#ኢትዮጵያ
የፀጥታ እና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ፥ ከሀገር ውጭ የሚገኙትን ፖለቲከኛው አቶ ልደቱ አያሌውን ፣ በቅርቡ ከልዩ ኃይል ጋር በተያያዘ በአማራ ክልል የተፈጠረውን አለመግባባት በስምምነት እንደፈታ የተነገረለት የምስራቅ አማራ ፋኖ አመራር ምሬ ወዳጆን ጨምሮ በሀገር ውስጥ በተደጋጋሚ ጊዜ በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የሚዲያ ሰዎች እና በውጭ ሀገር ያሉ በርካታ የሚዲያ ሰዎችን " ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል ለማፍረስ እንዲሁም #በሽብር_ወንጀል " እፈልጋቸዋለሁ ብሏል።
ግብረ ኃይሉ በአማራ ክልል እየወሰድኩ ነው ባለው እርምጃ " ፅንፈኛ ናቸው " ላላቸው ኃይሎች የሚዲያ እና ፕሮፖጋንዳ ክንፍ በመሆን እየሰሩ ናቸው ያላቸውን አካላት ነው #በወንጀል እንደሚፈልጋቸው ያሳወቀው።
በውጭ ሀገር ያሉትን ተፈላጊ ግለሰቦች በዐለም አቀፉ የፖሊስ ድርጅት እንዲሁም ከሚኖሩባቸው ሀገር መንግስት የፀጥታ እና ደህንነት ተቋማት ጋር በተመሰረቱ የትብብር ማዕቀፎች ተላልፈው እንዲሰጡ እየሰራሁ ነው ብሏል።
በሌላ በኩል የፀጥታ እና ደህንነት ግብረ ኃይሉ በአማራ ክልል " በህቡዕ አደረጃጀት " ውስጥ ሲንቀሳቀሱና የሽብር ተግባር ሲፈጽሙ አገኘኃቸው ያላቸውን 47 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን አሳውቋል።
ከእነዚህ 47 ግለሰቦች ውስጥ ረዳት ፕ/ር ሲሳይ አውጋቸው፣ ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ ለእስር ተዳርጋ የተፈታችው መምህርት መስከረም አበራ ይገኙበታል።
ግብረ ኃይሉ የተያዙት ግለሰቦች የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮችን " ለመግደል፣ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል በመናድ የክልሉን መንግሥታዊ መዋቅር በመቆጣጠር የፌደራል መንግሥትን ለመጣል " በአገር ውስጥ እና በውጭ አገራት ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ ስለደረስኩባቸው ነው ብሏል።
ግብረ ኃይሉ ለመገናኛ ብዙሃን ያሰራጨው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia

👎2.4K👍1.02K❤133😱18🕊17😢11🙏9🥰5