TIKVAH-ETHIOPIA
Video
#ጣልያን
በስደተኞች ቁጥር መጨመር እየተቸገረ ያለው የጣሊያን መንግስት ትናላንት ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ስደተኞች የሚታሰሩበት ጊዜ እንዲረዝም እና ህጋዊ የመኖሪያ ፍቃድ የሌላቸው ተይዘው እንዲመለሱ የሚያደርግ ህግ አጽድቋል።
ይህ እርምጃ የተወሰደው ባለፈው ሳምንት 10ሺ የሚሆኑ ስደኞች በጣሊያኗ ላምፔዱሳ ወደብ መድረሳቸውን ተከትሎ ነው።
የስደተኞቹ ወደ ጣሊያን መጉረፍ ህገወጥ ስደተኞችን ለመቆጣጠር ቃል ለገቡት የቀኝ ዘመም ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ትልቅ ችግር እንደፈጠረባቸው ተነግሯል።
ሜሎኒ ፤ በካቢኔ ስብሰብ መጀመሪያ ላይ እንደገለጹት ወደ ሀገራቸው ለመመስ የሚጠባቀቁ ስደተኞች ከ6 እስከ 18 ወራት እስራት ይጠብቃቸዋል።
የመንግስት ምንጮች ካቢኔው መንግስት ያቀረበውን ህግ ማጽደቁን እና ራቅ ባሉ ቦታቸው እስርቤቶች እንደሚሰሩ መወሰኑን ገልጸዋል።
ሜሎኒ ቀደም ሲል በነበሩት የስደተኞች ፖሊሲዎች ምክንያት የተዳከሙትን የማቆያ ቦታዎች ወይም እስርቤቶችን ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።
ህገወጥ ስደተኞች በአስቸኳይ ወደ ሀገራቸው የማይላኩ ከሆነ የሚቆዩበት እስርቤት ይኖራል ያሉት ሜሎኒ ስደተኞችን ለማቆም ከዚህ በፊት የተደረጉ ሙከራዎች ሳይሳኩ መቅረታቸውን ገልጸዋል።
የጣሊያን ባለስልጣናት አብዛኞቹ ስደተኞች በኢኮኖሚ ምክንያት የሚሰደዱ ስለሆነ ጥገኝነት ለመጠየቅ መስፈርት አያሟሉም ይላሉ።
ሜሎኒ በካቢኔ ስብሰብ መጀመሪያ ላይ እንደገለጹት ወደ ሀገራቸው ለመመስ የሚጠባቀቁ ስደተኞች ከ6 እስከ 18 ወራት እስራት ይጠብቃቸዋል።
መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።
@tikvahethiopia

👍357😢157❤63👎48😱20🕊10🙏6🥰3