TIKVAH-ETHIOPIA
#ለጥንቃቄ " በፎሬክስ ትሬዲንግ የኦንላይን ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን " የሚል የፌስቡክና የቴሌግራም ማስታወቂያ በሚያስነግሩ የተደራጁ ቡድኖች መጭበርበራቸውን ተበዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል። እነዚህ የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገጾች ስያሜአቸው ከፎሬክስ ትሬዲንግ ጋር የተያያዘ ሲሆን " ትሬድ እናደርጋለን ትርፋማ ትሆናላችሁ " የሚል ቃል በመግባት ከሰዎች ገንዘብ እያስላኩ የማጭበርበር ስራ…
#በድጋሜ⚠️
ውድ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ አድርጉ።
በሀገራችን ያለውን ከፍተኛ የሆነ የኑሮ ጫናን ለመቋቋምና ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዲሁም አንዳንድ ጊዜ ብዙ ሳይደክሙ በርካታ ገንዘብ ለማግኘት በሚደረግ ጥረት በርካታ የሀገራችን ልጆች ደክመው በላባቸው ያገኙትን ፤ ከቤተሰብም ለስራ በሚል የተቀበሉትን ብር በኦንላይን አጭበርባሪ ዘራፊዎች በየዕለቱ እየተበሉ ይገኛል።
ከዚህ ቀደም መላው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት በኦንላይን ከሚደረጉ የማጭበርበር ስራዎች እራሳችሁን እንድትጠብቁ የአደራ ማሳሰቢያ መላክችን ይታወሳል።
አሁንም ሰዎች በመቶ ሺህ የሚቆጠር ብራቸውን እየተበሉ ይገኛል።
እባካችሁን በ " ዋትአፕም " ይሁን በ " ቴሌግራም " አድራሻችሁን አግኝተው የሚያናግሯችሁን የማታውቋቸውን ሰዎች መልዕክት አትመልሱ።
" በተለያየ ኦንላይን ስራ ፣ በፎሬክስ ትሬዲንግ እና በሌሎችም በትንሽ እና በማያደክም ስራ ትርፋማ እናደርጋችኋለን ፤ ይሄን ይሄን ስራ ስሩ በዚህ አካውንት ገንዘብ አስገቡና እኛም መልሰን ትርፉን እናስገባለን " የሚሉ አጭበርባሪዎች ተንሰራፍተዋልና ተጠንቀቁ።
በነገው ዕለት ከዚህ ጋር በተያያዘ ስላጋጠመ ክስተት እናጋራችኃል። ለአሁኑ ግን ምናልባት " ይሄን ስራ ስሩና ትርፋማ ትሆናላችሁ ፤ ገንዘብ ላኩና ትርፉን እንልካለን " በሚል እያባበሉ ገንዘብ እድትልኩ የሚጠይቋችሁን ሰዎች ከማናገር ተቆጠቡ፤ ምንም ገንዘብም አትላኩላቸው።
@tikvahethiopia

❤1.91K🙏804👏164🕊73😢43😱40😭39🥰32😡31🤔1