TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63K photos
1.61K videos
216 files
4.38K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"...ቱርክ በየትኛዉም ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጎን ትቆማለች" - አምባሳደር ያፕራክ አልፕ

በኢትዮጵያ የቱርክ አምባሳደር ያፕራክ አልፕ የህዳሴዉ ግድብ ሶስትዮሽ ድርድር እና የኢትዮ ሱዳን የድንበር ዉዝግብ በሠላማዊ መንገድ ሊፈታ ይገባል አሉ።

አምባሳደሩ ይህን ያሉት ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሰጡት ቃለምልልስ ነው።

ቱርክ ከሱዳን እንዲሁም ከኢትዮጵያ ጋር መልካም ግንኙነት ያላት አገር መሆኗን የገለፁት አምባሳደሩ ፥ ጦርነት ለሁለቱም አገራት ስለማይበጅ ልዩነታቸዉን በዉይይት እንዲፈቱ ጠይቀዋል፡፡

አምባሳደር ያፕራክ አልፕ አገራቸዉ በየትኛዉም ዘርፍ ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆምም አስታዉቀዋል፡፡

አገራቸዉ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ልዉዉጥ ወደ 1 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ እንደምትሰራም ገልፀዋል።

ቱርክ እና ኢትዮጵያ በርካታ ዘመናትን ያስቆጠረ ግንኙነት እንዳላቸዉ የገለፁት አምባሳደር ያፕረክ አልፕ፤ አሁን ላይ የአገራቱ አመታዊ የንግድ ልዉዉጥ 6 መቶ ሚሊዮን ዶላር ደርሷል ብለዋል፡፡

በሌላ መረጃ : ኢትዮጵያና ቱርክ በትራንስፖርቱ ዘርፍ በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት የሚያስችላቸውን መግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ከቱርኩ የትራንስፖርት እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር አዲል ካራይስማይሎግሉ ጋር ስምምነቱን መፈራረማቸውን በትዊተር ገጻቸው አሳውቀዋል።

#EthioFM #WeyzeroDagmawitMoges

@tikvahethiopia
#አህያ🫏

በአዲስ አበባ ከተማ ከተለመደው " የከብት ስጋ ውጪ ህገወጥ እርድ እየተፈፀመ ነው " የሚል ጥርጣሬን ተከትሎ ጉዳዩን በአንክሮ እየተከታተለ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ማሳወቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ዘግቧል።

ህገወጥ እርድ የሚፈፅሙ አካላት ላይ የሚጣለው ቅጣት መሻሻሉንም ባለስልጣኑ የገለፀ ሲሆን ህገወጥ እርድ የሚፈፀም ወይም የሚያቀርብ ማንኛውም አካል እስከ 15ሺ ብር የሚደርስ ቅጣት እንደሚጣልበት አመልክቷል።

የአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ፤ ጨለማን ተገን በማድረግ የሚደረግን ህገወጥ እርድ የመከላከል ስራ እየተሰራ ነው ብሏል።

ከአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ጋር በመሆን ህገወጥ እርድን የመቆጣጠርና የማስወገድ ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልጾ ፤ ከእንስሳት ዝውውር፣ ግብይትና ዕርድ ጋር በተያያዘ የወጡ ደንቦች ተሻሽለዋል ፤ ደንቦቹን ተላልፈው የተገኙ አካላትም እስከ 15 ሺህ ብር የሚደርስ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ሲል ገልጿል።

ከህገወጥ ዕርድ ጋር በተያያዘ ከሰሞኑ በከተማዋ ከተለመደው የከብት ስጋ ውጪ እየተሸጠ ተድርጎ ቢወራም  ከዚሁ ጋር  ተያይዞ ባለስልጣኑ ምንም ጥቆማ እንዳልደረሰው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግሯል።

ነገር ግን ባለስልጣኑ ጉዳዩን በትኩረት እየተከታተለው እንደሆነ አስታውቋል፡፡

አሁን ባለው ሁኔታ በ119 ወረዳዎች እንዲሁም በ11ዱም ክፍለ ከተሞች ከዚህ ድርጊት ጋር በተያያዘ ለባለስልጣኑ የደረሰው  ጥቆማ አለመኖሩን ገልጿል።

በሌላ በኩል ፥ የስጋ ነጋዴዎች " የአህያ ስጋ በአዲስ አበባ እየተሸጠ ነዉ " በሚል ምክንያት የቀድሞ ገበያችን በከፍተኛ ደረጃ ተቀዛቅዟል ሲሉ ለ ' ካፒታል ጋዜጣ ' ተናግረዋል።

" በኢትዮጵያ ከተሞች በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ የአህያ ስጋ ለምግብነት እየቀረበ ነዉ " በሚል ተሰራጭቷል በተባለው መረጃ ሳቢያ የዕለት ገበያቸዉ ከቀድሞ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን የሚናገሩት ነጋዴዎቹ " ጉዳዩ በዚህ ከቀጠለ ከገበያዉ እንድንወጣ ሊያደርገን ይችላል " ብለዋል።

" አሁን እስከ 80 ሺህ ብር የተገዛው ሰንጋ በሬ ወደ ተጠቃሚዎች በሚቀርብ ጊዜ የአህያ ነዉ የሚል ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እናስተናግዳለን " በዚህ ምክንያት ሳይሸጥ የሚያድርበት ቀናቶች በርካታ ናቸዉ " በማለት ተናግረዋል።

ከገቢ አንፃር ምን ያህል አጣችሁ ? የሚል ጥያቄ የቀረበላቸዉ ሁለት የስጋ ሽያጭ ሉካንዳ ቤቶች "ከገቢ አንፃር ብቻ ሳይሆን በፊት ለገበያ የምናቀርበው ሁለት ሰንጋ ከብቶች በህጋዊ መንገድ በቄራ እርድ ተፈፅሞ ቢሆንም አሁን ግን አንዱን በትግል ነዉ የምንጨርሰዉ" የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

ሁኔታዉ አሳስቦናል ያሉት የስጋ ነጋዴዎቹ  ከገቢ አንፃር ከ10 እስከ 15 በመቶ የሚሆነዉን ማጣታቸዉን ለ 'ካፒታል ጋዜጣ' ገልጸዋል።

ከሰሞኑን፤ 'ብሩክ ኢትዮጵያ' የተሰኘ የአህያ መብት ተሟጋች ተቋም በኢትዮጵያ በመንግስት ዕውቅና ተሰጥቶት ስራ የጀመረው የአሰላ የአህያ ቄራ ምንም እንኳን ለውጭ ገበያ ታስቦ ቢከፈትም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአሰላ አካባቢ ያሉ ስጋ ቤቶችም ስጋውን ለሽያጭ ሲያቀርቡ እንደተገኙ ተናግሯል።

በአህያ ቆዳ ንግድ ሳቢያ አህዮች ላይ ከፍተኛ የሆነ መመናመን እየታየ ነው ብሏል።

በመንግስት እውቅና የተሰጠው የአሰላ የአህያ ቄራ በቀን ከ100 - 300 አህዮች ለእርድ ያቀርባል፤ በዚህ የተነሳ ከዚህ ቀደም ከ2 ሺህ እስከ 3 ሺህ ብር ይሸጥ የነበረው አህያ አሁን ከ9,000 እስከ 11,000 ብር እየተሸጠ ነው ተብላል።

ለቻይና ባሕላዊ ሕክምና እና ለኮስሞቲክስ አገልግሎት ጥቅም ላይ የሚውለውን ጄልቲን ‘ኢጂአኦ’ ለማምረት የአህያ ቆዳ ተፈላጊ እንደሆነ ይነገራል።

Credit - #Capital #EthioFM

@tikvahethiopia
😡2.01K😭361345😱195😢79🙏66👏62🥰57🕊56