ትናንት ሌሊት በአዲስ አበባ በ4 የተለያዩ አካባቢዎች የእሳት አደጋ ደርሷል።
በደረሰው የእሳት አደጋ ከ7 ሚሊየን 550 ሺህ ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት መውደሙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳዳር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን #ለኢዜአ አስታውቋል።
በተደረገው መከላከል 67 ሚሊዮን ብር ግምት ያለው ንብረት ማትረፍ መቻሉ ተገልጿል።
የእሳት አደጋው የተከሰተው በአቃቂ ቃሊቲ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተሞች እንዲሁም በየካ ክፍለ ከተማ በሁለት የተለያዩ አካባቢዎች ነው።
አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 8 "መልካ ሸኔ" ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ከምሽቱ 12 ሰዓት ከ50 ገደማ በከብቶች በረትና በ7 አባወራ ቤቶች ላይ ቃጠሎ ደርሶ ውድመት አስከትሏል።
በአደጋው 9 ላሞችና ሁለት ጥጆች ሞተዋል።
ምክንያት ?
አባወራዎቹ የወይራ ጭስ ለማጠን በተያያዘ እሳት መሆኑ ታውቋል።
በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ወይራ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 7 ሰዓት ላይ ጀመስጂድ ቅጥር ግቢ በሚገኝ መጋዘን ላይ የእሳት አደጋ ተከስቷል።
ምክንያት ?
ገና ፖሊስ እያጣራው ነው።
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው "ስኩል ኦፍ ቱሞሮው" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሌሊት 6 ሰዓት ገደማ የመኖሪያ ቤት ላይ ቃጠሎ ተከስቷል።
ምክንያት ?
የኤሌክትሪክ ኮንታክት ነው ተብሏል።
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሁለት "መለስ ፋውንዴሽን" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከሌሊቱ 4 ሰዓት ገደማ በአንድ ማተሚያ ቤት በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ደርሷል።
ምክንያት ?
እስካሁን አልታወቀም።
#ENA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

TIKVAH-ETHIOPIA
የዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ቴክኒካል ረዳቶች ጥያቄ ምንድነው ? ፤ የትምህርት ሚኒስቴር ምላሽስ ? • " እንደዚህ ዓይት ውሳኔ ላይ የተደረሰው አጠቃላይ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ኃላፊዎች ውይይት ካደረጉ በኋላ ነው " - የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት ፍቅረስላሴ አካሉ (ለአዲስ ስታንዳርድ) • " ማህበራችን የሥራ ማቆም አድማ እንዲደረግ ጥሪ አላቀረበም " - ዶ/ር በፍቃዱ ዘለቀ (ለዶቼ…
" የተሰራጨውን የአቋም መግለጫ አላውቀውም " - የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር
የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፤ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች ስም የተሰራጨውን አቋም አላውቀውም ብሏል።
ማህበሩ ይህን ያለው #ለኢዜአ በላከው መግለጫ ነው።
ማህበሩ ፤ ከቅድመ መደበኛ እስከ ከፍተኛ ትምሀርት ድረስ መምህራንና የትምህርት ባለሙያዎችን በማደራጀት በአምስት ዓላማዎች እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጿል።
ከአምስቱ ዓላማዎች መካከል አንዱ የመምህራን መብትና ጥቅም ማስከበር ነው ያለ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የዩኒቨርሲቲ መምራን ያነሱትን ጥያቄዎች ለትምህርት ሚኒስቴርና ለሚመለክታቸው የፌዴራል መንግስት አካላት እያቀረበ ለመፍትሄው እየሰራ መሆኑን አመልክቷል።
" አንዳንድ ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ ማግኘት የሚገባቸው መሆኑን " እናምናለን ያለው ማህበሩ " አንዳንዶቹ ደግሞ ጊዜ የሚፈልጉ መሆናቸው ሊታወቅ ይገባል " ብሏል።
ማህበሩ ከሰሞኑን " የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራንና ቴክኒካል ረዳቶች የአቋም መግለጫ " በሚል ርዕስ " ከህዳር 26/2015 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የሥራ ማቆም አድማ እናደርጋለን " በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ አላውቀውም ብሏል።
እውቅና ያለው የማህበሩ መዋቅር ስም " የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች መምህራን ማህበር " መሆኑን የገለፀው ማህበሩ ፤ መምህራን ማህበራቸው ጉዳዩን በጥብቅ ይዞ እየሰራ መሆኑን አውቀው የተለመደውን የማስተማር የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት በሙያዊ ኃላፊነታቸው እንዲቀጥሉ ጥሪውን አቅርቧል።
#ኢዜአ
ማስታወሻ : https://tttttt.me/tikvahethiopia/74911
@tikvahethiopia

👍550👎441😢17🙏15❤14🕊7