TIKVAH-ETHIOPIA
ℹ የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀሙድ ዛሬ ምሽት ለግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ስልክ ደውለው ነበር። ስልክ የደወሉላቸው አል ሲሲ ድጋሚ የግብድ ፕሬዜዳንት ሆነው በመመረጣቸው " እንኳን ደስ አልዎት " ለማለት ነው ተብሏል። በዚህ የስልክ ውይይታቸው ፤ " በቀጠናው ያሉ የጋራ ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ጥረቶችን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ…
ℹ️ ግብፅ በፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ቃል አቀባይ በኩል ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት ገልጻለች።
የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ሼክ ሀሰን ሞሀሙድ ፤ ትላንት ምሽት ወደ አል ሲሲ ስልክ ደውለው #ከሁለት_ሳምንት በፊት ላሸነፉት ምርጫ " እንኳን ደስ አልዎት " ብለዋል።
የስልክ ውይይቱን ተከትሎ የግብፅ ፕሬዜዳንት ቃል አቀባይ ሁለቱ መሪዎች ፦
- የሁለትዮሽ ጉዳይ ላይ መምከራቸውን፤
- ታሪካዊ ግንኙነታቸውን መሰረት በማድረግ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን የጋራ ትብብርን ለማጎልበት መወያየታቸውን ገልጸዋል።
አል ሲሲ ፤ ግብፅ ከሶማሊያ ጎን እንደምትቆምና ደህንነቷንና መረጋጋቷን ለመደገፍ ፅኑ አቋም እንዳላት መግለፃቸው ተነግሯል።
የሶማሊያው ፕሬዜዳንት ከአል ሲሲ በተጨማሪ ለኳታር ኤሚር ሼክ ታሚም ቢን ሃማድ አልታኒ ስልክ ደውለው ነበር።
ከኳታሩ ኤሚር ጋር ፤ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችሉ የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ የጋራ ጥቅሞችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸው ተሰምቷል።
ትላንት ምሽት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃላቸውን የሰጡ የቀጠናውን ጉዳይ የሚከታተሉ ምሁር ፤ የግብፅ እና ሶማሊያ የስልክ ውይይት ምንም ይሁን ምን የኢትዮጵያ #ፍትሃዊ የሆነውን የባህር በር ጥያቄ ማንሳትን እንደ ክፉ ነገር ፣ ጎረቤቶችን ለመጉዳት አድርገው የሚያዩ ኃይሎች ስላሉ ሁሉንም ነገር በከፍተኛ ጥንቃቄ መያዝ በአይነ ቁራኛ መከታተል ይገባል ሲሉ አሳስበው ነበር።
@tikvahethiopia

😡455👏177❤92🕊30😭19🙏10😱8🥰3😢1
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መቐለ
" ዲግሪ ለመያዝ 8 ዓመታትን መማር #ፍትሃዊ አይደለም " - ተማሪዎች
ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ አደባባይ የወጡ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በፖሊስ በኃይል እንዲበተኑ ተደርገዋል።
ተማሪዎቹ ምንድነው ጥያቄያቸው ?
" አንድ ዲግሪ ለመያዝ 8 (#ስምንት) ዓመታትን መማር #ፍትሃዊ አይደለም " ያሉት ተማሪዎቹ " ከሌሎች ዩኒቨርስቲዎች የምንለይበት ምክንያት የለም ፤ የመውጫ ፈተና መፈተን አለብን " ብለዋል።
" ተመርቀን ወጥተን ስራ መስራት ፤ ህይወትን ማሸነፍ ባለብን በዚህ እድሜያችን የመጀመሪያ ዲግሪ ለማግኘት 8 ዓመታት መጠበቅ የለብንም ፣ የወጣትነት እድሜያችን ያሳስበናል ፤ ብንጮህ ብንጮህ ሰሚ አላገኘንም " ሲሉ ገልጸዋል።
" በዚህ ዓመት መመረቅ ሲገባን ሌላ ተጨማሪ ጊዜ ትማራላችሁ እያሉን ነው ይሄ በፍፁም የማንቀበለው ነው " ብለዋል።
ዛሬ ተማሪዎቹ ከመቐለ ዩኒቨርስቲ ዋናው ግቢ በመነሳት የተለያዩ መፈክሮች በመያዝ ወደ ከተማ ለማምራት ሲሞክሩ በፓሊስ እንግልትና ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል።
የትራፊክ ፖሊስ አባላት ሰልፉን ለማደናቀፍ መንገድ ሲዘጉ ፤ ታጣቂዎች ሰልፈኛ ተማሪዎች ሲደበድቡ ታይተዋል።
ጥያቄ ካነሱ ሰላማዊ ሰልፈኞች መካከል ሶስት ሴት ተማሪዎች በፓሊስ #ሲደበደቡ መመልከቱን ህሉፍ በርሀ የተባለ የአይን እማኝ ገልጿል።
ከዛሬው ሰልፍ ጋር በተያያዘም አንድ የፖሊስ አባል አንዲት #ሴትን እያንገላታ #ገፍትሮ መሬት ላይ ሲጥላት የሚያሳይ ቪድዮ ብዙዎችን አስቆጥቷል።
የመቐለ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሰላማዊ ስልፍ በማስመልከት የዩቨርስቲው አስተዳደር እና የትምህርት ሚንስቴር እንዲሁም የከተማው ፖሊስ እስከ አሁን ያሉት ነገር የለም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተቋማቱ የሚሉት ካለ ተከታትሎ ያቀርባል።
መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የተዘጋጀ ነው።

😢1.73K😭393😡341❤261🕊64👏56🤔39🙏32🥰31😱27