TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
62.9K photos
1.61K videos
216 files
4.37K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" እድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸዋል "

ወንጀል የሚፈፅሙበትን ቦታ ቀድመው አይተውና መርጠው ከጨረሱ በኋላ የራይድ ተጠቃሚ መስለው ደውለው በመጥራት የመኪናውን አሽከርካሪ በመግደል መኪናውንና ስልኩን ይዘው የተሰወሩት ግለሰቦች በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት ተቀጡ።

ጉዳዩ እንዲህ ነው፦

1ኛ ተከሳሽ የአብስራ ሰለሞን እና 2ኛ ተከሳሽ በላይነው ንጉስ ካልተያዘው ግብረ-አበራቸው ጋር በመሆን ነሃሴ 6/2012 ዓ.ም ከምሽቱ 2፡30 ሰዓት ራይድ ደውለው አሽከርካሪውን በንፋስ ስልክ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ክልል የሰዎች እንቅስቃሴ ወደማይበዛበት ገባ ያለ ቦታ ይጠራሉ።

ሆራ ትራዲንግ ተብሎ የሚጠራው ስፍራ ሲደርሱ 2ኛ ተከሳሽና ያለተያዘው ግብረ-አበራቸው አሽከርካሪ ንጉስ ከፍያለውን አንገቱን አንቀው በመያዝ ወንበር ስር ሲያስተኙት 1ኛ ተከሳሽም መኪውን እየነዳ ሟችን ወደኋላ በመዞር በተደጋጋሚ በጩቤ ሆዱ ላይ በርካታ ቦታ በመውጋት ህይወቱ እንዲያልፍ አድርገዋል።

በኃላም የሟችን ቪትዝ መኪና፣ የሞባይል ስልክና ያደረገውን ጫማ አጠቃላይ ድምሩ 758,250 ብር የሚያወጣ ንብረት ወስደው ይሰወራሉ።

ፖሊስ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ ሲደረግ ቆይቶ በፈፀሙት ከባድ ውንብድና ወንጀል በፍትሕ ሚኒስቴር ክስ ተመስርቶባቸዋል።

ተከሳሾች ክሱ ፍ/ቤት ቀርበው የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሲጠየቁ ድርጊቱን አልፈፀምንም በማለት ክደው የተከራከሩ ሲሆን ዐቃቤ ህግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች በማቅረብ አስረድቷል።

በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ ግድያና ከባድ ውንብድና ችሎትም የዐቃቤ ህግና ተከሳሾችን ክርክር ሲከታተል ከቆየ በኋላ ተከሳሾች ጥፋተኛ ናቸው በማለት እያንዳንዳቸው በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።

#ፍትህሚኒስቴር

@tikvahethiopia
👍2.84K👏298😢280🙏8663🥰21👎5😱5