TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UN

" ሚሊዮኖች በምግብ እና ነዳጅ ዋጋ ንረት እየተሰቃዩ ነው " - ተመድ

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) በዩክሬን ጦርነቱ በመባባሱ ምክንያት ሚሊየኖች #በምግብ እና #በነዳጅ ዋጋ ንረት ምክንያት እየተሰቃዩ ነው አለ።

- በፋይናንስ፣
- በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ
- በአየር ንብረት ለውጥ እየተባባሰ በመጣው ቀውስ ላይ ጦርነቱ ሲጨመርበት በዓለም የኑሮ ውድነት መባባሱን ተመድ ገልጿል።

የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት ያስከተለውን ጫና እንዲያጠና በተመድ የተሰየመው ቡድን ይፋ ባደረገው መረጃ ጦርነቱ ፦
- የምግብ ዋስትና፣
- የኃይል አቅርቦት እና
- በፋይናንስ ላይ ከባድ እና ፈጣን ተጽዕኖው እየታየ ነው ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ ጀርመን እና ፖላንድ የምግብ አቅርቦትን ለመደገፍ በዩክሬን ወደቦች ላይ ተከማችቷል የተባለን እህል ወደተለያዩ አካባቢዎች ለማጓጓዝ የሚደረገውን ጥረት ለመርዳት ዝግጁ ነን ብለዋል።

ከዩክሬን እህል ማውጣት እንዲቻል ለማደራደር ቱርክ ከፍተኛ ሚና እንድትጫወት ይጠበቃል። ሆኖም ቱርክ በጥቁር ባሕር ላይ እህል እንድታጓጉዝ ስምምነት ተደርሷል የሚባለውን ሩሲያ የተሳሳተ መረጃ ነው ብላለች።

ሞስኮ በዩክሬን ወደቦች ላይ ተከማችቷል የሚባለው እህል መጓጓዝ እንዲችል የበኩሏን ኃላፊነት እንድትወጣ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥባለች።

ሌሎች ሃገራት በነዳጅ እና የምግብ እህል እጥረት እንዲቸገሩ ምክንያት ሆናለች በሚል የሚቀርቡ ክሶችንም ውድቅ ማድረጓን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
👍2🕊1