#ሸዋሮቢት
የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር ጸጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን መገደላቸውን የከተማው አስተዳደር አሳወቀ።
የከተማ አስታዳደሩ ፤ አቶ አብዱ የተገደሉት " ድንገት ማንነታቸው ባልታወቀ ግለሰቦች ነው " ብሏል።
ግድያው የተፈፀመባቸው የመንግስት ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ሲሰሩ መፈፀሙን የገለፀው አስተዳደሩ ግድያውን በተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ አላደረገም።
በሌላ በኩል ፤ የከተማው ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፓስት ባወጣው አስቸኳይ መግለጫ የሰዓት ገደብ ጥሏል።
ኮማንድ ፖስቱ የከተማውን የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ አስተማማኝ እንዲሆን እና ዜጎች ያለ ስጋት ወጥተው የሚገቡበት ለማድረግ ብዙ ጥረት የተደረገ ቢሆንም አሁንም ከተማዋን ሰው አልባ እንድትሆንና ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንዲከሰት ጥረቶች እየተደረጉ ነው ብሏል።
በዚህም ሳቢያ ፤ ከነገ ከሰኔ 28/2015 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ #ከምሽቱ_12_ሰዓት_ጀምሮ ፦
- ማንኛውም #ተሽከርካሪ ይሁን #የሰው እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ #እንዲገደብ ፤
- አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የምሽት ክለቦችን ጨምሮ ከምሽቱ 12 ስዓት በኃላ ምንም አይነት አገልግሎት እንዳይሰጡ ውሳኔ ተላልፏል።
የከተማው ጊዜያዊ የጸጥታ ኮማንድ ፓስት ፤ የከተማው ነዋሪ ለጸጥታ መዋቅሩ እገዛና ድጋፍ በማድረግ ከተማዋን ካለባት ከፍተኛ የጸጥታ ችግር እንዲታደጋት ጥሪ አቅርቧል።
ምንጭ፦ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopia

👍1.61K😢607👎236❤163🕊77🙏41😱31🥰26
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሸዋሮቢት
በሸዋሮቢት የተጣለው የሰዓት ገደብ ዛሬ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል።
ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ በተጣለው ገደብ መሰረት ከምሽቱ 12 ሰዓት አንስቶ ማንኛውም ሰውም ይሁን ተሽከርካሪ ከተማይቱ ውስጥ ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴ ማድረግ አይችልም።
በተጨማሪ ፤ አገልግሎት ሰጪዎች የምሽት መዝናኛ ቤቶችን ጨምሮ ምንም አይነት አገልግሎት መስጠት አይችሉም።
በሌላ በኩል ፥ ትላንት " ባልታወቁ ገዳዮች " የተገደለቱ የከተማው የፀጥታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አብዱ ሁሴን ስርዓተ ቀብራቸው ዛሬ ተፈፅሟል።
ቅብራቸው የተፈፀመው በዛው ሸዋሮቢት በሚገኘው እንሰርቱ የሙስሊም መካነመቃብር ነው።
አቶ አብዱ የሁለት ወንድ እና የአንድ ሴት ልጆች አባት እንደነበሩ ተገልጿል።
ፎቶ ፦ የሸዋሮቢት ከተማ አስተዳደር

👍419👎125😢106❤47😱9🥰5🙏5