K👍1.15K🙏6059😱32😢26🥰20
#AfricanDevelopmentBank

የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓለም አቀፍ ሰራተኞቹን በአስቸኳይ #ከኢትዮጵያ ሊያስወጣ ነው።

ባንኩ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ከአንድ ወር በፊት ዋና የኢትዮጵያ ተወካዩ እና ሌላ የባንኩ ሰራተኛ ላይ በፀጥታ አካላት ድብደባ መፈፀሙን ተከትሎ ነው።

በወቅቱ ባንኩ ቅሬታውን ለመንግስት አቅርቦ የነበረ ሲሆን መንግስትም አስቸኳይ ማጣራት አድርጎ ውጤቱን ይፋ እንደሚያደርግ ገልፆ ነበር።

አሁን ባንኩ ዓለም አቀፍ ሰራተኞቹን " በአስቸኳይ " ከኢትዮጵያ እንዲወጡ ሊያደርግ የወሰነው ድብደባውን ፈፅመዋል በተባሉት የፀጥታ አካላት ዙርያ ስለተደረገው ምርመራ የኢትዮጵያ መንግስት ለባንኩ መረጃ ባለማጋራቱ እንዲሁም በሰራተኞቹ ዘንድ በደህንነታቸው ዙርያ ሙሉ እምነት ሊያገኝ ባለመቻሉ እንደሆነ የባንኩ ፕሬዝደንት ዶ/ር አኪንዉሚ አዴሲና አሳውቀዋል።

ምንም እንኳን ባንኩ ዓለም አቀፍ ሰራተኞቹን ከኢትዮጵያ በአስቸኳይ ለማስወጣት ውሳኔ ላይ ቢደርስም በኢትዮጵያ ያለው ቢሮው ክፍት ሆኖ እንደሚቆይና ውሳኔው ከኢትዮጵያ የተቀጠሩ ሰራተኞችን እንደማይመለከት ገልጿል።

እነዚህ ከኢትዮጵያ የተቀጠሩ ሰራተኞች በስራ ገበታቸው እንደሚቀጥሉና በባንኩ ሙሉ የስራ ስምሪት ውስጥ / የባንኩ ሰራተኞች ሆነው እንደሚቆዩ ማረጋገጫ ተሰጥቷል።

አንድ ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ የባንኩ የኢትዮጵያ ቢሮ ሰራተኛ ከኢትዮጵያ ባስቸኳይ እንዲወጡ የሚደረጉት ዓለም አቀፍ ሰራተኖች ወደ ደቡብ አፍሪካ እና ኬንያ ሊዛወሩ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

እንደ ሬውተርስ ዘገባ የአፍሪካ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ውስጥ የ308 ሚልዮን ዶላር ዋጋ ያላቸው ስምንት ፕሮጀክቶች አሉት።

Credit - Journalist Elias Meseret

@tikvahethiopia
👏1.09K😭317169😱100😢57😡52🕊37🥰22🙏10
#Ethiopia

ማንኛውንም ሰው #ከሀገር_እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለህ/ ተ/ ም/ ቤት  ቀርቧል።

የአዋጅ ማሻሻያው ምን ይዟል ?

ማሻሻያው ማንኛውንም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ የማገድ ስልጣን ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ይሰጣል።

ነባሩ ህግ ምን ይላል ?

" ማንኛውም ሰው #ከኢትዮጵያ_እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው በህግ መሰረት #በፍርድቤት ሲታዘዝ ብቻ ነው " ይላል።

ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ በነባሩ ህግ ላይ የተቀመጠውን የፍርድ ቤትን " #ብቸኛ_ስልጣን " የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ በተጨማሪነት #ያጋራ ነው።

ማሻሻያው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ፦

⚫️ ከሚመለከታቸው የደህንነት አገልግሎት እና ህግ አስከባሪ አካላት ከሚያገኘው መረጃ ወይም አገልግሎቱ በራሱ ከሚያገኘው መረጃ በመነሳት ፤

⚫️ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ሊቀለበስ የማይችል ግልጽና ድርስ የሆነ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ሁኔታ መኖሩን ሲያምን፤ ማንኛውም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ ማገድ ይችላል ሲል ደንግጓል። 

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፤ " ከሀገር እንዳይወጣ ያገደውን ሰው ይዞ የሚያቆይ ከሆነ ፍ/ቤት መቅረቡን ማረጋገጥ አለበት "ም ይላል የአዋጅ ማሻሻያው። 

ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣን ላይ ማሻሻያ የተደረገው ፤ በነባሩ ድንጋጌ ምክንያት እየደረሰ ያለውን " ከፍተኛ ጉዳት " ለመቅረፍ እንደሆነ በማሻሻያው ላይ ሰፍሯል።

አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ መሰረት " ከፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ እስኪገኝ ድረስ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ወይም ሊያደርሱ የሚችሉ ሰዎች ከሀገር እየወጡ ከተጠያቂነት እያመለጡ በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው " ሲል የረቂቅ አዋጁ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፦

ማሻሻያ አዋጁ " #አስተዳደራዊ_ቅጣት " አንቀጽ ይዟል።

" ከጊዜ ወደ ጊዜ በህገ ወጥ መንገድ በሀገራችን ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች እየተበራከቱ፤ በህገ ወጥ ድርጊቶች እየተሳተፉ ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ በመሆኑ በአስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት ከህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ሲል ያስረዳል።

በዚህም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን " በጥቁር መዝገብ እንዲመዘገቡ እና ከሀገር እንዲወጡ ማድረግ ወደ ህጋዊ ስርዓት እንዲመጡ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚና " እንዳለው ተብራርቷል።

#የሚኒስትሮች_ምክር_ቤት በሚያወጣው ደንብ አማካኝነት፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መ/ቤት አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጥል በአዋጅ ማሻሻያው ስልጣን ተሰጥቶታል።

" ይህን አዋጅ አሊያ በዚህ አዋጅ መሰረት የወጣ ደንብ ወይም መመሪያን የጣሰ ማንኛውም ሰው ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል " ይላል ማሻሻያው።

Credit:
#EthiopiaInisider 
#JournalistTesfalemWoldeyes

@tikvahethiopia
😡1.41K210😭75🤔38👏36😢18🕊18😱17🙏17🥰13