TIKVAH-ETHIOPIA
ዳግም የሀገራችንን ስም በዓለም ከፍ ያደሩጉት ወጣቶች ! ላለፉት 6 ተከታታይ ቀናት በኮሎምቢያ ካሊ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲካሄድ ሰንብቷል። በዚችም ሀገራችን በ19 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በ10 የውድድር ተግባራት ብቻ ተሳትፋለች። የአትሌቲክስ ቡድናችን በሻምፒዮናው ፦ 🥇6 ወርቅ፣ 🥈5 ብር 🥉1 ነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች በማግኘት ከዓለም ሃገራት አሜሪካንን እና ጃማይካን…
#ኢትዮጵያ🇪🇹
በካሊ በተደረገው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና #ከዓለም 3ኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ዛሬ ምሽት በሰላም አዲስ አበባ ገብቷል።
ቡድኑ አዳሩን ስካይ ላይት ያደርጋል።
ነገ ከማለዳው አንድ ሰዓት ከ30 ጀምሮ ከስካይ ላይት ሆቴል በመነሳት በፓትሮልና በሲቲ ቱር ባሶች ታጅቦ በአዲስ አበባ ከተማ የተመረጡ ዋና ዋና መንገዶች በመዘዋወር ዜጎችን “ እንኳን ደስ አላችሁ ” እንደሚሉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ገልጿል።
በዕለቱም በስካይ ላይት የማበረታቻ ሽልማት እና የእውቅና መርሐ ግብር እንደሚካሄድ ተመላክቷል፡፡
በ19ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ6 ወርቅ፣5 የብር እና1 የነሐስ በድምሩ 12 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አሜሪካና ጃማይካን ተከትላ ሶስተኛ መውጣቷ ይታወሳል።
Credit : ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopia

👍1.78K❤268👏141🙏66😢44🥰34😱11