TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ #ሶማሌላንድ በዛሬው ዕለት በኢትዮጵያ እና በሶማሌ ላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈርሟል። ይህ ስምምነት ኢትዮጵያ የባሕር በር የምታገኝበትን መንገድ ይጠርጋል ተብሏል። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ ነው የተባለውን የመግባቢያ ሠንድ በአዲስ አበባ ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ መንግሥት እና የሶማሌላንድ መንግሥት የፈረሙት የትብብር…
ጅቡቲ ከ8 ቀናት በኃላ ዝምታዋን ሰብራለች።

በኢትዮጵያ እና ሶማሌላንድ መካከል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ከተፈመ በኃላ ስለ ቀጠናው ጉዳይ ሀገራት እና ተቋማት አቋማቸው ሲገልጹ ፣ ምክር ያሉትንም ሲለግሱ ነበር።

አብዛኞቹ ስለ ስምምነቱ በቀጥታ ባያነሱም በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ያለው ግንኙነት እንደሚያሳስባቸው ነው የገለጡት።

የኢትዮጵያ ጎረቤት #ጅቡቲ ደግሞ ስምምነቱ ከተፈረመ ከ8 ቀን በኃላ ዛሬ ቀጠናዊ ሁኔታን በተመለከተ አቋሟን ገልጻላች።

ስለ ስምምነቱ ያለችው አንዳች ነገር የለም።

የጅቡቲ መንግሥት ፤ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ  መካከል ያለው ሁኔታ በእጅጉ እንደሚያሳስበውና በአንክሮ እየተከታተለ መሆኑን ገልጿል።

መግለጫው የተለየ ሀገር ስምን ሳይጠቅስ #የሁሉም የኢጋድ አባል ሀገራት ሉዓላዊነት ፣ ነፃነት እና የግዛት አንድነት መከበር እንዳለበት አስገንዝቧል።

NB. የጅቡቲው ፕሬዜዳንት ኢሳማኤል ኦመር ጌሌህ የወቅቱ የኢጋድ ፕሬዜዳንት ናቸው።

ጅቡቲ ሁለቱ ወንድማማች ሀገራት ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የውይይትን መንገድን እንዲመርጡና ያለው ውጥረት እንዲረግብ በመቀራረብ እንዲሰሩ ጥሪዋን አቅባለች።

ሁኔታውን በተመለከተ ውጥረት እንዲረግብ ከሌሎች የኢጋድ አባል ሀገራት ጋር እንደምትሰራ አረጋግጣለች።

ጅቡቲ ለኢትዮጵያ ከጎረቤትነቷ ባለፈ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ ዘርፍ ከፍተኛ ቁርኝት አላት ፤ በዓመታዊ የወደብ እና የትራንዚት አገልግሎትም ከኢትዮጵያ በቢሊዮን ዶላር ታገኛለች።

@tikvahethiopia
😡349189🥰59🙏54🕊54😢17😱16😭10
#CPPI #WorldBank

የዓለም ባንክ ከኤስ ኤንድ ፒ ግሎባል ማርኬት ኢንተለጀንስ ጋር የሚያዘጋጀው የኮንቴይነር ወደብ የአፈጻጸም መለኪያ (Container Port Performance Index - CPPI) የ2023 ደረጃ ባሳለፍነው ሳምንት ይፋ አድርጓል።

ይህ መለኪያ ወደቦች የመረከብ አቀባበላቸውንና እንዴት እንደሚያስተናግዱ በአጠቃላይ ያላቸውን የስራ ቅልጥፍና እና አፈጻጸም የሚለካ ነው።

በዚህም ከ409 ወደቦች የራስ ገዟ #ሶማሌላንድ " #በርበራ " ወደብ 106ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሶማሊያ ፤ " #ሞቃዲሾ " ወደብ ደግሞ 166ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የ " #ጅቡቲ " ወደብ ከመጨረሻ ተርታ 379ኛ ደረጃ ላይ ነው የተቀመጠው።

በዚህ የዓለም ባንክ የአፈጻጸም መለኪያ የበርበራ ወደብ ከሞቃዲሾ እና ጅቡቲ ወደቦች የተሻለ ደረጃ ተሰጥቶታል።

በአጠቃላይ ዓለም አቀፍ ደረጃ ከተሰጣቸው ከ405 ወደቦች በመጨረሻ ተርታ ማለትም 379 ላይ የተቀመጠው የጅቡቲ ወደብ በሀገሪቱ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል።

የጅቡቲ ወደብ በ2022 ከዓለም የተሰጠው ደረጃ 26ኛ ሲሆን በ2023 መለኪያ 379ኛ ላይ መቀመጡ ጅቡቲን አላስደሰተም።

ሀገሪቱ " የ2023 ደረጃ አሰጣጥ ምክንያታዊነት የጎደለው በመሆኑ ያሳስበናል " ያለች ሲሆን " ምን አይነት ሳይንስ ነው የሚያብራራው በዓለም ደረጃ ከ350 በላይ ነጥብ መጣል ? " ስትል ጠይቃለች።

በአንድ ዓመት ውስጥ እንዲህ ያለው ደረጃ መሰጠቱ በመለኪያው ላይ የተዓማኒነት ጥያቄ እንደሚያስነሳ ገልጻለች።

ጅቡቲ ፥ " ደረጃ አሰጣጡ ነጻ እና ከተእጽኖ የጸዳ ነው ወይ ? " ስትል ጠይቃ " ለማንኛውም አድሏዊም ሆነ አልሆነ ጅቡቲ ከሰሃራ በታች እና ምስራቅ አፍሪካ ትልቁ እና ቀልጣፋ ማዕከል ናት " ብላለች።

ሙሉ ዶክመንቱን በዚህ ያግኙ ➡️ CPPI 2023

#WorldBank

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
292👏49😱33🤔32😡28🕊23😭22🙏17🥰16😢16