#Amhara
እጅግ አስከፊ ከነበረው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ገና ያላገገመው አማራ ክልል ዳግም የግጭት ቀጠና እየሆነ መምጣቱና የፀጥታውም ሁኔታ አሳሳቢ የሆነ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገልጿል።
በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በ " ፋኖ " የታጠቁ ኃይሎች እና በ " መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች " መካከል በተከሰቱ ግጭቶች የሰዎች ህይወት አልፏል፤ ጉዳትም ደርሷል።
በተለይ ከጥቂት ወራት ወዲህ " የክልሉና የአማራ ህዝብ ህልውና ከፍተኛ አደጋ ላይ ወድቋል " ፣ " መንግሥት የክልሉን ልዩ ኃይል መልሶ ለማደራጀት የሚያደርገው እንቅስቃሴን እንቃወማለን " የሚሉ ወገኖች ከመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተዋል።
በዚህም በአንዳንድ አካባቢዎች አለመረጋጋቶችና የሰላም መደፍረስ እየተበራከቱ መጥተዋል።
ከሰሞኑን ግን በተለያዩ አካባቢዎች ላይ ጠንከር ያሉ ከባድ የተኩስ ልውውጦች እና ግጭቶች መኖራቸውን ነዋሪዎች ይገልጻሉ።
ንፁሃን ዜጎች የተጎዱባቸው ቀጠናዎች ያሉ ሲሆን በተለያዩ መስመሮችም መንገዶች በመዘጋታቸው እንቅስቃሴዎች ተስተጓጉለዋል።
ጥቃት አድራሾቹ " ያልታወቁ ኃይሎች " በሚባሉ አካላትም የመንግሥት የፀጥታ እና አመራር አካላት እየተገደሉ ተገኝተዋል።
በታሪካዊቷ ጥንታዊቷ ላሊበላ አካባቢ በነበረ ግጭትም በረራ መስተጓጎሉ ተሰምቷል።
የክልሉ አስተዳደር ፤ እርስ በእርስ በመገዳደል ዘላቂ በሆነ መንገድ ክልሉ ይጎዳል እንጂ መፍትሄ አያመጣም ብሏል።
ያለው ሁኔታ በዚህ ከቀጠለ ሁለንተናዊ ችግር በክልሉ ይከሰታል የሚለው የክልሉ አስተዳደር ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ እና በውይይት እንፍታው ሲል ጥሪ አቅርቧል።
የሀገር መከላከያ ሠራዊት በበኩሉ ፥ አባላቱ በአማራ ክልል ባሉ በሁለት ስፍራዎች ድንገተኛ ጥቃት ተፈጽሞባቸው እንደነበር አሳውቆ ፤ " በፋኖ ስም እየተንቀሳቀሱ ሰላም በሚያውኩ ላይ እርምጃ ይወሰዳል " ሲል አሳውቋል።
የሀገሪቱ ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን ፤ በአማራ ክልል የሚታየው የፀጥታ ችግር አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አመልክተው ጥያቄዎች ሁሉ በሰላማዊ መንገድ እና በውይይት ሊፈቱ ይገባል ብለዋል።
የተቃዋሚ ኃይሎች በበኩላቸው መንግሥት በክልሉ እያካሄደ ካለው ዘመቻ እንዲቆጠብ እየጠየቁ ይገኛሉ።
ለአብነት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ እና የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤ የጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር " በአማራ ሕዝብ ላይ ወረራ ፈፅሟል ብለዋል። ከዚህ ባለፈም የንፁኃን ግድያ እየፈፀመ ነው " ሲሉ ከሰዋል።
" ይህ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲያቆም አሳስባለሁ ያሉት " የህ/ተ/ም/ቤት አባሉ ፤ መንግስት የቴሌኮም አገልግሎቶችን በመዝጋት ጭምር በአማራ ክልል በከባድ መሣሪያ ታግዞ በንፁኃን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀመ በመሆኑ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ እንዲሁም ሚዲያዎች እንድታወግዙና አገዛዙ ላይ ጫና እንድታሳድሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል።
በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ላይ #የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥን የሚያመልከቱ መረጃዎችን ለማግኘት ችለናል።
@tikvahethiopia

👍975😢581❤118👎89🕊41🥰18🙏14👏10😱1