TIKVAH-ETHIOPIA
#ነእፓ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን ዛሬ መጋቢት 18 /2014 በአዲስ አበባ ማካሄድ ጀምሯል። ይህ የፓርቲው አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ፓርቲውን ወደአዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል ተብሎ ይጠበቃል። ጉባኤው በተለያዩ የፓርቲው ውስጣዊ ጉዳዮችና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራል። በአሁን ሰዓት እየተካሄደ በሚገኘው የማስጀመሪያ ስነስርዓት የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች ፣አባላት፣ የሌሎች የፖለቲካ…
#Freedom_and_Equality
ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን በትናንት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች በተገኙበት አካሂዷል።
ጉባኤው የተሻሻለውን የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።
የተጓደሉ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም ምርጫ አካሂዷል፡፡
ቀደም ሲል በነበረው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት 35 የነበረው ማዕከላዊ ኮሚቴ ብሄራዊ ምክር ቤት በሚል የስያሜ ለውጥ አድርጎ አባላቱንም በ10 አሳድጓል፡፡
በዚህም መሰረት 28 አዳዲስ ቋሚ የብሄራዊ ም/ቤት አባላት በክልሎች እጩ አቅራቢነት ቀርበው በሚስጥር ድምጽ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
በዚሁ መሰረት ጉባኤው 45 ቋሚና 15 ተለዋጭ አባላት ያሉት ብሄራዊ ምክር ቤት አጽድቋል፡፡
በጉባኤው ከ900 በላይ አባላት ከመላው ኢትዮጵያ የተሳተፉ መሆናቸውን ከፓርቲው ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
@tikvahethiopia

👍415👎108👏17❤15😢5😱3🥰1
TIKVAH-ETHIOPIA
#Freedom_and_Equality ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ አንደኛ መደበኛ ጉባኤውን በትናንት የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ታዛቢዎች በተገኙበት አካሂዷል። ጉባኤው የተሻሻለውን የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ ላይ ተወያይቶ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። የተጓደሉ የብሄራዊ ምክር ቤት አባላትንም ምርጫ አካሂዷል፡፡ ቀደም ሲል በነበረው መተዳደሪያ ደንብ መሰረት 35 የነበረው ማዕከላዊ ኮሚቴ ብሄራዊ ምክር ቤት በሚል…
#Freedom_and_Equality
ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ መጋቢት 18 ካካሄደው አንደኛ ጠቅላላ መደበኛ ጉባኤ በኃላ ባለ10 ነጥብ የአቋም መግለጫ አውጥቷል።
ነእፓ በዚህ የአቋም መግለጫው ላይ ካነሳቸው ጉዳዮች ቀዳሚዎቹ የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት እና በሌሎች አካባቢዎች ያሉ የፀጥታ ችግሮች ናቸው።
ፓርቲው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ላይ የተለኮሰው የጦርነት እሳት ሙሉ ለሙሉ ይቆም ዘንድ ሁሉም አካላት ግጭቱን ለማስቆም ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል።
መንግስት በቅርቡ ለትግራይ ክልል ተጨማሪ ሰብአዊ ድጋፍ ከወትሮው በተሻለ መጠን እና ስፋት እንዲደርስ ለማድረግ ያሳየውን ተነሳሽነት እንደሚያደንቅ የገለፀው ነእፓ ውሳኔው በተቻለ ፍጥነት ተግባራዊ ይሆን ዘንድ የሚመለከታቸው አካላት የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቋል።
ነእፓ ፤ ምንም እንኳን በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ያለው ግልጽ እና ሰፊ ጦርነት የተለየ ትኩረት ያገኘ ቢሆንም፣ በሀገራችን የተለያዩ ግጭቶች እንዳሉ ይታወቃል ያለ ሲሆን በእነዚህ ግጭቶች ምክንያት በሰላማዊ ዜጎች ላይ ግድያ፣ መፈናቀል እና የንብረት ውድመት ዛሬም ድረስ ሊቆም አልቻለም ብሏል።
መንግስት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ላይ የተፈጠረውን ችግር እልባት ለመስጠት ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጎን ለጎን በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች የሚገኙ ዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅ በቂ ትኩረት ሊሰጥ ይገባል ሲል አሳስቧል።
(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

👍307👎42👏9😢4😱2