TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰሞነኛው ዝናብ ...

በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ከሰሞኑን እየጣለ ያለው ዝናብ በሰው ህይወት እና በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ፥ ጎፋ ዞን ዑባ-ደብረፀሃይ ወረዳ ዛባ ቀበሌ በጣለው ከባድ ዝናብ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ 21 ሰዎች መሞታቸውን ለማወቅ ተችሏል። በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በህይወት የተረፉ ዜጎ በትምህርት ቤቶች ውስጥ እንዲጠለሉ የተደረገ ሲሆን ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማፈላለግ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ስራ መገባቱ ተሰምቷል።

ተጎጂ ወገኖችን ለመደገፍም በዞኑ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ማቋቋሚያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000511561276 ላይ ድጋፍ እንዲደረግ ተጠይቋል።

#Amhara

በአማራ ክልል፣ ደቡብ ወሎ ዞን ለገሂዳ ወረዳ 02 አዋተል ቀበሌ ሚያዚያ 27/2015 ዓ.ም ምሽት ለተከታታይ 30 ደቂቃ የጣለው በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በእንስሳት፣ በሰብልና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በረዶ ቀላቅሎ የጣለው ዝናብ ከ37 ሄክታር መሬት በላይ የደረሱ ሰብሎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱ ተነግሯል።

#Gambella

በጋምቤላ ክልል ፤ በዲማ ወረዳና አጎራባች ወረዳዎች ከሚያዝያ 25 /2015 ዓ.ም ጀምሮ እየጣለ ባለው ሃይለኛ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው ጎርፍ በሚሊየን የሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

የጎርፍ አደጋው እስካሁን ባለው መረጃ በወረዳው ከ70 በላይ መኖሪያ ቤቶች በውሃ ያጥለቀለቀ ሲሆን በሰብል ላይም ጉዳት አድርሷል።

ጎርፉ በዲማ ከተማ ወንዝ ዳር የነበረውን የከተማ ንፁህ መጠጥ ውሃ መሳቢያ ጀነሬተርና ፖምፕ ግንብ ቤቱን ጨምሮ በሚሊዮን በሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ታውቋል።

በዚህም ችግር ሳቢያ የከተማው ንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት መቆሙ ተነግሯል።

በተመሳሳይ በዲፕ (መርከስ) ቀበሌ የሚገኘው የእኩጉ ስደተኞች መጠለያ ጣብያና የአካባቢው ማህበረሰብ የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት መሳቢያ ጀነሬተሮች በጎርፍ መወሰዱ ታውቋል።

ከዚህ በተጨማሪም የአኮቦ ወንዝ እስከጫፉ ድረስ በመሙላቱ ዲማ ወረዳን ጨምሮ ሁለት አጎራባች ወረዳዎች የሚያገናኝ የአኮቦ ብረት ድልድይ ላይ ጉዳት ደርሷል።

በደረሰው አደጋ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለማገዝ የክልሉ መንግሥትን ጨምሮ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የበኩላቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃ ምንጮች ፦ የጎፋ ዞን ፣ የለገሂዳ እና የዲማ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ናቸው።

@tikvahethiopia
👍377😢16369😱12👎10🕊5🥰3