TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.1K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DebreMarkos

በደብረ ማርቆስ ሠርግ፣ ተስካርና መሠል ፕሮግራሞች በግዚያዊነት ታገደ።

ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ሠርግ ፣ ተስካር እና መሠል የድግስ ፕሮግራሞች በግዚያዊነት የታገደ መሆኑን የኮማንድ ፖስት አባል እና የደብረ ማርቆስ ፖሊስ ጽ/ቤት ሀላፊ ኮማንደር ባንተአምላክ ካሳሁን ገልጸዋል።

" አሁን ካለንበት ሀገራዊ እና ክልላዊ ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር አንገብጋቢ የፀጥታ እና የኢኮኖሚ ችግር አኳያ በመቶሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በአለበት ሁኔታና ለሐገራቸው ሲሉ መስዋትነትን የሚከፍሉ ወንድሞቻችን እንዲሁም በሚሊየን የሚቆጠር የንበረት ውድመት አኳያ ሰርግ እና ሌሎች ፕሮግራሞችን ማካሄድ ለከፋ ርሀብ እና ችግር እንዳንጋለጥ በማሰብ እንዲሁም ያላስፈላጊ የሀብት ብክነትን ለመከላከል ታስቦ በጊዚያዊነት ሰርግ ፣ ተስካር እና መሠል ፕሮግራሞች ታግዷል " ሲሉ ኮማንደር ባንተአምላክ ካሳሁን አስረድተዋል።

በሌላ በኩል በርካታ ህዝብ ተፈናቅሎ እያለ የተትረፈረፈ ድግስ ደግሶ መዝፈን እና መደለቅ ለሞራልም ፤ ለሐይማኖትም ተቀባይነት የሌለው በመሆኑ ሰርግ ለመሠረግ እና ተያያዥ ፕሮግራሞች ለማድረግ ያሰቡ የህብረተሰብ ክፍሎች በክልሉ ለተፈናቀሉ እና ለጥምር ሀይሉ ድጋፍ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ምንአልባት በልዩ ሁኔታ መጋባት ያለባቸው ለኮማንድ ፖስቱ ጥያቄ አቅርበው በማስፈቀድ ጋብቻው ከሰርግ ዝግጅት ውጭ እንዲፈፀም የሚደረግ መሆኑን ገልፀዋል።

ክልከላው ተላልፎ ጋብቻም ሆነ ተስካር እንዲወጣ የሚፈጽም እና የሚያስፈፅም የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ አስፈፃሚ ግብረሀይሉ አስፈላጊውን ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ሁሉም የከተማው ነዋሪ ለተግባራዊነቱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ የደ/ማርቆስ ከተማ ፖሊስ ፌስቡክ ገፅ

@tikvahethiopia
👍14