TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
63.2K photos
1.62K videos
217 files
4.39K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

መረጃ እና መልዕክት ፦ 0919743630

ማርኬቲንግ ፦ 0979222111 ወይም
0979333111

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሀላባ

- " ባለቤቴ ከወንድሙና እህቱ ጋር በመሆን ፊቴ እስኪበላሽ ደበደቡኝ " - ተበዳይ

- " እንዲህ አይነቱን የሴት ልጅ ጉዳት አንታገስም " - የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊዉ አቶ ሙደሲር ጉታጎ

በሀላባ ከተማ " ባለቤቴ ከእህትና ወንድሙ ጋር በመሆን አደጋ አድርሶብኛል " ያለች ተበዳይ የህግ ድጋፍ ስጡኝ ስትል በማህበራዊ ሚዲያ ጥያቄ አቅርባለች።

ጉዳዩን የተመለከተው የሀዋሳ የቲኪቫህ ቤተሰብ አባል ባደረገዉ ማጣራት ፥ ተጎጅዋ ፊቷ ላይ ጉዳት መደረሱን በተጨማሪ የሷና የመጀመሪያ ልጇ ሰዉነት ትክሻቸዉ አካባቢ ' ጥርስ ንክሻ ' እንደደረሰባቸዉ ለማወቅ ችሏል።

የግል ተበዳዩዋ እናት ለቲክቫ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ልጃቸዉና የልጅ ልጃቸዉ በደም ተዘፍቀዉ በምሽት ወደቤት እንደመጡና በወቅቱ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገንተው እንደነበር ገልጸዋል።

የግል ተበዳዩዋ ወ/ሮ አበባ ቦረና ፤ " ምንም እንኳን የጋራ አራት ልጆች ቢኖሩንም ካሁን በፊት በመካከላችን በነበረ ግጭት ምክኒያት በፍርድ ቤት ለመለያየት ጫፍ ከደርሰን በኋላ  በሽማግሌ ተመልሰን አንድ ላይ መኖር ከጀመርን 3 ወር አልሆነም " ብላለች።

" ምንም እንኳን ቀን ላይ ቀላል ጭቅጭቅ ውስጥ ብንገባም ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ እንዲህ ያደርጋል ብዬ ፍጹም አልጠበኩም " ስትል ተናግራለች።

" በተለይ ተሰብስበዉ ሲደበድቡኝ ለመገላገል የገባዉን የመጀመሪያ ልጃችን ላይ ላይ በዚህ ልክ ይጨክናል ብዬ አላሰብኩም ነበር "  ብላለች።

ጉዳዩን በተመለከተ የጸጥታ አካላት ምን እየሰሩ ነዉ ? በማለት የጠየቅናቸው የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ሀላፊ አቶ ሙደሲር ጉታጎ ፤ " እንዲህ አይነቱን የሴት ልጅ ጉዳት አንታገስም " ብለዋል።

ጉዳዩን በሰሙ ቅጽበት የከተማው ፖሊስ በፍጥነት ችግር ፈጣሪዎችን  ይዞ እንዲያጣራ ማዘዛቸዉንም ነግረዉናል።

አቶ ሙደሲር  ጉዳዩ ተጣርቶ የሚደረስበትን ውጤት እንደሚያጋሩን ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
😡1.34K😭253147😢82🤔44🙏40🕊34😱30👏25🥰9