#ሰበር_ዜና
ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) አረፉ።
በቀድሞ ስማቸው አባ ኃይለማርያም መለሰ (ዶ/ር) በጵጵስና ስማቸው ብፁዕ አቡነ አረጋዊ (ዶ/ር) የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት እና የውጪ ግንኙነት መምሪያ የበላይ ኃላፊ የድሬዳዋና የጅቡቲ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
ብፁዕ አቡነ አረጋዊ ሐምሌ 9 ቀን 2009 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ ዕድ የሾሙት ጳጳሳት 14 ኤጲስ ቆጶሳት መካከል አንዱ ነበሩ።
ብፁዕነታቸው ለረጅም ጊዜ ከሀገር ውጪ እና በሀገር ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው ሊሻላቸው ሳይችል ቀርቶ ከዚህ ዓለም በሞተ ሥጋ ተለይተዋል።
ምንጭ፦ EOTC TV
@tikvahethiopia

😢7.58K🕊459😱262❤246🙏162👍104🥰52🤔50👎9
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በውግዘት የተለዩ 17 "የቀድሞ" አባቶች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት በተደረሰው ስምምነት መሰረት 10ሩን የስምምነት ነጥቦች መቀበልላቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ (ዶ/ር) አስገብተዋል ሲል የቤተክርስቲያኒቱ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ አስታውቋል። ደብዳቤውን ያስገቡት 17 ሲሆኑ አንዱ…
#ሰበር_ዜና
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የሦስቱን አባቶችና የ20ቹን መነኮሳት ውግዘት ከዛሬ 21/07/2015 ዓ/ም ጀምሮ ማንሳቱን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።
ውግዘቱ የተነሳላቸው ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው ማዕረግ እንዲጠሩም ገልጿል።
በዚህ መሠረት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ፣ ብፁዕ አቡነ ኤዎስጣቴዎስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ተብለው እንደሚጠሩና ወደ ነበረ የአባትነት ኃላፊነታቸው የሚመለሱ ሲሆን በይቅርታ የተመለሱት በቁጥር 20ዎቹ መነኮሳትም ቤተ ክርስቲያን በሰጠቻቸው የክህነት አገልግሎት እንዲያገለግሉ ሆኖ በምንኩስና ስማቸው እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።
#EOTCTV

👍912👎404🕊80❤56🙏49🤔38😢21😱17