TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GoE

የፌዴራል መንግስት በቅርቡ ወደ ትግራይ ፣ መቐለ ተጉዞ የነበረው የዲፕሎማቶች የልዑካን ቡድን " የህወሃትን የውሽት ትርክት አስተጋብቷል፤ ይህም ስህተት ነው " ብሏል።

ዛሬ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ሰላማዊት ካሳ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

በመግለጫቸው ላይ መንግሰት በራሱ ተነሳሽነት የተኩስ አቁም ስምምንት ለማድርግ ወሰኖ እንደነበር እና አሁንም #ለሰላም ውይይት ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል።

በአሁን ሰዓት ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ እርዳታ የሚውል የምግብ ድጋፍ በአየር እና በየብስ ትራንስፖርት ተደራሽ እየተደረገ ነው ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ ፤ " መንግስት ወደ ትግራይ የሚገቡ የሰብዓዊ ድጋፍ ባላቋረጠበት እና ክልከላዎች ባላደረገበት ወደ መቐለ ተጉዞ የነበረው የአሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኞችን የያዘው የዲፕልማቶች ቡድን የህወሓት የውሽት ትርክት ማስተጋባቱ ስህተት ነው " ብለዋል።

መንግስት በ #አፍሪካ_ህብረት በኩል የሚካሄደው የሰላም ውይይት ሁሌም በማንኛውም ቦታ እና ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲካሄድ መንግስት ዝግጁ መሆኑን በተደጋጋሚ አረጋግጧል ያሉት ወ/ሮ ሰላማዊት በህወሃት በኩል ከሰላም ድርድር ፍላጎት ይልቅ አሁንም የጦርነት ጉሰማዎችና ለሰላም ውይይት እንቅፋት የሚሆኑ ንግግሮች እየተሰሙ ነው ማለታቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
👍357👎14914😢11👏8🙏5🥰1😱1
" ... እያንዳንዱ የምናደርገው ነገር ፤ ሁሉም እንቅስቃሴያችን ወይም የምንፈርመው ስምምነት ሁሉ የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ህወሓትን በመወከል በፕሪቶሪያ የሰላም ንግግር ላይ የተሳተፉት እና በሰላም ስምምነት ሰነዱ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት አቶ ጌታቸው ረዳ  ዛሬ የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ ከኬንያ ሆነው በትዊተር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " እያንዳንዱ የምናደርገው ነገር ፤ ሁሉም እንቅስቃሴያችን ወይም የምንፈርመው ስምምነት ሁሉ የትግራይን ሕዝብ ጥቅም ለማስጠበቅ ያለመ ነው " ብለዋል።

" ሰላም ህዝባችን ከምንም ነገር በላይ የሚያስፈልገው ነገር ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው ፤ "  የሕዝባችንን ጥቅም ለማስጠበቅ የገባውን ቃል ማክበር መቻላችን ጊዜ የሚፈታው ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ባሰፈሩት ፅሁፍ ላይ ፤ " ወደ ጦርነት የገባነው ፈልገነው ሳይሆን እንደ ህዝብ ህልውናችን አደጋ ውስጥ በመግባቱ ነው" ብለው " የሰላም ስምምነት መፈረም የትግራይን ሕዝብ ሕልውና የሚያስጠብቅ ከሆነ ፣ #ለሰላም ለምን ዕድል አንሰጠውም ? " ብለዋል።

አቶ ጌታቸው ዛሬ በናይሮቢ የተጀማረው ከፕሪቶሪያ የቀጠለው የሰላም ንግግር (በኢትዮጵያ መንግስት እና ሕወሃት ወታደራዊ አመራሮች መካከል) ተሳታፊ ናቸው ይኸው ውይይት ለቀጣይ ቀናት ይቀጥላል።

@tikvahethiopia
👍848👎258🕊13237🙏20😱12😢12
#GetachewReda #AntonyBlinken

የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በአዲስ አበባ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከህወሓት አመራሮች አንዱ ከሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳ ጋር ውይይት አድርገው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ አዲስ አበባ ላይ ከብሊንከን ጋር መገናኘታቸውንና ስለ ሰላም ስምምነቱ አተገባበር እድገት እና ስላሉት እንቅፋቶች ዙሪያ መምከራቸውን ገልጸዋል።

አቶ ጌታቸው ፤ በውይይቱ ወቅት #ለሰላም ያላቸውን የማይናወጥ ቁርጠኝነት እንዲሁም ሰላምን ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎች የሚፈጥሩትን ተግዳሮቶች ለመወጣት በእነሱ በኩል ያላቸው የማያወላዳ ቁርጠኝነት እንዳረጋገጡ ገልጸዋል።

" ጊዜያዊ አስተዳደር መመስረትን ጨምሮ በህዝባችን ላይ እየደረሰ ያለውን ስቃይ ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት ሁሉ እንቅፋት የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የበኩላችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን " ሲሉም ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ከብሊንከን ጋር በነበረው ውይይት በትግራይ ውስጥ እና በትግራይ ላይ በተደረገው ጦርነት ለተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ አስፈላጊት ላይ ሃሳባቸውን እንዳካፈሉ አመልክተዋል።

አቶ ጌታቸው፤ ጠንካራ የሽግግር የፍትህ ማእቀፍ ተቀባይነት ያለውና የሚያስመሰግን ቢሆንም በትግራይ ለተፈፀሙ ወንጀሎች ተጠያቂነት ከሀገራዊ ማዕቀፍ የዘለለ በመሆኑ ዓለም አቀፍ ጥረቶች አስፈላጊ ናቸው የሚል አቋማቸውን እንደገለፁ አስረድተዋል።

አንቶኒ ብሊንከን በበኩላቸው ፤ ሀገራቸው አሜሪካ የሰብአዊ ድጋፍን ለማጠናከር፣ ለመልሶ ማቋቋም ሃብት ለማሰባሰብ፣ እንዲሁም በኢትዮጵያ እና በመላው ቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እንዲሰፍን ከስምምነቱ ተዋናይ ወገኖች ጋር በጋራ እንደምትሰራ በድጋሚ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል ሲሉ አቶ ጌታቸው ረዳ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

@tikvahethiopia
👎1K👍842108🕊54🤔23😱14😢12🥰9🙏7