TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ በከተማዋ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ጳጉሜን 5 ቀን 2014 ዓ.ም የካዳስተር ምዝገባ እና እወጃ ሥራ እንደሚካሄድ አሳውቋል። ከዚህ ቀደም የመሬት ይዞታቸውን በካዳስተር ያላስመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች መረጃዎቻቸውን ለሚቀጥሉት ተከታታይ 15 ቀናት ማዘጋጀት እንደሚችሉ ተነግሯል። ከተማ አስተዳደሩ ከ10 ዓመት በፊት ጀምሮ ሕጋዊ…
#AddisAbaba
" ... የመሬት አገልግሎት ከተመረጡ 25 ቀጠናዎች በስተቀር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ላይ መደበኛ አገልግሎት ይሰጣል " - ኤጀንሲው
የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ይዞታ ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ማምሻውን ለከተማው ኮሚኒኬሽን በሰጠው መረጃ ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት አገልግሎት ከተመረጡ 25 ቀጠናዎች በስተቀር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ላይ መደበኛ አገልግሎት ይሰጣል አለ።
መረጃውን ይፋ ባደረገው የከተማው ኮሚኒኬሽን ገፅ ላይ ፥ የተመረጡ 25 ቀጠናዎች ይባል እንጂ በዝርዝር የተገለፀ ነገር የለም።
ኤጀንሲው በተመረጡ 25 ቀጠናዎች ላይ የይዞታ ምዝገባ የሚያከናውን በመሆኑ ምዝገባውን በሚከናወንባቸው አካባቢዎች ብቻ እስከ ጳጉሜ 5 /2014 ዓ.ም አገልግሎት የሚቋረጥ መሆኑን ገልጿል።
ዛሬ " የመሬት አገልግሎት በሁሉም አካባቢዎች ላይ እንደማይሰጥ " የተሰራጨው መረጃ #ስህተት እንደሆነ ኤጀንሲው አሳውቋል።
ከዚህ ቀደም ይዞታቸውን በ " ዲጂታል ስርአት " ያስመዘገቡ ባለይዞታዎች አገልግሎት ማግኘት ይችላሉም ተብሏል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

👍578👎84❤22👏21😱15😢14🥰1
#Sidama #Hawassa #Motor
በሀዋሳ ከተማ ከሞተር ሳይክል የታርጋ ቁጥጥር ጋር በተያያዘ 221 ሞተሮች መያዛቸዉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና ስምሪት ክፍል ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአንፃሩ የሞተር ባለቤቶች ፤ " መንግስት የሞተር ሳይክል ታርጋ የለም ይለናል፤ በሌላ በኩል ደሞ ትራፊክ ፓሊስ ታርጋ የላቹም ብሎ ያሳድደናል " ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።
አንዳንዶች ደግሞ የቀድሞው የደቡብ ክልል ታርጋ ወደ ሲዳማ ታርጋ መቀየር አለበት በሚል የመያዝና የማንገላታት ነገርም አለ ሲሉ ቅሬታ አቅርበዋል።
የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የትራፊክ ፍሰት ቁጥጥር እና ስምሪት ምክትል ዳይሬክቶሬት ኃላፊ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ደምሴ ፤ ህብረተሰቡ ህጋዊ ታርጋ በማዉጣት ህጋዊ ይሆን ዘንድ 221 ሞተሮች መያዛቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ኢንስፔክተር ተስፋዬ አክለውም፤ " የደቡብ ታርጋ አየተያዘ ነዉ " የሚባለዉ #ስህተት መሆኑን በመግለጽ ማንም በነጻነት ማሽከርከር እንደሚችል ገልጸዋል።
" በዚህ ምክንያት የታሰሩ ሞተሮች ካሉ ስህተት ነው፤ ይለቀቃሉ። የደቡብ ክልል ታርጋ እስካልሸጠ እስካለወጠ ድረስ ችግር የለውም " ሲሉ አረጋግጠዋል።
ከአዲስ ታርጋ ጋር በተያያዘ በጹሑፍ ቅሬታቸውን ያቀረቡ የሀዋሳ ቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፤ " መንግስት የሞተር ሳይክል ታርጋ የለም ይለናል፤ በሌላ በኩል ደሞ ትራፊክ ፓሊስ አባላት ታርጋ የላቹም ብለው ያሳድዱናል። እኔ በግሌ 2% ግብር ከከፈልኩ ወራቶች ተቆጥረዋል ነገር ግን ታርጋ ማግኘት አልቻልኩም የሚመለከተው አካል መፍትኤ ይስጠን፤ ትራፊክ ፓሊስ አባላት እያንገላቱን ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
ይህንን አስመልክቶ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሀዋሳ ከተማ መንገድ ትራንስፖርት ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደስታ ዳንቾ ችግሩ መኖሩን በማመን ችግሩ ከሀገራዊ የዶላር ችግር ጋር ተያይዞ የመጣ (ለታርጋ ማሳተሚያ) መሆኑን አንስተዋል።
" አሁን ላይ ህትመቱ በማለቁ በሚቀጥለዉ ሳምንት ይሰጣል " ብለዋል።
ዳይሬክተሩ አክለውም፥ ታርጋ ያልደረሳቸዉ አሸከርካሪዎች ሪሲት በማሳየት እንዲንቀሳቀሱ የተያዙትም እንዲለቀቁ ከከተማዉ ትራፊክ ፖሊስ አመራሮች ጋር መግባባት ላይ ደርሰናል " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዉናል።
መረጃው የተዘጋጀው በሀዋሳ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።
@tikvahethiopia

🙏118❤46🕊16😱14🥰11👏7😢6😭4😡4