TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
218 files
4.4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AGOA

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ከዚህ ቀደም ከAGOA ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ በተላለፈው ውሳኔ ላይ ማስተካከያ እንዲያደርግና ተመልሳ እንድትገባ እንዲያደርግ የአሜሪካ ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ በደብዳቤ ጠይቋል።

ሙሉ መግለጫው ከላይ የተያያዘ ሲሆን በመግለጫው የተነሱት ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው ፦

- ኢትዮጵያን ከAGOA ዝርዝር ውስጥ ማስወጣት እስካሁን ከ200 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የስራ ዕድል እንዳሳጣ፣ በረዥም ጊዜ ተፅዕኖዎች ተጨማሪ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ለኑሯቸው መሰረት የሆነውን የስራ ዕድል ሊያጡ እንደሚችሉ ይጠበቃል ብሏል።

- ማዕቀቡ በግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን ፤ ብዙሃኑን የኢትዮጵያን ህዝብ የሚጎዳ ነው። አብዛኞቹ ስራ ያጡት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ ሴት ሰራተኞች ናቸው። ይህን ስራ ማጣት ለመላው ቤተሰብ እና ማህበረሰብ ድህነት እና እጦት አስከትሏል።

- የኢትዮጵያ ሕዝብ የተጠየቀውን አድርጓል። መንግሥት ታሪካዊ የሰላም ስምምነት ፈፅሟል ፤ ዕርዳታ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፣ አስፈላጊ አገልግሎቶች እየተመለሱ ነው፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ጥሰትን የሚያጣራ ኮሚሽን ባለፈው ዓመት አዲስ አበባን ጎብኝቷል።

- ኢትዮጵያን ከAGOA ለተጨማሪ አንድ አመት አስወጥቶ ማቆየት ሙሉ በሙሉ ፋይዳ የለውም። የአሜሪካ መንግስት በምትኩ ሀገሪቱ ሰላም ለማስፈን፣ ለመገንባትና ዲሞክራሲያዊትነቷን ለማስጠበቅ እየሰራች ባለችበት ወቅት ድጋፍ ማድረግ አለበት።

ኮሚቴው በመግለጫው ላይ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ውሳኔውን እንደገና እንዲያጤኑት እና በAGOA ውስጥ ኢትዮጵያ እንድትመለስ ጠይቋል።

ኢትዮጵያ ከAGOA ዝርዝር ከወጣች 1 ዓመት ተቆጥሯል።

@tikvahethiopia
👍585👎129🕊16🙏86😢5
የ ' ቅጥር ደመወዝ ' አልበቃ ቢላት ፤ ፊቷን ወደ " ሊስትሮነት " ያዞረችው የምህድስና ምሩቋ ምንታምር በለጠ ፦

" ስሜ ምንታምር በለጠ እባላለሁ።

በሊስቶር ስራ ነው የምተዳደረው አዲስ አበባ፤ ቦሌ አካባቢ ።

የተወለድኩት በአማራ ክልል ፣ ዳንግላ ከተማ ነው። ተወልጄ የተማርኩትም እዛው አካባቢ ነው።

እናት አባቶቼ አቅመ ደካማ ነበሩ። አሁን ላይ በህይወት የሉም ሁለቱም። እህቶች እና ወንድሞች አሉኝ።

ዩኒቨርሲቲ የገባሁት በ2007 ዓ/ም ነው በ2011 ዓ/ም በቴክስታይል ኢንጂነሪንግ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተመርቄያለሁ።

ከተመረቅኩ በኃላ ስራ ፍለጋ ነበር የወጣሁት ፤ ስራ ቶሎ ማግኘት ከባድ ስለነበር ወደ ሐዋሳ ነው የሄድኩት።

ሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ገባሁ፤ በ2500 ብር ደመወዝ ስራ ጀመርኩ የስራ ድርሻዬ የጥራት ደረጃ ማስጠበቅ ቁጥጥር ነበር እሰራበት የነበረው ጨርቃ ጨርቅ ነው፣ ጋርመት ቲሸርቶች ሱሪ ይሰራል እሱ ላይ ጥራት መቆጣጠር ነበር የኔ ስራ።

እዚያ ሁለት ዓመት ሰራሁ ፤ ከዛ በጦርነቱም በ #AGOA / አጎዋ ምክንያት እየቀነሱ ነበር ድርጅቶቹ ሰራተኞችን ፤ ከእሱ ወጥቼ ወደ አዲስ አበባ መጣሁ።

አዲስ አበባ መጥቼ እንደጠበኩት ስራ አላገኘኹም። እየፈለኩኝ ነበር አንዳንድ ቦታዎችም ገብቻለሁ ፤ ደሞዝ የማይሰጥ ድርጅትም አጋጥሞኝ ያውቃል፤ ብዙ ተግዳሮቶችን አሳልፌያለሁ።

ሰው ቤት በተመላላሽነት ምግብ መስራትም ጀምሬ ነበር መጨረሻ ላይ ሊስትሮ / ጫማ ማስዋብ ጀመርኩ።

ዲግሪ ይዣለሁ ፤ ያሳፍራል ዲግሪ ጥቅም የለውም፤ በዲግሪ ስራ ማግኘት አልቻልኩም። ባገኝም ህይወቴን Survive የማያደርግ  ፣ የቤት ኪራይ የማይከፍል ፣ ቤተሰብ የማያስተዳድር ፣ ህይወቴን የማይቀይር ደመወዝ ነው ያለው።

ቤተሰብ መርዳት ቀርቶ እራስን መቀየሪያ የለም ፤ እኔ ዩኒቨርሲቲ ስማር የገዛሁትን ልብስ ነው እስካሁን የምለብሰው ፤ ምናልባት ይሄን ሊስትሮ ከሰራሁ በኃላ ልገዛ እችላለሁ።

ከጥዋቱ 11:30 ከቤቴ እወጣለሁ ፤ ታክሲ ይዤ እዚህ ስራ ቦታዬ ላይ 12:30 ደርሳለሁ ፤ ከጥዋቱ 12:30 ጀምሮ እስከ ምሽቱ 12:40 ድረስ ስራ ቦታዬ ላይ እገኛለሁ።

ደስ ብሎኝ ነው የምሰራው፤ የራሴ መመሪያ አለኝ ፤ በጥዋት ተነስቼ መጥቼ እሰራለሁ፤ ለኔ መስሪያ ቤቴ ድርጅቴ ነው።

ወጣቱ ተስፋ መቁረጥ የለበትም ፤ ያኔ ተስፋ ቆርጬ እራሴን አልጎዳሁም አማራጭ ሳጣ ወደ ሊስትሮ ዝቅ ብዬ መስራት እንዳለብኝ አእምሮዬ ነገረኝ ፤ ይህንን በመስራቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።

ይሄን ወጥሬ ስለምሰራ እራሴን ለመቀየረ፣ ወደዓላማዬ ፣ ወደ መንገዴ ያስገባኛል።

ከዚህ በኃላ የተሻለ ነገር መስራት አስባለሁ። ከዚህ ቀጥሎ ከሞያዬ ጋር ስለሚያያዝ ወደ ፋሽን ፣ ጋርመንት ፣ ስፌት ሞያ ሰልጥኜ ፣ ትንሽዬ ማሽንም ይሁን ገዝቼ ወደዛ የማዘንበል እቅድ አለንኝ። "

Credit : BBC AMHARIC

@tikvahethiopia
👍8.12K😢1.07K849🙏250🥰113👎65🕊62😱60