TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ በፕሪቶሪያ ፤ በኢትጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነትን በተመለከተ የወጣው የጋራ መግለጫ 12 ነጥብ የያዘ ነው። ከዚህም ስምምነት መካከል ፦ - የህወሓት ቡድን #ትጥቅ_እንዲፈታ ከስምምነት ተደርሷል። - የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነት እና #የግዛት_አንድነት ለማረጋገጥ እና የኢፌደሪ ሕገ-መንግሥቱን ለማስከበር የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ተስማምተዋል። …
#ETHIOPIA🇪🇹
#በኢትዮጵያ_መንግስት እና #በህወሓት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ይዘት የሚገልፅ 12 ነጥብ ያለው #የጋራ_መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
ነገ ሁለት ዓመት የሚደፍነውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ሰላማዊ መፍትሄ እንዲበጅለትና ህዝቡም እረፍት እንዲያገኝ ፤ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ፣ አርሶ አደሮችም ወደ እርሻቸው ፣ ሰራተኞችም ወደ ስራቸው፣ ነጋዴዎችም ወደንግዳቸው እንዲመለሱ አጠቃላይ የቀደመው ሁኔታ እንዲፈጠር ሁሉም አካል ዛሬ ወደ ተደረሰው " የሰላም ስምምነት " #ተፈፃሚነት እና #ተግባራዊነት ላይ ትኩረት ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።
የአፍሪካ ህብረት ፤ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የዛሬው ስምምነት በስኬት እንዲጓዝ እና ሰላም እንዲሰፍን የስምምነቱ ትግበራ " ወሳኝ ይሆናል " ሲሉ ነው ያስገነዘቡት።
በዚሁ አጋጣሚ ለሰላም መስፈን የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ከሚጫወቱት ሚና ባለፈ በዚህ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጥላቻ እና እርስ በእርስ መራራቅን ከሚሰብኩ ንግግሮች በመቆጠብ በሰላም ማስፈኑ የራሳቸውን ድርሻ መወጣት አለባቸው።
@tikvahethiopia

🕊3.54K👍1.49K👎301🙏255❤216😱60😢57😡1
#አብን #ኢዜማ
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኀበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) እና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በሀገራዊ ወቅታዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ የመጀመሪያ ዙር ገንቢ ውይይት ማድረጋቸውን በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ አስታውቀዋል።
በቀጣይም #በሚያግባቡ_ሀገራዊ_ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ለማድረግና #የጋራ_አቋም ለመያዝ ከስምምነት ላይ መደረሳቸውንም ገልፀዋል።
ሁለቱ ፓርቲዎች የ " ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ / ህወሓት " ን ከሽብርተኝነት መዝገብ መሰረዝን በቅድሚያ የተቃወሙ ፓርቲዎች ናቸው።
ፓርቲዎቹ ተቃውሟቸውን በየተናጠል ባወጡት በመግለጫ አሳውቀዋል።
ይህ ከተሰማ ከሰዓታት በኃላ ነው ሁለቱ ፓርቲዎች በሚያግባቡ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ለማድረግና የጋራ አቋም ለመያዝ ከስምምነት ላይ እንደደረሱ የተነገረው።

👍3.01K👎849❤173🕊60🤔37🙏23😱13🥰9😢8